ፈልግ

የክርስቲያን ማህበረሰብ የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የክርስቲያን ማህበረሰብ የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት ወቅት  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ግድያና ሽብርተኝነትን ለመፈጸም የእግዚአብሔርን ስም መጠቀም አቁሙ ማለታቸው ተገለጸ!

“ሃይማኖትን ለጥላቻ፣ ለዓመፅ፣ ጽንፈኝነት እና ጭፍን አክራሪነትን ለመቀስቀስ እና ለግድያ፣ ለስደት፣ ለሽብር እና ለጭቆና ድርጊቶች በአምላክ ስም ከመጠቀም እንድንቆጠብ አቤቱታዬን በድጋሚ አቀርባለሁ” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በነሐሴ 17/2015 ዓ.ም የተከበረው በሃይማኖት እና እምነት ላይ የተመሰረተ የጥቃት ሰለባዎች የሚዘከበት የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ ቀን አስመልክተው ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሃይማኖት ነፃነት ዙሪያ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ስያጠና የቆየው በዓለም አቀፍ ደረጅት በስቃይ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ባወጣው ዘገባ መሠረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሃይማኖት ነፃነት ተጥሷል። በዓለም ዙሪያ በሃይማኖት ወይም እምነት ላይ በተመሰረቱ ጥቃቶች የተጎዱ ሰዎችን የሚረዳው ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍሎሪያን ሪፕካ ለቫቲካን ረዲዮ የክርስቲያን ስደት ዋና ዋና ምክንያቶችን አስረድተዋል።

የሃይማኖት ነፃነትን ጨምሮ የሁሉም ሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የተከሰቱት በአለምአቀፍ ደረጃ ስልጣናቸውን ለማስከበር በሚደረጉ ጥረቶች እና የመሠረታዊ ቡድኖች መሪዎች በስልጣን ላይ ለማቆየት ታስቦ የሚሰነዘር ጥቃት  መሆኑን ጠቁመዋል።

"ሁለተኛው ምክንያት ከእስላማዊ አገሮች ጋር የተያያዘ ነው"። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች እንደ ቡርኪናፋሶ፣ ኒጀር፣ ማሊ እና ሞዛምቢክ ባሉ አገሮች ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ ያሳስበናል። በእነዚህ ሁሉ አገሮች መንግሥታት እንደ ቦኮ ሃራም ባሉ ማህበራት እና እስላማዊ መንግስት ነን በሚሉ ተከታዮች ላይ እየወሰዱት ያለው እርምጃ እየቀነሰ ሲሄድ እናያለን ሲሉ ተናግሯል።

ሦስተኛው የሃይማኖት ነፃነት ሰብዓዊ መብቶች የሚጣሱበት ምክንያት በህንድ ውስጥ እንዳለን እጅግ በጣም ብሔርተኛ የሆኑ አገሮች ናቸው። አክሎም በህንድ ሰሜናዊ እና በደቡብ መካከል ልዩነት እንዳለ ለምሳሌ በኬሬላ በአጠቃላይ የሃይማኖት ነጻነት አለ።

ቅይጥ የስደት ዓይነቶች

በስቃይ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው አለም አቀፍ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አክለው እንደ ገለጹት በተጨማሪም ቅይጥ የስደት አይነቶች ማለትም "በሀር የተሰራ ጓንት ውስጥ ያለው የብረት ጡጫ" እና ደም መጣጭ አይነትን ጥቃቶችን ጠቅሰዋል። አንዳንድ አገሮች የሃይማኖት ነፃነትን የሚገድቡ ወይም ለተወሰኑ ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች የሚያደሉ አወዛጋቢ ሕጎችን ይተገብራሉ፣ በአጠቃላይ ያለምንም ተቃውሞ ማለት ነው። በሌላ በኩል “የተሳሳተ” ሀይማኖት ተከታዮች ላይ የሚሰነዘሩ የኃይል ጥቃቶች “መደበኛ” እና በዋናነት ክስ ያልተመሰረተባቸው ናቸው (ለምሳሌ፣ በላቲን አሜሪካ) ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

በተለምዶ ስደት የሚደርስባቸው አብዛኞቹ የሃይማኖት ቡድኖች በቁጥር አናሳ የሆኑ የሃይማኖት ማህበረሰቦች ናቸው። ነገር ግን አብዛኞቹ የሃይማኖት ማህበረሰቦች ስደት እየደረሰባቸው ነው (ናይጄሪያ፣ ኒካራጓ) በማለት በምሳሌነት ገልጿል።

ባደጉት ሀገራት ማህበራዊ ሚዲያ የሃይማኖት ቡድኖችን ለማግለልና ለማጥቃት ጥቅም ላይ ውሏል። እንደነዚህ ያሉት ክስተቶች የሕሊና፣ የአስተሳሰብ፣ የሃይማኖት፣ ሐሳብን የመግለጽ፣ የመንቀሳቀስና የመሰብሰብ ነፃነትን ጨምሮ መሠረታዊ እሴቶችን አፍርሰዋል ብሏል።

ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ፣ አብዛኛው የአለም ክልሎች የሀይማኖተኝነት ህዝባዊ መገለጫ የሆኑትን ጉልህ ሃይማኖታዊ በዓላትን ለማክበር ምእመናን በብዛት መመለሳቸውን ተመልክቷል።

በስቃይ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዳው አለም አቀፍ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አክለው እንደ ገለጹት በሃይማኖቶች መካከል የሚደረጉ የውይይት ውጥኖች መጨመራቸውን አስታውቋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ከሌሎች የሃይማኖት ማህበረሰቦች ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስፍተዋል፣ ይህም በጣሊያነኛ ቋንቋ ‘ፍራቴሊ ቱቲ’ (ሁላችንም ወንድማማቾች ነን) እና በብዙ የሃይማኖቶች ስብሰባዎች መገለጹ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.አ.አ በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በግብፅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድርጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ የአልዓዛር ታላቁ መስጊድ እና ዮኒቬርሲቲ ታላቁ ኢማም ከሆኑት አህመድ ሙሀመድ ኣል ታይብ ጋር በተገናኙበት ወቅት የሚከተለውን ንግግር አድረገው ነበር “የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደመሆናችን መጠን ማነኛውንም ዓይነት ቅድስናን የሚያጎድፉ ብጥብጦችን እና ግጭቶችን፣ የኋጢኣት ሁሉ መንስሄ የሆነውን የራስ ወዳድነት መንፈስን በማውገዝ እውነተኛ የሆኑ የውይይት መድረኮችን መክፈት ይኖርብናል። በሰው ልጆች ክብር እና ሰብአዊ መብት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለማውገዝ፣ በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ ጥላቻዎችን በመፍጠር፣ እነዚህን ጥላቻዎች በሐይማኖትና በእግዚኣብሔር  ስም እውነተኛ እንደሆኑ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደርጉትን ጥረቶች በሙሉ ለማጋለጥ እና እነዚህን ጉዳዮች የእውነተኛው አምላክ ፍላጎቶች ሳይሆኑ ነገር ግን የጣዖት አምላክ ፍላጎቶች መሆናቸውን በማሳወቅ፣ የእውነተኛው እግዚኣብሔር ስም ቅዱስ፣ እርሱ የሰላም አምላክ፣ እግዚኣብሔር ሰላም መሆኑን በድፍረት መመስከር ይኖርብናል። ስለዚህ የተቀደሰ ነገር የሚባለው ሰላም ብቻ ነው፣ ስለሆነም በእግዚአብሔር ስም ምንም ዓይነት ግፍ፣ ብጥብጥ፣ ግጭት ሊፈጸም አይችልም፣ ምክንያቱም በእግዚኣብሔር ስም የሚፈጸሙ ግፎች ቅዱሱን የእግዚኣብሔር ስም ያረክሱታልና” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

24 August 2023, 15:34