ፈልግ

ሌጎስ የሚገኘው የካቶሊክ የቅዱስ መስቀል ካቴድራል ሌጎስ የሚገኘው የካቶሊክ የቅዱስ መስቀል ካቴድራል 

የፓን አፍሪካ የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ 50ኛ ዓመቱን በአፍሪካ ቤተክርስቲያን በሌጎስ ሊያከብር ነው

የፓን አፍሪካ የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ 50ኛ ዓመቱን በናይጄሪያ ርዕሰ መዲና በሌጎስ ከተማ ከህዳር 8 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከመላው የአፍሪካ አህጉር እና ሌሎች ክፍላተ ዓለማት የተውጣጡ የኮሚኒኬሽን ሃላፊዎችን እና ታላላቅ ሰዎችን በተገኙበት ለማክበር ተዘጋጅቷል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በናይጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ በሚገኘው ‘በሉመን ክርስቲ ካቶሊካዊ ቲቪ ሪትሬት እና ሚዲያ ማዕከል’ የፓን አፍሪካን የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለማክበር ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የካቶሊክ ጳጳሳት እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች በዝግጅት ላይ ናቸው።
በዓሉ ከህዳር 8-11 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ የሚከበር ሲሆን ፥ ከየአፍሪካ ክልል የተውጣጡ ብጹአን ጳጳሳት ይገኙበታል ተብሎም ይጠበቃል።
የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ጳጳሳት ጉባኤ ሲምፖዚየም (ሴካም) ቋሚ ኮሚቴ አባላትም እንደሚሳተፉበት ለማወቅ ተችሏል።
የፓን አፍሪካን የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ ፕረዚዳንት የሆኑት የኦዮ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ኢማኑኤል ባዴጆ እንደተናገሩት በዝግጅቱ ላይ በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ የኮሙዩኒኬሽን ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች የተጋበዙ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ከጉባኤው ውጪ ያሉ ሌሎች የውጭ ሀገር መሪዎችን ጨምሮ ይሳተፋሉ” ብለዋል።
በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ለማክበር የአህጉራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን የሚመሩት ናይጄሪያዊው ጳጳስ በሌጎስ ውስጥ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን ፣ ካህናትን እና ምእመናንን እና ሌሎች የናይጄሪያ እና የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የቤተክርስቲያን ባለስልጣናትን ያካተተ የሀገር ውስጥ አዘጋጅ ኮሚቴ (LOC) አቋቁመዋል።
በበዓሉ ወቅት ከሁሉም የአፍሪካ ክልሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የማይረሳ ልምድ እንዲኖራቸው የሃገር ዉስጥ አዘጋጅ ኮሚቴው ሃላፊነቱን ወስዷል ።

ወደ ሌጎስ ለሚመጡት ልዑካን አቀባበል ማድረግ

የፓን አፍሪካን የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ 50ኛ ክብረ በዓል ላይ የሚጠበቁት ልዑካን ከመላው አፍሪካ እና ከሌሎችም የተውጣጡ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ያካትታሉ።
የሌጎስ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መሪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ አልፍሬድ አዴዋሌ ማርቲንስ ሌጎስ በዓሉ የሚከበርባት ከተማ ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለአዘጋጅ ኮሚቴው ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ሊቀ ጳጳስ አዴዋሌ ይህንን በማስመልከት እንደተናገሩት “የፓን አፍሪካን የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴ 50ኛ የምስረታ በዓላቸው የሚከበርበትን ቦታ ሌጎስ ከተማ እንዲሆን በመምረጣቸው ደስተኛ ነን” ብለዋል። በማከልም "በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በሃገር ውስጥ አስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ በሚያገለግሉ ሰዎች ብቃት እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ሕዝብ ድጋፍ ዝግጅቱ አስደናቂ ስኬትን እንደሚያስመዘግብ አምናለሁ” ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ የመክፈቻ እና የምስጋና አከባበር ወደ ሚከበርበት እና የቀጥታ ስርጭት ወደሚሰራጭበት ሌጎስ በሚገኘው ቅዱስ መስቀል ካቴድራል የሚመጡትን ልዑካን በሙሉ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ነው።
የአፍሪካ እና ማዳጋስካር ጳጳሳት ጉባኤ ሲምፖዚየም (SECAM) በአፍሪካ ቤተክርስቲያን ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጌልን ለማስፋፋት በማሰብ የፓን አፍሪካን የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚቴን (Pan African Committee for Social Communications , CEPACS) እ.አ.አ. በ1973 መመስረቱ ይታወቃል።
 

15 September 2023, 16:37