ፈልግ

ስድስቱ የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ከፕሮጄክቱ ዳይሬክተር ፓኦሎ ሩፊኒ እና ከፕሮጄክት አስተባባሪዋ ከሲልቪያ ግሬቺ ጋር ስድስቱ የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ከፕሮጄክቱ ዳይሬክተር ፓኦሎ ሩፊኒ እና ከፕሮጄክት አስተባባሪዋ ከሲልቪያ ግሬቺ ጋር 

ገዳማዊያንን ያቀፈ ‘የሚዲያ ሃዋሪያነት’ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እየተስፋፋ ነው ተባለ።

መረጃ በተለያዩ መድረኮች በሚሰራጭበት በአሁኑ የዲጂታል ዘመን ፥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማዊያን በየአካባቢያቸው ካሉ ሰዎች ጋር ለመገናኘት የመገናኛ ብዙኃን ዓለም ላይ መሳተፍ እና መገኘት አለባቸው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ዓለማችን በመረጃ በተጨናነቀበት እና የማያቋርጥ ማህበራዊ ትስስር ባለበት በዚህ ዘመን ፥ ገዳማዊያኑ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ትርጉም ያለው የመግባቢያ ፍላጎት ለማሟላት እየሰሩ እንደሆነ ተመላክቷል።
የሚዲያ ሐዋርያነትን የተቀበሉት ገዳማዊያኑ ከአሁን በኋላ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተማር ወይም በሆስፒታል ውስጥ መሥራት ላይ ብቻ ሳይወሰኑ ጎን ለጎንም በሚዲያ ሃዋሪያነት ላይም መሳተፍ እንዳለባቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተረድተዋል።
እንደሚታወቀው የመገናኛ ብዙሃን የህዝብ አስተያየትን በማቀናጀት እና በህብረተሰቡ ላይ ተፅእኖ በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። ለረጅም ጊዜያት የወንጌል ተልእኮ የካህናት እና የሃይማኖት አባቶች ተቀዳሚ ሚና እንደሆነ ተደርጎ ይታይ ነበር። እንዳጋጣሚ የጌታን ትንሳኤ መልእክት ቀድመው የተቀበሉት ገዳማዊያን ሴቶች ረዳት ተግባራትን ማለትም ካህናት ወንጌልን እንዲሰብኩ መርዳት፣ ትምህርተ ክርስቲያንንን ማስተማር እና የመሳሰሉትን ብቻ እንዲከውኑ ተደርገው ነበር። በርግጥ እነዚህም ተግባራት የተቀደሱ እንደሆኑ አይዘነጋም።

ግንኙነት እንደ ትክክለኛ ሐዋርያነት

የወንጌል እሴቶችን ለማስፋፋት እና በእግዚአብሔር ህዝብ እና በሰፊው ማህበረሰብ መካከል ውይይትን ለማዳበር በሚደረገው ጥረት ገዳማዊያኑ እህቶች ሚዲያዎች በሁሉም መስኮች ውስጥ ገብተው መሰራጨት እንደሚችሉ ተገንዝበዋል። ገዳማዊያኑ እህቶች በደንብ ወንጌልን ለመስበክ በመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም እና ስርጭት ረገድ ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል። "ይህም በጉባኤዎቻችን ውስጥ እርስ በራሳችን እንድንግባባ እና መልዕክታችንን ለውጭው ዓለም እንድናስተላልፍ ይረዳናል" ብለዋል በፕሮጄክቱ ውስጥ የሚሳተፉት ሲስተር ቺዳኑ ጆርጂኒያ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የመገናኛ ዘዴ ወይም የመገናኛ ብዙኃን ሃዋሪያነት የተለያዩ ልማዳዊ የህትመት እና የስርጭት መድረኮችን እና አዳዲስ እንደ ማህበራዊ እና ዲጂታል ሚዲያዎች በመጠቀም እና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሃይማኖት ትምህርቶች እና ሌሎች እሴቶችን እንዲሁም ወንጌልን ለማሰራጨት ያገለግላሉ።
የመገናኛ ብዙሃን ሐዋሪያነት ሴት ገዳማዊያኑን ከወንዶች በተለየ መልኩ እምነታቸውን ወይም ሃይማኖታቸውን እንዲገልጹ ያስችላቸዋል። አልፎ ተርፎም በሰፊው ታዳሚ በኩል በህብረተሰቡ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ልዩ እድል ይሰጣቸዋል።
ባህላዊ ሚዲያዎች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የዛሬው አርዮስፋጎስ (ጥንት የግሪክ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የሚሰበሰብበት በግሪክ አቴንስ ከተማ ከአክሮፖሊስ በስተሰሜን ምዕራብ የሚገኝ ታዋቂ የድንጋይ ክምር ነው። የእንግሊዘኛ ስሙም ‘Hill of Ares’ የሚባል ሲሆን ፥ “የኤረስ ኮረብታ” በሚለው እንተረጉማለን)
ናቸው ፥ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተፃፈው ‘ሪዴምቶሪስ ሚሲዮ’ (Redemtoris Missio ቁ. 37) መልዕክታቸው “እህቶች ወደ መድረኩ መውጣት አለባቸው” ይላል።
ስለዚህ በእግዚያብሄር መገኛ በሆነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለው ልምምድ ለመጀመር ምን የተሻለ ቦታ አለ?ቤተክርስቲያን ቀደም ሲል ብዙ ብቁ ተቋማት እና በማህበራዊ ግንኙነት የሰለጠኑ ሰዎች አሏት።

የጊዜ ምልክቶች እና የጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት

የቫቲካን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፋውንዴሽን ከሂልተን ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የዘመኑ ህብረተሰብ ውስጥ ውጤታማ ግንኙነት እንዲኖር ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ እና የጊዜውን ፍላጎት ለማሟላት የገዳማዊያኑን የሚዲያ ክህሎትን ለማሳደግ ተገቢ ሆኖ ተግኝቷል። በዚህም ምክንያት እና ‘በጴንጤቆስጤ ፕሮጀክት’ አማካኝነት የሚዲያ ክህሎቶችን እንዲሁም ማንበብ እና መፃፍን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።
በዚህ አነሳሽነት የሀይማኖት ማኅበረ ቅዱሳን አባሎቻቸው በመገናኛ ብዙኃን እና በጋዜጠኝነት ዘርፍ በተለይ ለገዳማዊያን ተብሎ በተዘጋጀ የኦንላይን አጫጭር ኮርሶች የማህበራዊ ግንኙነት ትምህርት እንዲከታተሉ ወይም ገዳማዊያኑን ወደ ቫቲካን ኒውስ/ቫቲካን ራዲዮ ዋና መሥሪያ ቤት ለ3 ወራት የልምምድ ጊዜ በመላክ እንዲረዱ ያበረታታል። እነዚህን አዳዲስ ክህሎቶችን በልምምድ ጊዜው በማካበት እነዚህ ገዳማዊያን እህቶች እምነታቸውን በብቃት ለማስተላለፍ የታሪክ አተራረክ እና የጋዜጠኝነት ጥበብን ማዳበር ይጀምራሉ።

የሚዲያ ስልጠና አስፈላጊነት በገዳማዊያን ምስረታ ውስጥ

የቫቲካን የግንኙነት ጽ/ቤት ‘ዲካስተሪ’ ከሚሰራው ሥራ በተጨማሪ ወጣት ገዳማዊያት ተጨማሪ ምስረታ እና ስልጠና ማግኘት አለባቸው። በእርግጥ አንዳንድ የገዳማዊያን ጉባኤዎች የምሥረታ ሂደታቸው ውስጥ የሚዲያ ትምህርቶችን ማካተታቸውን ማወቁ አስደሳች ነገር ነው። ያም ሆነ ይህ ዛሬ ወደ ሃይማኖታዊ ሕይወት የሚገቡት አብዛኞቹ ወጣቶች እንደ ‘ሲስተር’ ሆነው ራሳቸውን ለመመስረት በሚያቀርቡበት ወቅት የመገናኛ ብዙኃንን ጥቅም ተረድተው ነው የሚመጡት። ሃይማኖታዊ ሕይወት እነዚህን ተሰጥኦዎች እንዲያንጸባርቁ፣ እንዲቀርጿቸው እና የወንጌል እሴቶችን በእጩዎች ውስጥ እንዲሞሉ ማድረግ አለበት።

ትረካውን መለወጥ

“በትምህርት ቤቶች፣ በጤናው ዘርፍ እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ሐዋሪያትነታቸው የተነሳ ገዳማዊያኑ ብዙውን ጊዜ በህብረተሰቡ ውስጥ እየሆነ ባለው ነገር ግንባር ቀደም ናቸው። ገዳማዊያን እህቶች ከዚህ በፊት በተግባር ያጋጠሙንን ነገሮች በጽሁፍ በማዘጋጀት የመገናኛ ብዙሃን ሐዋሪያት የወንጌል ተልእኮአችን አካል መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን” ይላሉ ሲስተር ቺዳሉ ጆርጂኒያ።
ገዳማዊያኑ የታሪክ አተራረክ ችሎታቸውን በብዙ የመማሪያ ክፍሎች እና የትምህርተ ክርስቲያን ክፍሎች ከፍ አድርገዋል። በሀሰት ዜናዎች እና በተሳሳቱ መረጃዎች በተሞላው ዓለም ውስጥ እያደገ ለመጣው ትክክለኛ እና አስተማማኝ መረጃ ፍላጎት የገዳማዊያኑ የመገናኛ ብዙኃን ሐዋሪያነት ጥሩ ምላሽ ነው።
የሚዲያ ሐዋርያነት እንደሌላው ጥሪ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ገዳማዊያት የሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎች የእግዚአብሔርን እውነት ውበት እንዲያካፍሉ ተጠርተዋል ፥ የውሸት ዜናዎችን ከእውነት በመለየት እና በፍቅር እና በቤዛነት መልእክቶች እንደሚያሰራጩ ተስፋ እናደርጋለን።
በመጨረሻም የሚዲያ ሐዋርያነት የእግዚአብሔርን እውነት መስበክ ሲሆን ይህንንም ለሌሎች ማስተላለፍ ነው።

ሃይማኖታችንን ወደ ህዝብ ውይይት ማምጣት

ሲጠቃለል የገዳማዊያን ሴቶች በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ ያላቸው ሚና መረጃን ከማስተላለፍ የዘለለ ነው።
"የማህበረሰብ ህይወት የምንኖር ሰዎች እንደመሆናችን መጠን በዓለም ላይ በአጠቃላይ የማህበረሰብ እና የአብሮነት ስሜትን የማሳደግ ልዩ እድል አለን። የመገናኛ ብዙኃን ሐዋሪያነት የእምነታችን እና የሕይወታችን እሴቶች በሕዝብ ውይይት ውስጥ እንዲገኙ በማድረግ አዎንታዊ ለውጥ እንድናመጣ ያስችለናል" ይላሉ ሲስተር ቺዳሉ ጆርጂኒያ።
 

18 September 2023, 15:41