ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ሼቭቹክ ሲኖዶሱ ከተጠናቀቀ በኋላ  ጋዜጣዊ መግለጫው ሲሰጡ ሊቀ ጳጳስ ሼቭቹክ ሲኖዶሱ ከተጠናቀቀ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫው ሲሰጡ 

የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሮም ከተማ መጠናቀቁ ተነገረ።

የዩክሬን የግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶሱን ጉባኤ ስታጠናቅቅ ሜጀር ሊቀ ጳጳስ ስቪያቶስላቭ ሼቭቹክ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንደተናገሩት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለዩክሬን ሕዝብ ላሳዩት ቅርበት እና ቤተክርስቲያኒቱ በጦርነት ለተጎዱ ሰዎች የምታደርገውን የሃዋሪያዊ ሥራ እርዳታ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የዩክሬን የግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት በሮም ሲያካሂዱት የቆየውን ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያቸውን እና ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጋርም ሲያደርጉት የነበረውን ውይይት ትናንት መስከረም 3 2016 ዓ.ም. አጠናቀዋል።
የዩክሬን ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ሲኖዶስ በዩክሬን ውስጥ ሩሲያ በምታካሂደው ጦርነት ለተጎዱ ሰዎች ቤተክርስቲያኒቱ በምትሠራው ሃዋሪያዊ ሥራ ላይ ትኩረት አድርጓል።
ከጋዜጣዊ መግለጫው ጎን ለጎን የዩክሬን የግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ሲቪያቶስላቭ ሼቭቹክ ስለ ሲኖዶሱ ሥራ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለዩክሬን ስላደረጉት ድጋፍ ከቫቲካን ዜና ጋር ተወያይተዋል።

ጥያቄ፡- ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጋር ካደረጋችሁት ውይይት ለእርስዎ በጣም አስፈላጊው የነበረው ምንድነው?

መልስ፡ ቅዱስ አባታችን ከእኛ ጋር ናቸው ፥ እኛም ካቶሊካዊነታችንን እና ሙሉ የሆነውን የሚታይ ኅብረታችንን ለቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ለሆኑት ብጹእነታቸው ገልፀናል። እናም በዚያ የህብረት እና የምስራቹ ቃል በሆነው መልካም ዜና መንፈስ ወደ ቤት እየተመለስን ነው። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስን ትሕትና አደንቃለሁ። እሳቸው የራሳቸውን ስህተቶች እና በጣም ግልጽ ያልሆኑ አገላለፆቻቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ ፥ በዚህም የተነሳ ማስተካከያ አድርገዋል።ወንድሞችህ በሆኑት ጳጳሳት ፊት ያለ ምንም ሃፍረት ራስህን ማረም መቻል ይህ የጠለቀ ትህትና ምልክት ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ፥ የቤተክርስቲያኑ ኃላፊ ለሆንኩት ለእኔ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለ45ቱ ጳጳሳት እኛን ለማዳመጥ በመፈለግ ፥ የተጎዱትን እና ተስፋ የቆረጡ ዩክሬናዊያንን ወክለው እንዲናገሩ ቀለል ያለ ክፍት መድረክ ሰጥተዋል።
እናም ይህ የእርስ በርስ ውይይት፣ የመስማት ችሎታ፣ የመደማመጥ አገልግሎት ለእኛ በጦርነቱ ለቆሰለን የፈውስ ጊዜ ነበር።

ጥያቄ፡- ከካርዲናል ዙፒ የቻይና ጉብኝት ምን ይጠብቃሉ?

መልስ፦ የሚጠበቁ ነገሮች አሉኝ ፥ ጉብኝቱ ወደ እውነተኛ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ ሰላም የሚያመጣ ጉዞ እንዲሆን እመኛለሁ።

ጥያቄ፡- የሲኖዶሱ ትኩረት ለተጎዱ ሰዎች ስለሚደረገው ሃዋሪያዊ ዕርዳታ ነበር። በትክክል ምን መሰራት አለበት ብለው ተስፋ ያደርጋሉ?

መልስ፦በመጀመሪያ ደረጃ የካህናት፣ የገዳማዊያን እና የጳጳሳት ምስረታ ላይ አጽንዖት እየሰጠን ነው ፥ ምክንያቱም አሠራራችንን መለወጥ ስላለብን ነው።
በሰው ልጅ ሥነ ልቦናዊ እና ስሜታዊ ክፍል ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ በደንብ መረዳት አለብን ፥ እንዲሁም ስመንፈሳዊ ህይወቱ ማወቅ አለብን ፥ ይህም ለሰዎች የበለጠ ግልጽ ለመሆን እና የተጎዱትን የበለጠ ለመርዳት ይጠቅማል። ምክንያቱም እግሩን በጥይት ተመቶ እግሩን አጥቶ ሆስፒታል ውስጥ ላለ ወታደር ዝም ብለህ ‘ጉዳትህን እረዳለሁ’ ብለህ ብትነግረው ተሳስተሃል። በዚህም የተነሳ ለቆሰሉ ሰዎች በሃዋሪያዊ አገልግሎት መንከባከብ በተለይም ለቤተክርስቲያኗ መፈሳዊ አገልግሎት ትልቅ ፈተና ይመስለኛል።

ጥያቄ፡- አገራችሁ በጦርነት ላይ ነች። በዩክሬን ውስጥ ስላሉት ቤተክርስቲያን ፣ ምእመናን እና  ገዳማዊያንን በተመለከተ ምን እየሆነ ነው?

መልስ፦ ብዙ ነገሮች እየሆኑ ነው ፥ ነገር ግን በመጀመሪያ በእንደዚህ አይነት አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ሁላችንም ካቶሊኮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ኦርቶዶክሶች፣ አይሁዶች እና ሙስሊሞች ዛሬ ላይ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንዴት መለየት እንደምንችል ተምረናል።
እናም ለእኔ በጣም አስፈላጊው ነገር የግሌ የፅናት ምንጭ የሆነው እምነት እንደሆነ ተምሬያለሁ።
ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ መሆን ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ማመን ፣ በጦርነት ግፍ መካከል የቅድስት ሥላሴን ቅዱስ ስም መቀደስ እንደሚገባ ነው ፥ የዩክሬን ህዝብ የጥንካሬ እና የመቋቋም ምንጭ ይሄ ነው።
 

15 September 2023, 14:07