ፈልግ

አንቶኔላ ስቺያሮኔ የባህል እና ትምህርት ቢሮ ዋና ጸሐፊ አንቶኔላ ስቺያሮኔ የባህል እና ትምህርት ቢሮ ዋና ጸሐፊ 

የዓለም ወጣቶች ቀን በትምህርት ዘርፉ ላይ ባለን ጥሪ መሰረት የመስራትን ጥቅም ያበረታታል ተባለ

በቫቲካን የባህል እና ትምህርት ጽ/ቤ የበላይ ፀሐፊ የሆኑት አንቶኔላ ስቺያሮኔ በትምህርቱ ዘርፍ ላይ መስራት የሚያስከብር የሥራ ዘርፍ እንደሆነ በተለይ የወጣቱን ትውልድ ማስገንዘብ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አስምረውበታል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በዓለም ወጣቶች ቀን በዓለም አቀፍ የትምህርት ስምምነት እና በሁለት ልዩ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ አቋም ይዘን እዚህ ተገኝተናል ያሉት የባህል እና ትምህርት ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊዋ አንቶኔላ ስቺያሮኔ ፥ በሊዝበን የሚገኘው ጽ/ቤት ያከናወናቸውን የተለያዩ ተግባራትን አቅርበዋል።

ክርስቲያናዊ ኑሮ እና ደስታ

ተቋሙ የሚገኘው የደስታ ከተማ በሆነችው እና መንፈሳዊ ነጋዲያኑ በርካታ ክርስቲያናዊ አኗኗርን እንዲሁም የደስታ ምንጮችን ልምድ የሚያገኙበት ቦታ ላይ ይገኛል። “ዋናው ሀሳቡ” ይላሉ ወይዘሮ ስቺያሮኔ ሲገልጹ ፥ “የወጣቶቹን ሃሳብ ለማዳመጥ ነው ፥ እስከ ነሃሴ መጨረሻ ድረስ የተከፈተውን ስለ ትምህርት በኦን ላይን የተካሄደውን ዳሰሳ በያዘው ድህረ-ገጽ እና በQR ኮድ ሃሳቦችን እና ጥቆማዎችን መግለጽ ይችላሉ” ብለዋል።

በትምህርት ላይ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት

የሚከወኑት ተግባራቶች በሙሉ በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ተነሳሽነት በተጀመረው እና ህፃናት በትምህርት ቤት አካባቢ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቦቻቸው እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ጭምር ለትምህርት ያለው ቁርጠኝነትን ለማጎልበት ተብሎ በትምህርት ላይ ከተደረጉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተያያዙ ናቸው።
ጎብኚዎች ፕሮግራሙ ከተመሠረተባቸው ሰባት ግዴታዎች ውስጥ አንዱን የመምረጥ እድል ይኖራቸዋል። በፖርቹጋል የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ስለ ዓለም አቀፍ ስምምነቱ (ግሎባል ኮምፓክት) ላይም ውይይት ተደርጎበታል።

እንደ ጥሪ በትምህርት ዘርፍ ውስጥ መሥራት

በሊዝበን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ የትምህርት ክፍል ውስጥ ሌላ የፓነል ውይይት ረቡዕ እለት ተካሂዷል።
የዚህም የውይይት ርዕስ ‘የትምህርት ዋጋ ፣ ትምህርትን የመረዳት አስፈላጊነት’ የሚል ሲሆን እንዲሁም ተዛማጅ የሙያው ባለድርሻ አካላት የሆኑት መምህራን ፣ ፕሮፌሰሮች እና የመሳሰሉት በዘርፉ ላይ ስለሚያመጡት ለውጥ ውይይት ተደርጎ ነበር።

የትምህርቱን የሥራ ዘርፍ ማክበር

“ወጣቶች በእንደዚህ ዓይነት ሙያዎች እንዲማረኩ ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ፥ ምክንያቱም ያለ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች በጣም ፍሬያማ የሆነ የትምህርት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም” ሲሉ ወይዘሮ ስቺያሮኔ አረጋግጠዋል።
ወይዘሮ ስቺያሮኔ አንቶኔላ ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉ “ለእነዚህ ሙያዎች የበለጠ ክብር ሊሰጠው በሚችልበት ሂደት ውስጥ መገኘት አስፈላጊ መሆኑን በማመልከት ፥ በብዙ ሃገራት አስተማሪ እና ፕሮፌሰር መሆን ያን ያህል የሚያስከብር የሙያ ዘርፍ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
 

04 August 2023, 14:05