ፈልግ

2023.07.28 Young people rejoice in prayer, encounter, meeting, happiness, during preparations for WYD, World Youth Day (Poland 2016)

ወጣት ቤተክርስትያን ውስጥ

ወጣትነት ዝም ብሎ ብቻ የተወሰነ ግዜ ማለት አይደለም የአእምሮ ወይም የአስተሳሰብ ሁኔታ ነው “ለዚያም ነው እንደ ቤተ ክርስትያን ያለች ጥንታዊ ተቋም ተሃድሶን የምትለማመደው እና በዘመኗም የተለያዩ ጊዜያት ወደ ወጣትነት የምትመለሰው” ለዚህም ነው በእርግጥም እጅግ በጣም አስደናቂ በሆኑ ታሪኮቿ ግዜያቶች" ወደ መጀመሪያ ፍቅሯ እንድትመለስ እንደተጠራች የሚሰማት$ ይህንን እውነት በማስታወስ" ሁለተኛው የቫቲካን ካውንስል" “በሚኖርና ረጂም በሆነ ታሪኳ ዳብራ" ወደ ሰብአዊ ፍጽምና እየገሰገሰች የታሪክ እና የሕይወት ወሰን ላይ ለመድረስ በመሞከር" ቤተ ክርስትያን እውነተኛ የዓለም ወጣት ነች”ብሏል ።

ለመታደስ ዝግጁ የሆነች ቤተ ክርስትያን

ቤተ ክርስትያን እንድታረጅ" ባለፈው ውስጥ ተጀቡና አንድትቀመጥ" ተስተካክላ እንዳትቆም ጎትተው ከሚይዙ ሰዎች" እስቲ ጌታ ነጻ እንዲያወጣት እንለምነው እንደገናም ደግሞ ከሌላ ፈተናም ነጻ እንዲያወጣት እንጠይቀው:- ዓለም የሚያቀርብላትን ሁሉ ስለምትቀበል ወጣት እንደሆነች አድርጎ የመቁጠር" መልእክቷን ወደ ጎን በማለት እንደሌላው ሰው ሁሉ ስለምትከውን የታደሰች አድርጎ ከማሰብ ሁኔታ ነጻ እንዲያወጣት አይደለም! ቤተክርስትያን ወጣትነቷ ራስዋን ስትሆን" ከእግዚአብሔር ቃል የሚወጣውን ብርታት" ቅዱሰ ቁርባኑን" የጌታን የዘወትር ሀልዎቱን" እንዲሁም የመንፈሱን ኃይል" በሕይወታችን ውስጥ መገኘቱን ሁልጊዜ እንደ አዲስ ስትቀበል ነው$ ቤተ ክርስትያን ወጣት የምትሆነው አዘወትሯ ወደ ምንጯ የመመለስ አቅም ሲኖራት ነው።

በእርግጥም" እንደ ቤተ ክርስትያን አባልነታችን" ከሌሎች ተለይተን መቆም የለብንም$ ሁሉም ሰው ሊቆጥረን የሚገባው እንደ ጓደኞችና ጎረቤቶች" ልክ እንደ ሐዋርያቱ" “በሕዝቡ መልካም ነገር ይደሰቱ”(ሐዋ 2: 47; 4: 21"33; 5:13) እንደነበሩ እኛም እንደዚያ እንድንቆጠር መሆን አለብን$ እንደዚያም ሆኖ ግን ልንለይባቸው የሚገቡን ነገሮች ደግሞ" ዓለማዊ የሆኑ ነገሮችን መጠቆም" ስለ ልግሥና" አገልግሎት" ንጽሕና" መቆጠብ" ይቅርታ" ለየግል ጥሪያችን ታማኝነት" ጸሎት" ፍትህንና እኩልነትን መሻት" ለተቸገሩ ፍቅርን" እና የማኅበራዊ ወዳጅነትን ውበት" ስንመሰክር መገኘት አለብን$

የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ሁልጊዜም ቢሆን ወደ ፈተና ልትገባ ትችላለች" ምክንያቱም ጌታ አደጋዎችን ሳይቆጥር ምንም ሳያስቀር በእምነት ላይ የሚጋረጡ አደጋዎችን እንድትታደግ ሲጠራት ስለማትሰማ ነው; ሐሰተኛ የሆኑ ምድራዊ ጥበቃዎችን እንድትሻ የሚፈታተኗት ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ$ ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል" ወጣት እንደሆነች ሊያቆያት ይችላል$ ብልሹ እንዳትሆን ሊያስቆማት" በኩራት እንዳትወጠርና ዓለማዊ እንዳትሆን ሊከላክልላት" ይበልጥ ድኻ እንድትሆንና ምስክርም እንድትሆን" ከድኾችና ከተገለሉት ቆን እንድትቆም ሊረዳት" ለፍትህ እንድትቆምና በትህትና ተግዳሮቶችን ለመቀበል ራሷን እንድታዘጋጅ ሊረዳት ይችላል” ወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል የቤተ ክርስትያን በአዳዲስ ጅማሮዎች “ሐሴት እንድታደርግ" ለመታደስ እና ለበለጡ ስኬቶች ራሷን ያለምንም ገደብ እንድትሰጥ" የወጣትነት ውበቷን ሊሰጣት ይችላል”

ወጣት ያልሆንነው ሰዎች ለወጣቶች ድምጽ እና ግድ ለሚሏቸው ነገሮች ከጎናቸው ለመሆን መንገዶችን መፈለግ ይገባናል$ “አጋርነት ለቤተ ክርስትያን የመነጋገሪያ ቦታና ሕይወት ለሚሰጥ ወድማማችነት ምስክር ነው$”12 የወጣቶች ድምጽ እንዲሰማ ይበልጥ ቦታ ልንሰጣቸው ይገባናል: “ማድመጥ" በመተዛዘን ስጦታዎችን ለመለዋወጥ ያስችላል .... በዚያም ላይ" ወንጌል በእውነት ልብን በሚነካ ሁኔታ" በቁርጠኝነት እና ፍሬያማ በሆነ መልኩ እንዲሰበክ ሁኔታዎችን ያመቻቻል” ።

 ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርዕስት ርዕሰሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከጻፉት !ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 34-38 ላይ የተወሰደ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አቶ ባራና በርግኔ

29 July 2023, 16:51