ፈልግ

ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 2/ 2016 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው የአፍሪካ ሴት የነገረ መለኮት ምሁራን እና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 2/ 2016 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው የአፍሪካ ሴት የነገረ መለኮት ምሁራን እና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ  

የሴቶች ድምፅ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ማንነቷን እንድትቀበል ይረዳታል ተባለ

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 'አፍሪካውያን ሴት የነገረ መለኮት ሊቃውንት እና ሲኖዶሳዊነት' ላይ የሚወያይ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተከፈተ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

“የሴቶች ድምጽ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ማንነቷን እንድታገኝ እና አንዲት፣ ቅድስት፣ ካቶሊካዊት እና ሐዋርያዊት የሆነች ሲኖዶሳዊ ማንነቷን እንድትቀበል ይረዳታል” ያሉት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው ‘የአፍሪካ ሴት የሥነ መለኮት ሊቃውንት እና ሲኖዶሳዊነት’ ጉባኤ መክፈቻ ላይ አባ ጆሴ ሚናኩ የሰጡት ማረጋገጫ ነው።

የአፍሪካ እና ማዳጋስካር የኢየሱሳውያን ጉባኤ ፕሬዝደንት የሆኑት አባ ሚናኩ በመክፈቻው ንግግር ላይ ስለ ሴት የነገረ መለኮት ሊቃውንት እና በአጠቃላይ የሴቶች ድምጽ ከቤተክርስቲያን ጋር ስላለው ጠቀሜታ ተናግረዋል።

ሴቶች እና የቤተክርስቲያን ካቶሊካዊነት

የሴቶች ድምፆች ልዩ ቦታ አላቸው ያሉት አባ ሚናኩ፥ በብዝሃነቷ የበለጸገች ቤተክርስቲያን አንድነት የተለየ ድምጽ ይሰጣሉ ካሉ በኋላ አክለው እንደተናገሩት፥ እነዚህ ድምፆች በሴቶች ምስክርነት የቤተክርስቲያኗን ቅድስና ያጠናክራሉ፥ ከዚህም በተጨማሪ ድምጾቹ “የቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊነት እና በተፈጥሮዋ ማግለልን ለማታውቀው ነገር ግን ክፍት እና ሁሉንም የምታቅፍ ቤተክርስቲያን ነው” በማለት አባ ሚናኩ በድጋሚ ተናግረዋል።

ስለዚህም ቤተክርስቲያኒቱ ከዚህ ውድ እና ልዩ አስተዋፅዖ ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ እንድትሆን በመንጋዋ ውስጥ ያሉ የሴቶችን ድምጽ በስልት ለማካተት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ጋናዊዋ የነገረ መለኮት ምሁር ሜርሲ አምባ ኦዱዮዬ የሴቶችን ድምጽ የማካተት ሂደት የሥነ መለኮት ሊቃውንት ሥራ ላይ ብቻ ሳይሆን "የቃል ሥነ መለኮት በሚጸልዩት ጸሎት ውስጥ፣ በሚያቀናብሩትንና በሚዘመሩትን መዝሙሮች ውስጥ፣ በሚሰሩት የጥበብ ሥራዎች ውስጥ በተገነባ ሰዎችንም” ማካተት እንዳለበት ጠቁመዋል።

‘ኪምፓ ቪታ’- የሲኖዳሳዊነት ማሳያ

የሳንታ ክላራ ዩኒቨርሲቲ (ካሊፎርኒያ) ፕረዚዳንት የሆኑት የኢየሱሳውያን ካህን አባ አጎንቺያንሜግ ኦሮባቶር እና በሥነ መለኮት የትምህርት ክፍል ውስጥ ፕሮፌሰር የሆኑት ሲስተር ሊዮካዲ ሉሾምቦ በጋራ ሆነው እ.አ.አ ከ1684-1706 በጥንታዊ ኮንጎ ውስጥ ትኖር የነበረችዋን የዶና ቢትሪዝ ኪምፓ ቪታ ምስል አቅርበዋል።

በጥንታዊ የኮንጎ መንግስት ውስጥ ነቢይ የነበረች እና ኢየሱስ እና ሌሎች የጥንት ክርስቲያኖች ከኮንጎ ሥርወ መንግስት የመጡ መሆናቸውን የሚያስተምረውን ‘አንቶኒያኒዝም’ የተባለ የራሷ የክርስቲያን እንቅስቃሴ መሪ የነበረችው ኪምፓ ቪታ፥ የሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያንን እና የእምነትን መፈልሰፍን የሚደግፍ የሥነ-መለኮታዊ ንግግር ቀዳሚ ሆኖ ብቅ አለ።

ስለዚህ የዛሬዎቹ የአፍሪካ ሴት የሥነ መለኮት ሊቃውንት በቤተክርስቲያኑ ሲኖዶሳዊ ጠረጴዛ ላይ ንግግር በማድረግ ሲኖዶሳዊ እና የቤተክርስቲያንን ራዕይ ያዳበሩ የረጅም ጊዜ የሴቶች ባህል አካል ናቸው።

እ.አ.አ. በ1684 በኮንጎ ግዛት የተወለደችው ኪምፓ በጊዜው በነበሩ ሚስዮናውያን ዶና ቢያትሪስ ተብላ የተጠመቀች ሲሆን፥ ህይወቷ በአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓውያን በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ቅኝ ግዛት በመቃወም ያደረገችው ትግል እንደትምሳሌት ይታይ ነበረ።

የኮንጎ ሥርወ መንግሥት መልሶ እንዲቋቋም እና ክርስትናን አፍሪካዊ ማድረግን ለሚደግፈው እንቅስቃሴዋ በሕይወት የተቃጠለችው ኪምፓ ፣ “ኮንጎሌሳዊው ጆአን ኦፍ አርክ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጣት ሴት ስትሆን፥ ለበለጠ ሁሉን አቀፍ እና የተዋቀረች ቤተክርስትያን እንዲመሰረት እና በተለያዩ የበላይነት አገዛዝ ዓይነቶች ላይ በማሰላሰል እና በማብራራት ባደረገችው አስተዋጽኦዋ ወሳኝ የአፍሪካ ሴት ተምሳሌት ነበረች ሲሉ አባ ኦሮባቶር እና ሲስተር ሉሾምቦ አብራርተዋል።

ሲኖዶሳዊነት - ሌላኛው የቤተ ክርስቲያን ህልውና መንገድ

ሲኖዶሳዊነት ወደ መንፈሳዊ ጉዞ ማዕከል ይመራናል፣ ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ እንዳለ የእምነት ማኅበረሰብ፣ በመንፈስ እየተመራች፣ በዘመናችን ያሉ የሃዋሪያዊ እና የማኅበራዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በአንክሮ እርስ በርስ መደማመጥና ማስተዋል እንድንችል ያደርገናል።

በሲኖዶሱ ጽሕፈት ቤት እንደ ኤክስፐርት እና አስተባባሪ በመሆን የተሳተፉት ሴኔጋላዊ መነኩሴ የሆኑት ሲስተር አኔ ቢትሪስ ፋዬ ጥቅምት 2015 ዓ.ም. በተካሄደው የሲኖዶስ ሂደት እና ጉባኤ ላይ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል።

የካስትሬስ እህቶች ጉባኤ አባል የሆኑት መነኩሴዋ፥ ወደ ማያቋርጥ እድገት የምትጓዘው ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ሁሉን አቀፍ እና አሳታፊ ባህሪ በአጽንዖት ገልጸዋል። በዚህ ጉዞ ውስጥ በሁሉም የቤተ ክህነት ሕይወት ውስጥ የሲኖዶሱን መንፈስ በመሳብ ሁሉም አማኝ የራሱንን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።

እንደ ሲስተር ፋዬ ገለጻ ከሲኖዶሱ ሂደት የተገኙት ትምህርቶች በማዳመጥ፣ በኅብረት እና የማያቋርጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመከተል ላይ ያለውን “ሌላኛው የቤተ ክርስቲያን ህልውና መንገድን" ያሳያሉ ብለዋል።

በዚህ ልዩ ገጽታ፣ የሲኖዶሱ ሂደት የሴቶች እና የአፍሪካ ሴት የሥነ መለኮት ምሁራን ድምጽ መግለጫ ምቹ ጊዜ ነው ተብሏል።
 

11 March 2024, 15:30