ፈልግ

የያውንዴ ሃዋሪያዊ ግዛት ጳጳሳት ጉባኤ የያውንዴ ሃዋሪያዊ ግዛት ጳጳሳት ጉባኤ 

በካሜሩን የያሁንዴ ሃዋሪያዊ ግዛት ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያን እና ዲጂታል ዓለም ዙሪያ ተወያዩ

በካሜሩን የያውንዴ ሃዋሪያዊ ግዛት ጳጳሳት ጉባኤ የመጀመሪያው መደበኛ ዓመታዊ ስብሰባቸውን በቅርቡ ያካሄዱ ሲሆን፥ የምልአተ ጉባኤው መሪ ሃሳብም “ቤተ ክርስቲያን እና ዲጂታል ዓለም፡ በወንጌል አገልግሎት የሚያጋጥሙ ችግሮች እና ተግዳሮቶች” የሚል ነበር። ጉባኤው የተካሄደው በደቡብ ምዕራብ ካሜሩን በምትገኘውና የባህር ወደብ በሆነችው ክሪቢ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ሃዋሪያዊ ሥራ ማዕከል ውስጥ ነው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የያውንዴ ሃዋሪያዊ ግዛት አባል የሆኑት ጳጳሳት በውይይታቸው ወቅት፥ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባሕልን ከወንጌል ሥራ ጋር ማቀናጀት እንደሚያስፈልጋቸው የተስማሙ ሲሆን፥ “ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ለክርስትና ሕይወት በርካታ የክርስትና  መግቢያ በሮችን የሚከፍቱ የሃዋሪያዊ ሥራ እድሎችን ይሰጣሉ” ብለዋል።

ክርስትናን ዲጂታል ማድረግ እና ዲጂታልን ክርስቲያናዊ ማድረግ

የያሁንዴ ሃገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ዣን ምባርጋ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በማጣቀስ፥ “ቤተክርስቲያኒቷ በታሪክ ሂደት ውስጥ መሳተፍ ይገባታል፥ ከሁሉም በላይ ደግሞ የመሪነት ሚናዋን መጫወት አለባት” ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ከተናገሩ በኋላ፥ በመቀጠል “ከአሁን በኋላ በቁርጠኝነት መስራት ያለብን ክርስትናዊ ህይወትን ከዲጂታሉ ዓለም ጋር ማስማማት እና ዲጅታሉንም ክርስቲያናዊ ማድረግ ላይ ነው" ካሉ በኋላ፥ "እነዚህ ለእናንተ ለእግዚአብሔር ሰዎች የክርስቲያናዊ ህይወት መግቢያ በሮችን የሚከፍቱ የሃዋሪያዊ ሥራ መንገዶችን ናቸው፥ አምላክ የለሽነትን እውን ለማድረግ እና ለመመስረት ብቻ ወደሚፈልገው የዓለም ልብ ውስጥ ጸጋዎችን የሚያፈስ መሆን ይገባዋል” ብለዋል።

ለፈጠራ ሥራ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ

የያውንዴ ሊቀ ጳጳስ የክሪቢ ከተማን እንዲሁም የክሪቢ ሀገረ ስብከትን በችሎታ እና በፈጠራ ሥራ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ግንባር ቀደም በመሆናቸው አመስግነው፥ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት የክሪቢ ከተማ የምትሰጠውን ሰፊ የኢኮኖሚ ልማት እድሎች እንዲጠቀሙ በማሳሰብ፥ “ሆኖም ግን ይህች በባህር ዳርቻ የምትገኝ ዘመናዊ እና ብዙ ተስፋ ያላት ከተማ ብትሆንም፥ ከከተሞች መስፋፋት ጋር በተያያዙ ችግሮች ውስጥ ትገኛለች” ብለዋል።
 

25 March 2024, 19:21