ፈልግ

በዓለም ወጣቶች ቀን  የተሳተፉ ወጣቶች በሊዝበን በዓለም ወጣቶች ቀን የተሳተፉ ወጣቶች በሊዝበን   (ANSA)

የዓለም ወጣቶች ቀን ለወጣቶቹ የሚፍጥረው የደስታ ስሜት ልዩ እንደሆነ ተነገረ።

ባለፈው ሃምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጀመረው የዓለም ወጣቶች ቀን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አና አልቬዝ እንደተናገሩት በሊዝበን የሚገኙ የሚዲያ ድርጅቶች በሙሉ “ከልብ የመናገር” ግዴታ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የዘንድሮው ዓመት የዓለም ወጣቶች ቀን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አና አልቬዝ ከመላው ዓለም የሚመጡ ሰዎች በሚሳተፉበት በዚህ ዝግጅት ሥራ ላይ መሳተፍ ‘በጣም የሚያስደስት ነገር’ እንደሆነ እና ይሄም ከስንት ጊዜ አንዴ የምናገኘው “ጸጋ” እንደሆነ ተናግረዋል።

ከ20 በላይ ቋንቋዎች

ወ/ሮ አና ከቡድናቸው ጋር ሆነው የዘንድሮው የዓለም ወጣቶች ቀን የሚጠቀሙባቸው እንደ ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም ፣ ዩቲዩብ ፣ ትዊተር እና ቲክቶክን ጨምሮ የሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የበላይ ሀላፊ ናቸው።
ከነዚህም ውስጥ በተለየ ሁኔታ የፌስ ቡክ ድህረ ገጽ በ20 የተለያዩ ቋንቋዎች ተክፍቷል ፥ ስለዚህም ሲናገሩ “በእውነቱ ይህ የማይታመን ነው” ይላሉ። እንደ አልቬዝ ገለጻ ፥ ይህ መሆኑ በጎ ፈቃደኞቹ በፖርቱጋል ብቻ ሳይሆን በዓለም ዙሪያ እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ አጉልቶ ያሳያል።
የኮሙኒኬሽን ኃላፊዋ በተጨማሪም የዓለም ወጣቶች ቀን ድህረ ገጽን የሚመራው የቴክኒክ ቡድን "እዚህ በሊዝበን የሚደረጉ ማናቸውም ክስተቶች እና ምስሎች እንዲሁም ከቦታው በቴለቪዥን ለሚተላለፉ መንፈሳዊ ነጋዲያኑን የሚመለከቱ ዋና ዋና ዝግጅቶች ሃላፊነቱን እንደወሰደ ተናግረዋል።

ለዓለም ማህበረሰብ ማድረስ

“ይህ ሁሉ ነገር ለዓለም ሁሉ መነገር አለበት” የሚለውን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥረቱ ቀጥሏል ያሉት ሃላፊዋ ፥ ይህ በዓለም ወጣቶች ቀን በአምስቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋዎች (ፖርቹጋልኛ፣ ስፓኒሽ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ) ትርጉም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ዋና ዋና ክስተቶችን በልዩ ስርጭቶች ተተርጉመው የሚተላለፉ የአስተርጓሚዎችን ስራም ጭምር ያካትታል። በዚህም ምክንያት ሁሉም መንፈሳዊ ነጋዲያን በአካባቢያቸው ቋንቋ በሬዲዮ ማዳመጥ እንደሚችሉም ተነግሯል።
ተግባቦት ሰዎችን ስለ አንድ ክስተት ብቻ ከማሳወቅም በላይ ነው። በ “ወንጌል ስርጭት’ ላይ የተመሰረተው የምእመናን የቤተሰብ እና የቤተክርስቲያ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ የተዘጋጀውን “ሥነ-መለኮታዊ መሠረት ያለውን ቁምነገር ነው ማስተላለፍ የምንፈልገው ብለዋል።
“መፈሳዊ ነጋዲያኑ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች መጥተው እርስ በርሳችን ስንገናኝ እና የተለያዩ ተሞክሮዎችን ስንካፈል ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደተሰበሰብን ነው የሚታየው” በማለት ገልጸዋል ወ/ሮ አና።

የዓለም ወጣቶች ቀን መልዕክቶች

መቻቻል ፣ አንድነት ፣ የተለያዩ ባህሎችን በአንድ ቦታ የማሳየት እድል እነዚህ የዓለም ወጣቶች ቀን ለሌላው የዓለም ህዝብ ማስተላለፍ የሚፈልጋቸው ፅንሰ-ሀሳቦች ሲሆኑ ፥ “በአሁኑ ጊዜ በተለይም በአውሮፓ ውስጥ ሰላም በጣም አስፈላጊ ነው” ከሚለው መልዕክት ጋርም ሊያያዝ ይችላል ብለዋል።
የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ መልዕክት ከሆነው ‘ላውዳቶ ሲ’ አስተምርሆ ላይ በመመርኮዝ ከዘላቂነት ጋር ለተያያዙ መልእክቶች ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል።
እንደ ወ/ሮ አና አልፌዝ ሃሳብ የዓለም ወጣቶች ቀንን በማስመልከት የሚሰራጩት መልእክቶች ፥ የካቶሊክ ያልሆኑ ሚዲያዎች በሚሰጡት ሽፋንም ቢሆን ፥ የመደመር ስሜትን ማካተት አለበት ባይ ናቸው።

"ደስታን ያስተላልፉ"

“የዓለም ወጣቶች ቀን ለሁሉም ነው” ሲሉ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዋ አረጋግጠዋል። በማከልም "ከቤተክርስቲያኒቷ ውጭ ያሉ ሰዎች ይህ ለምን ለሁሉም እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፥ ሆኖም የሚተላለፉት መልእክቶች እና አግባብነታቸው በፖርቱጋልም ሆነ በዓለም ዙሪያ የተለመደ ነው” ብለዋል።
ከመላው ዓለም ለተውጣጡ የሚዲያ ድርጅቶች ከተለቀቁት 2,500 የሚሆኑ መረጃዎች መሃል ትልቁ ተግዳሮት የነበረው በወጣቶች መሃል የነበረውን ‘የደስታን ስሜት ማስተላለፍ’ መቻል ነበር። እንደሚታወቀው አንድን ነገር በትክክለኛ ቃላት ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ፥ ነገር ግን ጉዳዩን በትትክል ማየት ከተቻለ በዝግጅቱ ውስጥ በጣም ልዩ የሆነ ነገር እንዳለ ይሰማዎታል” ብለዋል።
“ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ልዩ ነገር አለው ፥ ይህ እኛ ከምናስበው ይበልጣል። እኛ ሙሉ ሀላፊነት ስላለብን ሁሉንም ነገር በፍፁምነት ማከናወን አለብን ፥ ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔር ልዩ እጅ አለ ፥ ይሄንንም አምናለው” በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል።

"ከልባችሁ ተናገሩ"

በዓለም ወጣቶች ቀን ላይ ለተገኙት ጋዜጠኞች ሁሉ የመጨረሻው መልእክት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ "ከልባችሁ ተናገሩ" የሚለውን ቃል ከወጣቶች አንፃር አስታውሰዋል።
“ትናንት በሊዝበን ከተማ ውስጥ በእኩለ ለሊት ላይ ስዘዋወር ወጣቶች በጣም በደስታ እና በሰላማዊ መንገድ ሲራመዱ እና ሲዘምሩ አየሁ ፥ ይሄ በእውነት በጣም ልዩ የሆነ ነገር ነው” ሲሉ ወ/ሮ አልቬዝ ተናግረዋል።
 

03 August 2023, 15:50