ፈልግ

ፕሬዝዳንት ማርሴሎ ሬቤሎ ዴ ሱሳ ፕሬዝዳንት ማርሴሎ ሬቤሎ ዴ ሱሳ   (ANSA)

የፖርቱጋሉ ፕሬዝዳንት ለዓለም ወጣቶች ቀን መንፈሳዊ ነጋዲያን የማበረታቻ መልእክት ላኩ።

የፖርቹጋሉ ፕሬዝዳንት ማርሴሎ ሬቤሎ ደ ሱሳ በዘንድሮው ዓመት በሊዝበን እየተከበረ በሚገኘው የዓለም ወጣቶች ቀን ላይ ለሚሳተፉ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያን የቪዲዮ መልእክት በቫቲካን ዜና በኩል አስተላልፈዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ፥ በፖርቱጋልዋ ከተማ ሊዝበን በሚገኘው ፊጎ ማዱሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዚዳንት ማርሴሎ ሬቤሎ ደ ሱሳ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የፖርቹጋሉ ፕሬዝደንት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ውስጥ በሊዝበን የተደረጉ በሁሉም ህዝባዊ መርሃግብሮች ላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን አጅበዋቸው ተሳትፈዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ሐሙስ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፥ የዓለም ወጣቶች ቀን ላይ የሚሳተፉ መንፈሳዊ ነጋዲያንን ያማከለ የቪዲዮ መልእክት ለቫቲካን ዜና ሰጥተዋል።
ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በአካል መገናኘት ያለውን ጠቀሜታ በማውሳት የዓለም ወጣቶች ቀን ክስተትን “በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ምናልባት አንዴ ብቻ የሚገኝ ልዩ ተሞክሮ ነው” ሲሉ ገልጿል።
ፕሬዝዳንቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈታኝ እየሆነ በመጣው ዓለማችን ውስጥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ችግሮችን ለመፍታት የሚጫወቱትን ወደር የሌለው ሚና እውቅና ሰጥተዋል። ማርሴሎ ይሄንን ሲያብራሩ
"እኚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ በጣም አስቸጋሪ ዓለም ውስጥ የተከሰቱ በጣም ልዩ ሰው ናቸው” ሲሉ ጳጳሱ በዓለም ላይ ባሉ ስፍር ቁጥር በሌላቸው ግለሰቦች ሕይወት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተጽዕኖ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በመቀጠልም ወደ ሊዝበን ለመጡ በርካታ ወጣት መንፈሳዊ ነጋዲያንም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝደንት ደ ሱሳ በፖርቹጋል፣ ሊዝበን ከተማ ለስድስት ቀናት በሚቆየው የዓለም ወጣቶች ቀን ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ከ143 ሀገራት ለጎረፉ በርካታ ምዕመናን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወደፊት ሃላፊነቱን የሚረከብ ወጣት

ፕሬዝደንት ዴ ሶሳ ወጣቶቹ በእምነታቸው ምክንያት ዓለምን እንዴት እንደሚለውጡም ተናግረዋል።
ከዓለም ወጣቶች ቀን በኋላ ወጣቶች ወደ ትውልድ አገራቸው ሲመለሱ ብዙ ትርጉም ያላቸው ልምምዶችን እና ህይወትን የሚቀይሩ ምስክርነቶችን ይዘው ይሄዳሉ።
እነዚህ ታሪኮች ስለወደፊቱ እና ስለሚኖሩበት ዓለም ያላቸውን አመለካከት እንደሚለውጡ ጥርጥር የለውም።
ፕሬዝደንት ማርሴሎ ዴ ሶሳ እነዚህ ሁነቶች በዓለም ዙሪያ ባሉ ወጣቶች ላይ የሚኖራቸውን ከፍተኛ ተጽእኖ በማጉላት ፥ ወጣቶቹ በማህበረሰባቸው እና ከዚያም ባሻገር ባሉ ሰዎች ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን አዎንታዊ ለውጦችን እና አዲስ አመለካከትን እንደሚያጎለብት ተናግረዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ፖርቹጋል ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ቀጥሎ ባለበት በአሁኑ ሠዓት ፥ መንፈሳዊ ነጋዲያኑ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጋር በሚያደርጉትን ቆይታ ምክንያት በሊዝበን ያለው ድባብ በደስታ እና በጉጉት የተሞላ ነው።
 

04 August 2023, 14:49