ፈልግ

ታሊታ ኩም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጂዎችን ለማገዝ አለም አቀፍ ዘመቻን ተቀላቀለ። ታሊታ ኩም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጂዎችን ለማገዝ አለም አቀፍ ዘመቻን ተቀላቀለ። 

ታሊታ ኩም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጂዎችን ለማገዝ አለም አቀፍ ዘመቻን ተቀላቀለ።

ታሊታ ኩም ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት የሚሠራው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሴት ገዳማዊያት እህቶች አውታረ መረብ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተጎዱትን ሁሉ ለመደረስ እና ማንንም ወደ ኋላ የማይተው ዓለም አቀፍ ዘመቻን በመቀላቀል ላይ ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.ኤ.አ. ሐምሌ 30 ቀን የሚከበረውን ዓለማቀፍ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚቃወም ቀን ምክንያት በማድረግ  ታሊታ ኩም እ.አ.አ በ2009 ዓ.ም ከአለም አቀፉ የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት ጋር የተቋቋመው የአለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሴት ገዳማዊያት እህቶች ፣ አጋሮች እና በእዚህ ጥላ ሥር የሚተዳደሩ ሌሎች ድርጅቶች አጋሮች አውታረ መረብ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተቀላቅሏል። ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመቃወም ማለት ነው።

እ.አ.አ በ2023 ዓ.ም የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚቃወመው ቀን መሪ ሐሳብ "በህገወጥ የሰዎች ዝዝውር ወንጀል የተጎዱትን ሁሉ ይድረሱ፣ ማንንም ከኋላ አትተዉ" የሚለው እንደ ሆነ ተገልጿል።

ታሊታ ኩም እ.አ.አ በሐምሌ 28/2023 በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ላይ ከወጣት ተሳታፊዎች ጋር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት ቁርጠኛ በመሆን እርስ በርስ እንዲገናኙ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን እና ሀሳቦችን እንዲለዋወጡ የኦንላይን ስብሰባ ያካሂዳል።

የታሊታ ኩም ኢንተርናሽናል የልዑካን ቡድን እ.አ.አ ከነሐሴ 1 እስከ 6/2023 ባለው የአለም ወጣቶች ቀን በሊዝበን ይሳተፋል እና ስለ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ግንዛቤን ለማስጨበጥ ስራ ይሰራል።

ታሊታ ኩም በቅርቡ በ 5 ቋንቋዎች www.talithakum.info/it/report2022 ላይ የሚገኘውን የቅርብ ጊዜ ዘገባውን አቅርቧል።

ሪፖርቱ በመረጃዎች ታሪኮች፣ ምስክሮች እና ሂሳዊ ትንታኔዎች የበለፀገ ሲሆን የታሊታ ኩምን እንቅስቃሴ የመጨረሻ አመት በዝርዝር ያሳያል። ሪፖርቱ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከተጋለጡ ሰዎች ሁሉ ጋር የሚሰራ  መሳሪያም ያቀርባል።

ሪፖርቱ በመከላከል ፣በተጎጂዎች እንክብካቤ ፣በፍትህ ተደራሽነት እና በኔትዎርክ ትስስር ዘርፎች በጥራት እና በመጠን አስደናቂ እድገት አሳይቷል።

ታሊታ ኩም በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 560,606 ሰዎችን የሚደርስ የአውታረ መረብ ትሥር ለመፍጠር ችሏል። እድገትም እያሳየ ይገኛል። ይህ ከ2021 ጋር ሲነጻጸር የ40% እድገትን ያሳያል። ከዚህ 560,606 ሰዎች 34,463 ተጎጂዎች ወይም ከጥቃት የተረፉ፣ 442,276 በመከላከያ ተግባራት ተጠቃሚ ሲሆኑ 83,867 በኔትወርክ፣ በስልጠና እና በአቅም ግንባታ ስራዎች ተሳትፈዋል።

ሌላው የታሊታ ኩም ጠንካራ ትብብር ከሌሎች ሀይማኖቶች ወይም ከሀይማኖቶች መካከል ከተመሰረቱ ቡድኖች ጋር እ.አ.አ በ2022 ባሳየው የ31% እድገት፣ በአካባቢ፣ በክልላዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በእስያ፣ በአፍሪካ እና በኦሽንያ ይታያል።

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ብዝበዛ ላይ እንደ አለም አቀፍ ተነሳሽነት ታሊታ ኩም በአገር አቀፍ፣ በክልል እና በአህጉር ደረጃ በተደራጁ ኔትወርኮች መካከል ትብብርን ያበረታታል፣ ተጎጂዎችን፣ የተረፉትን እና በአደጋ ላይ ያሉ ሰዎችን በንቃት ይደግፋል። ሪፖርቱ ይህንን ባለ ብዙ ደረጃ መዋቅር የሚያንፀባርቅ እና የሁሉንም ቅንጅቶች እና የአውታረ መረብ አባላት አስተዋፅኦ ይሰበስባል።

የታሊታ ኩም ኢንተርናሽናል አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር አቢ አቬሊኖ እንዳሉት፣ “ያለፈው ዓመት እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰቱት በርካታ ቀውሶች፣ በብዙ አገሮች ግጭቶች፣ ለምሳሌ በማያንማር፣ ስሪ ላንካ፣ ሶሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቬንዙዌላ፣ የዩክሬን ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አስጨናቂ እና አስከፊ የተፈጥሮ አደጋዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እነዚህ ሁሉ ቀውሶች በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች ዝውውር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። የአመራር ሽግግሩን ተግዳሮቶች እና የምንኖርበትን ጊዜ ውስብስብነት በማሰላሰል፣ የታሊታ ኩም ኔትዎርክ ለተልዕኮው ቁርጠኛ ሆኖ፣ በብዝበዛ የቆሰሉ ሰዎችን ለመንከባከብ እና በሰው ልጅ ዝውውር ላይ እርምጃ ሲወስድ እናያለን። ምንም እንኳን የተመለከትናቸው ፈተናዎች ቢኖሩም፣ አባላት ለድርጊት ጥሪ ምላሽ መስጠታቸውን ቀጥለው የተጎጂዎችን እና የተረፉትን ህይወት በመንከባከብ፣ በማዳን፣ በማበረታታት እና በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እና ብዝበዛ ላይ ያሉ ህዝቦችን በማሳተፍ ነው።

27 July 2023, 13:45