ፈልግ

የክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ቅብዓተ ጵጵስና ሥርዓት ተከናወነ። የክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ቅብዓተ ጵጵስና ሥርዓት ተከናወነ።  

የክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ ቅብዓተ ጵጵስና ሥርዓት ተከናወነ።

የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምድብር ሀገረስብከት የክቡር አባ ተሾመ ፍቅሬ የሢመተ ኤጲስ ቆጶስ ሥርዓት ተካሄደ።

ሥነ-ሥርዓቱ በብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የተመራ ሲሆን በዚህ ታላቅ በዓል ብፁዕ ሊቀጳጳስ አንቷን ካሚሌሪ በኢትዮጵያ የቅድስት መንበር ተወካይ፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ከኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተገኙ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ብፁዓን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት፣ ክቡር አባ አንቶኒ ማኩንዴ የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጽ/ቤት ጠቅላይ ጸኃፊ፣ ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ መልከፄዲቅ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ እና የምዕራብ ጉራጌ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ክቡር ዶክተር ቄስ ዮናስ ይገዙ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነየሱስ ፕሬዝደንት፣ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋው የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ እና ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ ካቶሊካውያን ተሳትፈዋል።

የብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ሲመተ ጵጵስና
የብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ሲመተ ጵጵስና

በዕለቱም ብፁዕ ካርዲናል ባስተላለፉት ቃለ ምዕዳን ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞትዮስ እንዳለው በሚመችም በማይመችም ጊዜ ወንጌልን መስበክ እና ማሰራጨት አንዱ የጳጳስ ኃላፊነት መሆኑን አስታውሰው አዲስ የተቀቡት ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ይህንን እና ሌሎች በርካታ ኃላፊንቶች ይወጡ ዘንድ ከጎናቸው አብረው እንደሚቆሙ እና ለአገልግሎታቸው በጸሎት እንድሚያግዙ ቃል ገብተዋል።

የብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ሲመተ ጵጵስና
የብጹዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ሲመተ ጵጵስና

የበዓሉ መርሃግብር ከመስዋተ ቅዳሴ ቅዳሴ በመቀጠል የምስጋና ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ክቡር አባ ሀብቴ የእምድብር ሀገረስብከት ጽ/ቤት ኃላፊ የብፁዕ አቡነ ሙሴ የሃያ አመታት የተምሳሌት የአገልግሎት ዘመናትን አጠር ባለ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን ለተተኪው ጳጳስ አቡነ ሉቃስ አቀባበልም ሀገረስብከቱን በመወከል ገልፀዋል። በዕለቱ የተገኙ የክብር እንግዶችም የደስታ እና የአብሮነት መግለጫቸውን አሰተላልፈዋል።

ምንጭ፡ የኢትዮጲያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት

12 February 2024, 09:56