ፈልግ

እስራኤል ኅዳር 29 በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ ውስጥ በሚገኝ መዋዕለህፃናት ባደረሰችው ጥቃት አንዲት ሴት አንዳንድ መጽሃፎችን ለማዳን እየሞከረች እስራኤል ኅዳር 29 በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ራፋህ ውስጥ በሚገኝ መዋዕለህፃናት ባደረሰችው ጥቃት አንዲት ሴት አንዳንድ መጽሃፎችን ለማዳን እየሞከረች   (AFP or licensors)

ዮርዳኖስ ጋዛ ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት የገናን በዓል እንደወትሮው እንደማታከብር ታወቀ

በዮርዳኖስ ያሉ ክርስቲያኖች ለፍልስጤም ህዝቦች አጋርነታቸውን ለማሳየት ሲሉ ቀዝቀዝ ያለ የገና በዓልን እንደሚያከብሩ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በዮርዳኖስ ግዛተ መንግሥት የዚህ ዓመት የገና በዓል አከባበር የተለየ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን፥ ክርስቲያኖች የጌታን መወለድ ሲያከብሩ በፊት በተለያዩ መብራቶች ትደምቅ የነበረቿ ከተማ ዘንድሮ እንደማይኖር ተነግሯል።

በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የክርስቲያን መሪዎች ጥያቄ መሰረት፥ ከድንበር ባሻገር በጦርነት ከሚሰቃየው የፍልስጤም ህዝብ ጋር አብሮነታቸውን ለማሳየት ወትሮ በከፍተኛ ድምቀት ይከበር የነበረው የገና በዓል ዘንድሮ በፀጥታ ውስጥ ሆነው እንደሚያከብሩ ታውቋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እስራኤል መስከረም 27 ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከ18,000 በላይ ሰዎች በተገደሉበት የጋዛ ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ደጋግመው መጠየቃቸው ይታወቃል።

ባዛሮች፣ ሙዚቃዊ ትዕይንቶች እና የስጦታ ሥርጭትን ጨምሮ የተለያዩ ፌስቲቫሎችን የመሰረዝ ውሳኔ የተላለፈው የዮርዳኖስ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ሲሆን፥ ማኅበረሰቡ የገና በዓላቸውን በጸሎት እና በሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ብቻ እንዲገድቡ እንዲሁም በጦርነቱ ለተጎዱት ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

እስካሁን ከ10,000 የሚበልጡ ሕፃናት በጦርነቱ ምክንያት እንደሞቱም ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህም በላይ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ምንም ዓይነት ደህንነቱ የተጠበቀ መሄጃ ቦታ በሌለበት እና ምግብም ሆነ ውሃ በሌለበት ሁኔታ እንደተፈናቀሉ፥ ይህንንም ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ እና ሰብአዊ እልቂት ሲሉ ታዛቢዎች ይገልጹታል።

የቤተልሔም ከተማም በገና በዓል ወቅት ደብዛዛ ሆና እንደምታሳልፍ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት ባህላዊ ቦታ ላይ ምንም ዓይነት የገና ዛፍ እንደማይኖር የተነገረ ሲሆን፥ በቅድስት ሀገር የሚገኝ የካቶሊክ ገዳም አለቃ የሆኑት አባ ፍራንቸስኮ ፓቶን ይህን አስመልክተው እንደተናገሩት “በዓሉን በጥሞና እናከብራለን” ብለዋል።

ዓለም በግፍ ለተገደሉት እያለቀሰ በሚገኝበት በዚህ ዓመት ምንም አይነት ክብረ በዓል አይኖርም ተብሏል።
 

12 December 2023, 14:45