ፈልግ

2024.01.16   settimana preghiera unita' cristiani

የክርስቲያኖች መለያየት እግዚአብሔር እጅግ ያሳዝነዋል!

ከጥር 9-16/2016 ዓ. ም. ሲከበር በቆየው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል። ረቡዕ ጥር 16/2015 ዓ. ም. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመለሰበት ዓመታዊ በዓል የተከበረበት ዕለት እንደነበር ይታወቃል። እግዚአብሔር በክርስቲያኖች አለመግባባት እና ግፍ በተሞላው መስዋዕትነት እንደሚያዝን የሚታወቅ ስሆን ሁሉም ሰው ልቡ ተለውጦ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሚፈልገው ሙሉ አንድነት ለማደግ እንዲተባበር ጥሪ ማድረግ ያስፈልጋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ስሆን፣ ያደግሁት ግን በዚህ ከተማ ነው። የአባቶቻችንን ሕግ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ በሚገባ ተምሬአለሁ፤ ዛሬ እናንተ እንዲህ የምትቀኑለትን ያህል እኔም ለእግዚአብሔር እቀና ነበር። ይህን መንገድ የሚከተሉትንም እስከ ሞት ድረስ እያሳደድሁ፣ ወንዶችንም ሴቶችንም አስሬ ወደ ወህኒ እጥላቸው ነበር። ይህን ተግባሬን ሊቀ ካህናቱም ሆነ ሸንጎው ሁሉ ሊመሰክሩ ይችላሉ። ከእነርሱ ደብዳቤ ተቀብዬ ደማስቆ ወዳሉት ወንድሞቻቸው በመሄድ፣ እነዚህን ሰዎች አሳስሬ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥቼ ለማስቀጣት ወደዚያ እሄድ ነበር።

ይህንን ዝግጅት በድምጽ ለማዳመጥ ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ

“ስንጓዝም እኩለ ቀን ገደማ ወደ ደማስቆ እንደ ተቃረብሁ፣ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤ እኔም ምድር ላይ ወደቅሁ፤ ከዚያም፣ ‘ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።

“እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?’ አልሁት።

“እርሱም፣ ‘አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ በትክክል አልሰሙም።

“እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ምን ላድርግ?’ አልሁት።

“ጌታም፣ ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ሁሉ ይነግሩሃል’ አለኝ። ከብርሃኑም ጸዳል የተነሣ ዐይኔ ስለ ታወረ፣ ከእኔ ጋር የነበሩት እጄን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አደረሱኝ።

“ከዚያም ሐናንያ የተባለ ሰው ሊያየኝ ወደ እኔ መጣ፤ እርሱም ሕግን በጥንቃቄ የሚጠብቅና በዚያ በሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ዘንድ እጅግ የተከበረ ሰው ነበረ። በአጠገቤም ቆሞ፣ ‘ወንድም ሳውል ሆይ፤ ዐይኖችህ ይብሩልህ!’ አለኝ፤ እኔም በዚያችው ቅጽበት አየሁት።

“እርሱም ቀጥሎ እንዲህ አለ፤ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ፣ ጻድቁን እንድታይና ቃሉን ከአንደበቱ እንድትሰማ መርጦሃል፤ ስላየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆነዋለህና። ታዲያ፣ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥተህ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኀጢአትህም ታጠብ።’ (ሐዋ. 2፡3-16)

እግዚአብሔር አምላክ፣ በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት አማካይነት በሚሰጠን ምክር፥ በክርስቲያኖች መካከል በሚታዩ ግድ የለሽ አለመግባባቶች፣ ከእርሱ ይልቅ የራሳችንን ራዕይ ስናስቀድም እና ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች በሚያደርሱት የጦርነት እና የአመጽ መከራዎች ልቡ እንደሚያዝን እሙን ነው። ስለዚህ አመለካከታችንን ለውጠን፣ ሌሎችን በራስ ዕይታ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕይታ መመልከት አለብን፣ “በጸጋው ተለውጠን በጸሎት፣ በአገልግሎት እና በውይይት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደሚፈልገው ሙሉ አንድነት መድረስ እና ማደግ የምንችለው በጋራ በመሥራት ነው”።  ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመለሰበት መታሰቢያ ዕለት በተካሄደው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት ማጠቃለያ ላይ እኛም የክርስቶስን ስም የተላበስን ክርስቲያን ተብለን የምንጠራ ሁላችን፣ በሕብረት ሆነን የክርስቶስን የፍቅር ምስጢር ልንሰብክ እና በሕይወታችን ልንኖር ይገባል። 

በሮም የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አጽም በሚገኝበት በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ውስጥ በቀረበው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች የሚገኙ ሲሆን፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ለዓመታዊው የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎት ሳምንት መሪ ቃል እንዲሆን የተመረጠው “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህና በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ” (ሉቃስ 10፡27) የሚለው እንደ ነበረም ይታወቃል።  እስቲ እኛ ራሳችንን ክርስቲያን ብለን የምንጠራ ሰዎች በእውነት እግዚአብሔርን እና ባልንጀራችንን እንደምንወድ ለማወቅ ራሳችንን እንመርምር።

ለለውጥ የቀረበ ምክር

ከትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ እንደምናነበው፣ እግዚአብሔር የሚፈልገው ወደ መቅደሱ በስሙ የሚቀርበውን ዕጣን እና ቍርባን ብቻ ሳይሆን፣ የተገፉት እንዲረዱ፣ ለድሆች ፍትሕ እንዲሰጥ እና ለመበለቲቱ እንዲሟገቱላት የሚጠይቅ መሆኑ እናስታውስ። በነቢዩ ዘመን፣ ባለጠጎችና ብዙ መስዋዕቶችን ያቀረቡ የነበሩ በእግዚአብሔር የተባረኩ ተደርገው ሲቆጠሩ ድሆች ግን ይናቁ እንደ ነበር፣  እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ ሁኔታ በዘመናችንም በገሃድ የሚታይ ነገር ነው።

ባለመግባባታችን እግዚአብሔር አዝኗል!

“ነገር ግን ይህ ሁሉ እግዚአብሔርን አለመረዳት ይገልጻል” ኢየሱስ ክርስቶስ ድሆች ብፁዓን እንደሆኑ ሲያውጅ እና በመጨረሻው የፍርድ ቀን ምሳሌም እራሱን ከተራቡት፣ ከተጠሙት፣ ከመጻተኞች፣ ከድሆች፣ ከታመሙት እና ከእስረኞች ጋር እንደሚያስቀምጥ ኢየሱስ የገለጸ ሲሆን “የእግዚአብሔር ቁጣ የመጀመሪያው ምክንያት፣ የእርሱን ምሳሌነት ባለመከተላችን ነው”።

ራሳችንን ታማኞች ነን ብለን ስንጠራ፣ ራእያችንን ከእርሱ ራእይ ስናስቀድም፣ ከሰማዩ ይልቅ ምድራዊ ፍርድን ስንከተል፣ በውጫዊ ገጽታ ብቻ ስንረካ እና እርሱ ለሚጨነቅላቸው ሰዎች ግድ የለሾች ስንሆን፣ እግዚአብሔርም በዚህ የተነሳ የሚያዝን መሆኑን ሁላችንም ልንረዳ ይገባል።

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሆነው ሰው ላይ የሚፈጸመው የረከሰ ዓመፅ

“እግዚአብሔር የሚከፋበት ሁለተኛው እና ከባዱ ምክንያት፣ ‘የረከሰ ዓመፅ’ ነው” ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ስለ "ወንጀል እና ስለ ረከሰ በዓል፣ እንዲሁም ደምን ስለምያፈሱ እጆች" እንደሚናገር አውቀን፣ ሰው ሠራሽ ለሆነው ቤተ መቅደስ ክብር እየተሰጠው ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሆነው ሰው ላይ በሚፈጸም ግፍ ምክንያት እግዚአብሔር መቆጣቱን አይቀሬ ነው። "ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች በሚያካሂዱት ጦርነቶች እና የዓመፅ ድርጊቶች እግዚአብሔር ምን ያህል እንደሚሰቃይ መገመት እንችላለን"።

እምነት፣ የብሔርተኝነት አመጽ እና ጥላቻን አይፈቅድም

የንጉሡን ጭካኔ በመቃወም በጾም ወቅት ሥጋ ለማቅረብ ወደ ንጉሡ ዘንድ የሄደውን ቅዱስ ሰው እናስታውስ፣ ንጉሡ በሃይማኖት አክባሪነቱ የተነስ ይህንን ሲመለከት ቁጣውን በመግለጽ ሥጋውን ለመብላት አሻፈረኝ ባለ ጊዜ ቅዱሱ ሰው፣ ይህ የእግዚአብሔርን ልጆች ለመግደል ያላቅማማ፣ ነገር ግን የእንስሳትን ሥጋ ለመብላት ለምን ተቸገረ? ብሎ ይጠይቃል።

ምንም እንኳን "መንፈሳዊነት እና የሥነ-መለኮት ዕድገት" በቂ ምክር ቢሰጥም፣ አንዳንድ ሰዎች ከሚከተሉት እምነት ፍቃድ እንደተሰጣቸው እና ብርታትን ያገኙ ይመስል፣ ጨካኝ ብሔርተኝነትን ለሚደግፉ፣ የጥላቻ አስተሳሰቦችን ለሚያራምዱ፣ ንቀትን አልፎ ተርፎም እንግልትን ለሚመርጡት በሙሉ፥ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” የሚለውን ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ልናነብ ይገባናል፣ ከእዚህ ዓይነት ድርጊቶቻችን እንድንመለስ ሊመክረን ይችላል፣ “የሐዋርያው ​​ጳውሎስን ምሳሌ በመከተል በእኛ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ከንቱ እንዳይሆን ከፈለግን ጦርነትን፣ ዓመፅን እና ኢ-ፍትሐዊነትን በሁሉም ሥፍራ መቃወም አለብን”።

ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ከክፉ ወደ በጎነት መሸጋገር ያስፈልጋል!

በትንቢተ ኢሳ. ምዕ. 1:17 “መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትህን እሹ. . .” ተብሎ የተጻፈውን ስናነብ የክርስቲያኖች ሕብረት የጸሎተ ሳምንት ማብቂያ ላይ ባለፈው አመት 2015 ዓ.ም ይህ ጥቅስ ከዚህ ቀደም በሰሜን አሜሪካ ነባር ተወላጆች እና በአፍሮ አሜሪካውያን ላይ የተፈፀመውን ኢ-ፍትሃዊነት ለማስታወስ ከሚኒሶታ ግዛት በመጡ የምዕመናን ቡድን መመረጡን እናስታውሳለን፣ ንቀት እና ዘረኝነት ላለበት፣  አለመግባባት ለሚታይበት እና ክፉ ዓመፅ ለሚካሄድበት ለዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ቃል፥ “መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትህን እሹ፤...” (ኢሳ 1፡17) በማለት እንደሚመክረን አውቀን  እነዚህን መጥፎ ተግባራት ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ከክፋት ወደ በጎነት መሸጋገር ያስፈልጋል! 

ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን በኅብረት ለወጥን ማምጣት ይቻላል!

“ስህተቶችን ከመረመርናቸው በኋላ ምሕረትን እንድናገኝ እግዚአብሔር እንደሚፈልግ ከኃጢአታችን ሊያነጻን የሚችለው እርሱ ብቻ እንደሆነ እና ይህን ለማድረግ ቃል መግባቱን እናስታውስ፣ "ለእግዚአብሔር ካለን ቸልተኝነት እና በውስጣችን ካለን ዓመፅ በኃይላችን መላቀቅ አንችልም" እርሱ ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ከመጥፎ መንገዳችን እንድመልሰን ልንጸልይ ይገባል። የሐዋርያው ​​ጳውሎስ ሕይወት እንደሚያስታውሰን መንፈሳዊ ለውጥ የማምጣት ፍላጎት ምንጭ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሆነ፣ ብቻችንን ምንም ማድረግ እንደማንችል፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር በመታመን በኅብረት ከቆምን ሁሉን ነገር ማድረግ እንደሚቻል እና እግዚአብሔርም የእርሱ ተከታዮች እንዲለወጡ ሁሌም እንደሚጠይቅ ልብ ልንል ይገባል።

መለወጥ የሚለው ቃል ብዙ የተደጋገመ እና በሚገባ ለመረዳት ቀላል እንዳልሆነ ፣ መለወጥ ለሕዝቦች የሚቀርብ፣ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ ትርጉም ያለበት ጥያቄ መሆኑን፣ ክርስቲያኖች ወደ ሕብረት የሚያደርጉት የለውጥ ጉዞ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሚያስፈልገው እና ይህም የሚሆነው የእርሱን ምሕረት ስንገነዘብ፣ ሁላችንም በሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ላይ የምንመካ መሆናችንን ስንገነዘብ፣ በእሱ ዕርዳታ በእውነት ሕብረት መፍጠር እንችላለን።

 

 

25 January 2024, 15:45