ፈልግ

PORTUGAL-VATICAN-POPE-RELIGION-WYD

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው"

ሥራ

የዩናይትድ ስቴትስ ሊቀ ጳጳሳት እንዲህ አሉ" “ወጣት ሰው መሆን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሥራ ዓለም መግቢያ ላይ መሆንን ያመለክታል” 'በምን ሥራ ላይ ተሰማርተሃል?' የሚለው ጥያቄ የማያቆም ጥያቄ ነው ምክንያቱም ሥራ መስራት ዋነኛ የሕይወታቸው አካል ነው” ወጣት የሕብረተሰብ ክፍል" በጣም የሚዋልል ነው ምክንያቱም ከአንዱ ሥራ ወደ ሌላኛው ሥራ እንዲያውም ደግሞ ከአንድ የሥራ መስክ ወደ ሌላ የሚዘዋወሩበት ነው” ሥራ" ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባቸው" ብሎም ደግሞ ምን መሥራት እንደሚችሉ ወይም ምን ያህል የመግዛት አቅም እንዳለቸው መወሰን ይችላል” የጊዜ ማሳለፊያቸውንም ጥራትና ብዛትም ይወስናል” ሥራ የወጣቱን ሕብረተሰብ ክፍል ማንነት እና ራስን የማወቅን ሁኔታ ላይ ተጽእኖ አለው" ጓደኝነቶችና ሌሎችም ግንኙነቶች የሚያድጉበት ነው ምክንያቱም ለብቻ የሚሆን ነገር አይደለም” ወጣት ወንዶችና ሴቶች ስለ ሥራ ሲናገሩ ትርጉም የሚሰጥና የሚያሟላ ነው ይላሉ” ሥራ ወጣት የሕብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎቶቻቸውን ያሟላል ከዚያም በላይ ደግሞ ራዕይና ሕልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ያደርጋቸዋል” ምንም እንኳን ሥራ ሕልሞቻቸውን እንዲጨብጡ ባይረዳቸውም" ራዕይን መኮትኮት መንከባከብ" በእውነትና ሕይወት ሰጪ በሆነ መንገድ መሥራት እና የእግዚአብሔርን ጥሪ ማድመጥን መቀጠል ግን አስፈላጊ ነው “”።

269. ወጣት የሕበረተሰብ ክፍሎችን የምጠይቀው በሌሎች እርዳታ ላይ ተሞርኩዘው ያለ አንዳች ሥራ እንዳይኖሩ ነው” ይህ ጥሩ አይደለም" ምክንያቱም “ሥራ አስፈላጊ" በዚህ ምድር የመኖር የሕይወት ትርጉም ክፍል" የእድገት መንገድ" ሰብአዊ እድገትና የግል ስኬት ነው” በዚህ ትርጉሙ" የተቸገሩትን በገንዘብ መርዳት ሁልጊዜም የጊዜው መፍትሄ መሆን አለበት”” ስለዚህ" “በቅዱስ ፍራንሲስ እንደምናገኘው አስደናቂ ማሰላሰል" የክርስትና መንፈሣዊ ልምድ" የበለጸገና የተመጣጠነ የሥራ ትርጉም አሳድጓል" እንደ ምሳሌ የተባረከውን ቻርልስን እና ተከታዮችን መጥቀሰ ይቻላል””።

ሲኖዱ በሥራ ዙሪያ" ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል" “የመገለል ችግር" የወጣቶች ሥራ አጥነት በተለይም በአንዳንድ አገሮች ከመጠን ያለፈ ደረጃ ላይ በመሆኑ ሊቸገሩ ይችላሉ” ችግረኛ ከማድረጉም በላይ" የሥራ እጦቱ ለማለም እና ተሰፋ ለማድረግ እንዳይችሉ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድርባቸዋል" ለሕብረተሰቡ እድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዳያደርጉ ያግዳቸዋል” በብዙ አገሮች" ይህ ሁኔታ አንዳንድ የወጣቱ ክፍል በቂ ክህሎት ያለመኖሩ እንደ ችግር ይቆጠራል ያም ደግሞ ምናልባት ከትምህርት እና ከአሠለጣጠኑ ችግር ሊሆን ይችላል” አብዛኛውን ጊዜ በቂ የሥራ ዋስትና ያለመኖር ወጣቱ በጉልበት በዝባዥ የኤኮኖሚ ፍላጎቶች ጋር ይተሳሰራል””።

ይህ በጣም የተወሳሰበ እና ጥንቃቄ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ የፖሊቲካው መስክ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል" በተለይም አሁን" ቴክኖሎጂው በአፋጣኝ እያደገ እና ያለውን የሰው ኃይል ክፍያ ለመቀነስ ብዙዎቹን ሥራዎች በመሣሪያ ለመተካት ጥድፊያ በሆነበት ሰዐት” በተጨማሪም ይህ የሕብረተሰቡም ዋነኛ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ወጣቱ ሥራ እንዲኖረው የሚፈልገው ለገንዘብ ብቻ አይደለም” ሥራ የሰው ልጅ ክብር መገለጫ" የእድገት ጎዳና እንዲሁም ወደ ማኅበራዊ ሕይወትም መቀላቀያ ነው” በኀላፊነት እና በፈጠራ ለማደግ የማያቋርጥ ማነቃቂያ ነው" ግለኝነትና ራስን መካብን የመከላከያ መንገድ ነው” በዚያውም ልክ" ችሎታን በማሳደግ ለእግዚአብሔር ክብር መስጫም ነው”።

ወጣት ልጆች ምን ዓይነት ሥራ መስራት እንዳለባቸው" ወይም ጉልበታቸውና ልዩ ችሎታቸው እንዴት ሥራ ላይ መዋል እንዳለበት" ሁልጊዜ የመወሰን እድል የላቸውም” ምክንያቱም" ከራሳቸው ግብ" ችሎታዎች" እና ምርጫዎች ጎን ለጎን" የሥራው ገበያ ተጨባጭ ሁኔታ አለ” እውነት ነው" ያለ ሥራ መኖር አትችሉም" አንዳንድ ጊዜም ያለውን ለመቀበል ትገደዳላችሁ" ዳሩ ግን ሕልሞቻችሁን እጅ ሰጥታችሁ አትተዉ" ጥሪያችሁን ፍጹም አትቅበሩ" ሽንፈትንም አትቀበሉ” ቢያንስ ቢያንስ ጥሪያችን ነው ብላችሁ ካሰባችሁት ነገር በከፊልም ቢሆን ኑሩት”።

እግዚአብሔር ለአንድ ነገር እየጠራን እንደሆነ ስናውቅ" ለዚህ ወይም ለዚያ እንደተፈጠርን - ለነርሲንግ ወይም ለአናጢነት ለምህንድስና ለመምህርነት ለሥነ ጥበብ ወይም ለሌላ ለማንኛውም ዓይነት ሥራ - ምርጥ የሆነ ችሎታችንን ያን ጊዜ ለመስዋዕትነት ለልግሥና መስጠት እንችላለን” ነገሮችን ለመሥራት ያህል ብቻ ሳይሆን ትርጉም ያለው ሥራ" ለሌሎች ከልባችን ልናደርግ እንደሚገባን አወቀን ከሆነ የምንሠራው - ያ ነው ለእነዚህ ሥራዎች ጥልቅ የሆነ እርካታ የሚያስገኘው” ከጥንታዊው የመክብብ መጽሐፍ ስናነብብ “ሰው በሥራው ደስ ከሚለው በቀር ሌላ መልካም ነገር እንደሌለው አየሁ”” (3:22) ።

ለልዩ ቅድስና ጥሪ

 

መንፈስ ቅዱስ ለክህነትና ለገዳማዊነት ጥሪዎችን እንደሚያነሣሣ የምናምን ከሆነ" “መረቦችን እንደገና አንድ ጊዜ” በፍጹም መተማመን በኢየሱስ ስም መጣል እንችላለን” እያንዳንዱን የወጣት ሕብረተሰብ ክፍል ለመከተል የፈለጉት መንገድ ይህ እንደሆነ መጠቅ ግድ ይለናል”።

አልፎ አልፎ" ይህንኑ ጉዳይ ከወጣቶች ጋር አነሣለሁ" ምላሽ የሚሰጡትም በቀልድ ዓይነት ነው - “አይ" ያ ለእኔ አይደለም!” ሆኖም ግን" ከጥቂት ዓመታት በኋላ" አንዳንዶቹ በሴሚናሪ ውስጥ ይገኛሉ” ጌታ ለቤተ ክርስትያን የገባውን እረኞችን የመስጠትን ቃል አያጥፍም" ምክንያቱም ያለ እነርሱ እሷ ተልዕኮዋን ማሳካት አትችልም” አንዳንድ ካህናት መልካም ምስክርነት የላቸውም የሚባለው እውነት ከሆነ" ያ ማለት ግን ጌታ ጥሪውን ያቆማል ማለት አይደለም” በተቃራኒው" ያበዛዋል ምክንያቱም የሚወዳትን ቤተ ክርስትያን መንከባከቡን ስለማያቆም”  ጥሪያችሁን ስትሰሙ" ራሳችሁን ለክህነት" የገዳማዊነት ሕይወት ወይም በሌሎች የቅድስና ጥሪዎች ለእግዚአብሔር እየሰጣችሁ መሆናችሁን እንዳትሰርዙ” ለምን? ከእግዚአብሔር የሆነ ጥሪን ስታውቁ እርግጠኞች ትሆናላችሁ" በዚያም ሙሉ ርካታን ታገኛላችሁ”።

በገሊላ እንዳደረገው ኢየሱስ በመኻከላችን እየተራመደ ነው” በጎዳናዎቻችን ላይ ይመላለሳል" በጸጥታም ቆም ብሎ ዐይኖቻችንን ይመለከታል” ጥሪው የሚስብና የሚያስደስት ነው” ዳሩ ግን አሁን ያለንበት ጊዜ ውጥረቱና ፈጣን እርምጃው አዘውትሮ ለተለያዩ ነገሮች ውርጂብኝ ስለሚያወርድብን ለውስጠኛው ሠላም - የኢየሱስን ወደ እኛ ዝም ብሎ መመልከትና ጥሪውን ለመስማትም ቦታ እንድናገኝ አያደርገንም” አሁን በሚያምር ሁኔታ የታሸጉ ስጦታዎች በመንገዳችሁ ላይ ይመጡላችኋል” የሚያስደስቱ ሊመስሉ ይችላሉ" ነገር ግን ውሎ እያደረ ባዶ የሚያደርጓችሁ" የሚያደክሟችሁና ብቸኛ የሚያደርጓችሁ ናቸው” ይህ እንዲሆንባችሁ አትፍቀዱ" ምክንያቱም የዚህ ዓለም አደገኛ እሽክርክሪት ትርጉም ወደሌለው መንገድ" ያለ ምንም አቅጣጫ" ያለ ምንም ግልጽ የሆነ እቅድ ስለሚመራችሁ" ጥረታችሁ ሁሉ መና ይሆናል” የተረጋጋውንና ጸጥ ያለውን" ለማሰላሰልና ለመጸለይ" በዙሪያችሁ ያለውን ዓለም በጠራ ሁኔታ እንድታዩ" ከዚያም ከኢየሱስ ጋር" በዚህ ምድር የናንተ የሆነውን ጥሪ እንድታውቁ ያንን መፈለግ ይሻላል”።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 270-279 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ ሮም።

 

 

 

 

08 March 2024, 13:07