ፈልግ

2024.01.07 Santa Messa nella festa del Battesimo di Gesu', con il Battesimo di alcuni neonati

ካቶሊኮች በሕፃንነታቸው የሚጠመቁት ለምንድነው?

አንዳንድ ወንጌላውያን ጥምቀት ሰው ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የመቀበሉ ምልክት የሆነ ምሳሌያዊ መታጠብ ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህ የእምነት መርህ መሠረት ነፍስ ያላወቀ ሕፃን ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ ለመቀበል ስለማይችል ጥምቀት ዋጋ የለሽ ነው፡፡ ሕፃናትን ማጥመቅ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ጥምቀት የግድ አስፈላጊ መሆኑን ኢየሱስ ይናገራል (ዮሐ 3፡5)፡፡

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሁላችንም ከአዳም ኃጢአት ጋር እንደተወለድን እና መጠመቅ እንደሚያስፈልገን ያስተምራል(ሮም 5፡18-19)፡፡ ኢየሱስ በበኩሉ ሕፃናት ወደ እርሱ ሲመጡ መከልከል ተገቢ አለመሆኑን በግልጽ ተናግሯል(ማር10፡14)፡፡ ሐዋርያት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሙሉ ቤተሰቦችን አጥምቀዋል(ሐ.ሥ 16፡15፣16፡33፣1ቆሮ 1፡16)፤ እንግዲህ መላ ቤተሰቡ ተጠመቀ ሲባል በዚያ ውስጥ ሕፃናት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሕፃናት እንዳይጠመቁ የሚያዝ አንድም ዓረፍተ-ነገር አይገኝም

 የቤተክርስቲያን አበው ሕፃናትን የማጥመቅ ሥርዐት በቀጥታ ከሐዋርያት የመጣ መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ የሕፃናት ነፍስ አለማወቅ (አለመብሰል፣ ምራቅ አለመዋጥ) በጥምቀት ከሚመሰረተው አዲሱ የኢየሱስ ቃልኪዳን ውጪ ሊያደርጋቸው አይችልም፡፡ በብሉይ ኪዳን ሕፃናት በግዝረት አማካኝነት የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ሕዝብ አባል ሲሆኑ እንመለከታለን፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ወላጆች ልጃቸውን በማስገረዝ ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ቃልኪዳን ይገባ ዘንድ ኃላፊነት እንደሚወስዱ እና ልጁ ነፍስ አውቆ በህፃንነቱ የገባውን ቃል-ኪዳን ደግሞ እስከሚያረጋግጥ በእግዚአብሔር ፊት በእርሱ ፈንታ የእምነት ምሥክሮች ሆነው እንደሚቀርቡ ሁሉ የአዲስ ኪዳን ወላጆችም እንዲሁ በልጆቻቸው ጥምቀት ላይ በእነርሱ ፈንታ የእምነት ምሥክርነት በመስጠት ወደ አዲስ ኪዳን ቃል ያስገቧቸዋል፡፡

29 February 2024, 16:47