ፈልግ

World Youth Day in Lisbon

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው" ዋነኛ የእርምጃ አቅጣጫዎች

የወጣት አገልግሎት ሁለት ዋና ዋና የእርምጃ አቅጣጫዎችን ያካትታል በማለት አጽንኦት መስጠት እፈልጋለሁ” አንደኛው" ወጣቶችን ወደ ጌታ የምንማርክበት ስብከተ ወንጌል ነው” ሁለተኛው ደግሞ" እድገት" እነዚያ ወንጌሉ የደረሳቸውን እንዲያድጉበት የምንረዳበት መንገድ ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ

ስብከተ ወንጌልን በተመለከተ" አንድ ላይ ለመሰባሰብ ወጣቶች ራሳቸው ማራኪ የሆኑ መንገዶች አሏቸው ብዬ እተማመናለሁ” ስፖርታዊ ውድድሮችን" ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም" ቴክስት በመለዋወጥ" በመዝሙሮች" ቪዲዮዎች እና በሌሎችም መንገዶች ዝግጅቶችን ማስተባበር ይችላሉ” ሌሎች ወጣቶች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ወንጌል እንዲደርሳቸው ተግተው እንዲሠሩ ማበረታታት እና ነጻነት መስጠት ብቻ ነው የሚያስፈልገው” በወጣቶች የሱባኤ ጊዜም ሆነ በቡና ቤት ውስጥ ንግግር" የትምህርት ቤት እረፍቶች" አልያም በእግዚአብሔር የረቀቁ ዘዴዎች" መልእክቱ መጀመሪያ ሲደርስ ጥልቅ የሆነ የእምነት ተሞክሮ ማነቃቃት ይችላል” ዋነኛው ነገር" እያንዳንዱ ወጣት ያንን የመልእክት ዘር በመልካም መሬት - በሌላኛው ወጣት ልብ ውስጥ መዝራቱ ነው”::

በዚህ በስብከተ ወንጌል" ከምንም በላይ መጠቀም ያለብን የቅርበት ቋንቋ" የልግሥና ቋንቋ ሲሆን ልብን የሚነካ የትስስር ፍቅር ሕይወትን ይነካል" ተስፋዎችን እና መሻቶችን ያነቃል” ወጣቶች ሊቀርቧቸው የሚገባው በፍቅር ሰዋሰው እንጂ በመስበክ አይደለም” ወጣቶች የሚገባቸው ቋንቋ የሚነገረው ሕይወትን በሚያንጸባርቁ" ከእነርሱ እና ለእነርሱ ባሉላቸው" እንዲሁም ውሱንነትና ድከሞች ቢኖሯቸውም እንኳን እምነታቸውን በሐቅ ለመኖር የሚሞክሩት ናቸው” በተጨማሪም ደግሞ ይበልጥ አሳብ ልንሰጥ የሚገባን በዛሬው ወጣት ቋንቋ" ኬሪግማ (እንደ መጀመሪያዋ ቤተክርስትያን ወንጌልን መስበክ) ላይ ሕይወት መዝራት ነው”።

እድገትን በተመለከተ" አንድ ዋነኛ ነጥብ ማንሣት እፈልጋለሁ” በአንዳንድ ስፍራዎች" ወጣቶች የእግዚአብሔርና" ልባቸውን የነካውን ኢየሱስን እንዲገናኙ እገዛ ይደረግላቸዋል” ነገር ግን የሚደረግላቸው ክትትል" የኅንጸት ስብሰባዎች እነሱም ስለ አስተምህሮ እና ሥነ ምግባር ጉዳዮች" የዚህ ዘመን ክፋቶች" ቤተ ክርስትያን" ማኅበራዊ አስተምሮዋ" ቅድስና" ጋብቻ" የወሊድ መቆጣጠሪያ" እና የመሳሰሉት የሚነገሩበት ነው” በውጤቱም ብዙ ወጣቶች ስልችት ይላቸዋል" ያ ከክርስቶስ ጋር የመገናኘት እሳት እና እርሱን የመከተሉ ደስታም ይከስማል; አብዛኛዎቹ ተስፋ ይቆርጣሉ ሌሎች ደግሞ አሉታዊ አመለካከት ይፈጠርባቸዋል” ይልቁንም የአስተምህሮ ክምር ከማብዛት" የክርስትናን ሕይወት የሚያቆየውን ታላቅ ተሞክሮ ለማነቃቃት እንሞክር” ሮማኖ ጋርዲኒ አንዳለው" “ታላቅ ፍቅርን ስንለማመድ .... ሌላው ነገር ሁሉ የዚያ አካል ይሆናል””።

ማናቸውም ትምህርታዊ ፕሮጀክት አልያም ወጣቶች የሚያድጉበት ጎዳና የክርስትና አስተምህሮ እና ሥነ ምግባራዊነትን በእርግጠኝነት ማካተት ይኖርበታል” ሁለት ዋነኛ ግቦችም ሊኖሩት ይገባል” አንደኛው" በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከእግዚአብሔር ጋር የመገናኘት መሠረታዊ ልምምድ የኬሪግማ እድገት” ሌላኛው ደግሞ የወንድማማችነት ፍቅር" የማኅበራዊ ሕይወት እና አገልግሎት ነው” ።

የወንጌል ደስታ በተሰኘው ጽሑፌ ትኩረት የሰጠሁበት አንድ ነገር ይህ ነው" እዚህም መደገም የሚገባው ነገር ነው ብዬ አስባለሁ” “በወጣት አገልግሎት" ኬሪግማ ይበልጥ ጠንካራ ኅንጸት መንገድ ከፋች ነው ብሎ መገመት ትልቅ ስሕተት ነው” ከመጀመሪያው አዋጅ የሚበልጥ ምንም ጠንካራ" ጥልቅ የሆነ" ደህንነቱ የተጠበቀ" ትርጉም ያለው" ጥበብ የተሞላ ነገር የለም” ሁሉም የክርስትና ኅንጸት" ይበልጥ ወደ ኬሪግማ ውስጥ መግባትን ያካትታል””።

የወጣት አገልግሎትም የእግዚአብሔርንና የሕያው ክርስቶስን ፍቅር የግል ተሞክሮአችንን የምናድስበትና ጥልቀት እንዲኖረው የምናደርግበትን ሁኔታ ማመቻቸትን ያካትታል” ይህንን ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች አሉ - ምስክርነቶች" መዝሙሮች" አምልኮ" በቅዱስ ቃሉ ንባብ" ጥበብ በተሞላው የማኅባራዊ ኔትወርኮችም እንኳን ሳይቀር ማድረግ ይቻላል” ዳሩ ግን ይህ ጌታን የማግኘት ሁኔታ በ“ማሳመኛ” ዓይነት ነገር መተካት የለበትም”

በሌላ በኩል ደግሞ" ማንኛውም ዓይነት የወጣት አገልግሎት በግልጽ ሊያካትት የሚገባው የተለያዩ መንገዶችንና ግብአቶችን" ወጣቶች በወንድማማችነት እንዲያድጉ የሚያስችል" እንደ ወንድምና እህት ሆነው እንዲኖሩ" እንዲደጋገፉ" ማኅበር እንዲመሠርቱ" አንዱ ሌላውን እንዲያገለግል" ድኾችን እንዲያቀርቡ የሚያደርግ ሊሆን ይገባዋል” እርስ በእርስ መዋደድ “አዲሱ ትእዛዝ” ከሆነ (ዮሐ 13:34)"“የሕግ ፍጻሜ ነው” (ሮሜ 13:10) ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ነውና በሁሉም የወጣት ኅንጸት ፕሮጀክትና እድገት ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ ሊኖረው ይገባል”።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 209-216 ላይ የተወሰደ።

 

12 January 2024, 16:30