ፈልግ

2022.04.01 Il cardinale Berhaneyesus convegno con il ministro dell'educazione etiope

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለአገራችንና ለሕዝቦቿ ሰላም ጾመ-ፀሎት እንዲደረግ ጠየቀች

ጌታ ሆይ ፀሎታችንን ስማ ፤ ጩኸታችንም ወዳንተ ይድረስ፡ በመከራችን ቀን ፊትህን ከእኛ ወዲያ አትመልስብን! አሜን። “ኑና እንዋቀስ” ይላል ጌታ “ኃጢአታችሁ እንደ ዓለላ ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።” (ኢሳ 1፤18)

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለአገራችንና ለሕዝቦቿ ሰላምና ደኅንነት ጾመ-ፀሎት እንዲደረግ ለካቶሊካውያን ምዕመናን እና በጎፊቃድ ላላቸው ሁሉ የተላለፈ መልዕክት  

ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ ያላት ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር ነች። የሰውልጅ መገኛ ብለን የምንኮራባት፣ የተለያዩ ህዝቦችና የተለያዩ እምነቶችየሚገኙባት የአብሮነት ምሳሌ ሆና የቆየች የምንወዳት ሀገር ናት። በረከቶቿብዙ ቢሆኑም ሀገራችንና ሕዝቦቿ በተለያዩ ጊዜያት ከጦርነት አዙሪትመውጣት አልቻንም፤ ከድህነትና ጉስቁልና መላቀቅ አቅቶናል። አረጋውያን፣ እናቶችና ህፃናት ከመከራ ጩኸት ነፃ መውጣት አልቻሉም። የሕዝባችን ደምበከንቱ ይፈስባታል፤ ነፍስም በተማዕጽኖ ወደ አባቷ ትጮሃለች። ብዙወጣቶቻችን በየጦር ሜዳው ተሰውተዋል። በሀገራችን ችግሮችን በንግግር፣ በውይይትና በእርቅ መፍታት መገለጫ ባህላችን ሆኖ እያለ ለተለያዩ ብሶቶቻችንግን ጦርነትን እንደ አማራጭ መውሰድ ልማድ እየሆነ የመጣ ይመስላል፤ ሆኗልም።

ሀገራችን ሌሎች ሥልጣኔዎች የደረሱበት እንድትደርስ እንመኛለን፤ ይህንንምበብዙ መስኮች በተደረጉ እንቅስቃሴዎችና መሻሻሎች ለመረዳት ያስችለናል።በተቃራኒው ግን የመኖር ተስፋችን በዚያው ልክ እየደበዘዘ በፍርሃትና ተስፋበመቁረጥ ተውጠናል። ለዚሁም ማሳያው በዘመናት ካየናቸው አስከፊጦርነቶች በተለይም በቅርቡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተካሄደው ጦርነትበውይይት ልዩነቶችን መፍታት ሲቻል ወደ ጦርነት ተገብቶ ቁጥራቸው ቀላልየማይባሉ ወገኖቻችን ረግፈዋል፣ ብዙዎች ቆስለዋል፣ የስነ ልቦና ጉዳትምደርሶባቸዋል፤ ብዙዎችም ተሠደዋል፣ ብዙ ንብረትም ወድሟል። ይህ ክስተትለዘመኑ ሥልጣኔና ዕድገት ለምትዳክር ሀገርና ሕዝብ ባይመጥናትም ዘግይቶምቢሆን በውይይት ሠላም እንዲሰፍን መደረጉ እጅጉኑ አስደስቶናል፤ ሕዝባችንም እፎይታ አግኝቷል፤ እናቶችም ከሀዘን ስብራት አርፈዋል። ይህየሚያመለክተው ሕዝባችን ምን ያህል ጦርነት እንዳንገሸገሸውና ኑሮውንምእንዳጎሳቆለው ማሳያ ነው። ጦርነት የመሸከም አቅማችን ተሟጧል።ሰለሆነም የአገራችን የሰላም እጦትና ጊዜውን እየጠበቀ የሚከሰተውየግጭቶች መፈራረቅ ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል፤ በመሆኑም አገራችንኢትዮጵያ ከወትሮውም በላይ ሰላም የሚያስፈልጋት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
ለሰላም እጦታችን ደግሞ ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ለመፍታትና ጠንካራሕዝባዊ ትስስርንም ለመፍጠር በየጊዜው የሚነሱ ብሶቶችን በውይይትመፍታት ከመቸውም በላይ በጣም አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን። በተቃራኒውግን በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ የጦርነት እንቅስቃሴዎች ያለፈታሪካችንን ቆም ብለን እንድናስብ ይጋብዙናል። ከጦርነት ያተረፍነው ነገርቢኖር የሕይወት መስዋዕትነትና ውድመትን እንዲሁም ቀዬን ጥሎ መሰደድነው። ለዚህም ምክንያታችን አሁንም ችግሮቻችንን በብልሃት፣ በጥበብ፣ በጸሎትና በመነጋገር እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችንና የሃይማኖት አባቶችንበመስማት መፍታት አለመቻላችን ነው። በፅሞናና በጥንቃቄ መደማመጡቀርቶ መቆጣጠር ወደማንችላቸው …ፍልሚያ ውስጥ ገብተናል። በሰዎችመሃከል ያለው የአስተውሎት ተግባቦቶች በችግር ላይ ወድቋል፤ የፈለግነውንብቻ የምንፈበርክበትና መቆጣጠር የማንችለውን ወደጐን የምንልበት አዲስየሕይወትና የተግባቦት ዘይቤ ‹ፈብርከናል›። (ፍራንቸስኮስ፣ ፊራቴሊ ቱቲ ቁ. 49)።
ስለዚህ አውዳሚና አስከፊ እንቅስቃሴዎቻችንን ቆም ብለን በማሰብ ራሳችንንእናውጣ፤ ዳግም ሞትና ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን። ጦርነትለየትኛውም የፖለቲካዊ ችግር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም። ፖለቲካዊ ችግርመፈታት ያለበት መከባበር ባለበት የጋራ ጥቅም በሚያስቀድም ሁኔታበሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ነው። ውይይቱም ብሶት የወለዳቸውን ምሁራንን፤ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን ጭምርያካተተ ቢሆን የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነታችን ነው። ይህእንዲሆን ደግሞ የመንግሥት የፖለቲካ ፈቃደኝነት በጣም አስፈላጊእንደሚሆን ይሰማናል። ምክንያቱም መንግስት ከሁሉም በላይ እኛ በብዙመልኩ ወንድማማችና እህትማማች የሆነውን ኢትዮጵያውያንን በጋራየማምጣት አቅም አለው ብለን እናምናለን።
ስለዚህም የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በሀገራችንእየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱመንግስትንና ተፋላሚ ወገኖችን አጥብቆ ይማፀናል። በዚህም በፍልሰታ ጾምጸሎት ወቅት ልቦናችንን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ፣ ስለ ሰላም፤ ስለፍትህ፤ ስለ ውይይት እንድንጸልይ ለምዕመኖቻችንና በጎ ፊቃድ ላላቸውወገኖቻችን ሁሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር ለሀገራችንና ለሕዝቦቿ ሰላምን ያውርድልን። አሜን!


   አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

08 August 2023, 10:02