ፈልግ

ሰኔ 21 ቀን በስቶክሆልም መስጊድ ደጃፍ ላይ የተቃጠለውን ቁርአን በመቃወም በህንድ ፀረ-ስዊድን ተቃውሞ ሲያደርጉ ሰኔ 21 ቀን በስቶክሆልም መስጊድ ደጃፍ ላይ የተቃጠለውን ቁርአን በመቃወም በህንድ ፀረ-ስዊድን ተቃውሞ ሲያደርጉ  (AFP or licensors)

የስዊድን አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በስቶክሆልም ከተማ የተፈፀመውን የቁርአን ቃጠሎን አወገዘ

የስዊድን የማኅበረ ቅዱሳን አካል የሆነው የአቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባለፈው ሰኔ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ከታላቁ የስቶክሆልም መስጊድ ውጭ የተፈፀመውን ቁራንን የማቃጠል ድርጊት በመቃወም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አጋርነቱን ገልጿል ፤ “ይህ ሆን ተብሎ የሙስሊምን እምነት እና ማንነትን የሚያንፀባርቀውን ህግ መጣስ ሲሆን ፥ የሃይማኖት ሰዎች ላይ የተቃጣ ጥቃትም ነው” ብሏል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

 ስዊዲን ውስጥ ባለፈው ሳምንት ሰኔ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ረቡዕ ዕለት ቅዱስ ቁርአን የተቃጠለበት ክስተት ያጋጠመው በሙስሊሞች የጊዜ ቀመር ዋነኛ ከሚባሉት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የኢድ አል አድሃ በዓል በመላው ዓለም በሚከበርበት ቀን አንድ የ37 ዓመት ወጣት ከታላቁ የስቶክሆልም መስጊድ ውጪ የቁርኣንን ቅጂ በእግሩ ረግጦ በርካታ ገፆቹን ደግሞ አቃጥሏል።
በሙስሊሞች ዘንድ ቁርአን የፈጣሪን ቅዱስ ቃልን የያዘ መጽሐፍ ተደርጎ ስለሚታመን፣ ሆን ተብሎ በመጽሐፉ ላይ የሚፈጸም ጥፋት ወይም አከብሮትን መንፈግ በቀላሉ የሚታይ ጥፋት ተደርጎ አይታይም።
በስዊድን ዋና ከተማ ውስጥ የተፈጸመው ይህ ርኩሰት ከመላው ዓለም ኃይለኛ ተቃውሞ የደረሰበት ሲሆን ፥ በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ውስጥ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ በድርጊቱ በተቆጡ ሰዎች ጉዳት ደርሶበታል።
ይሄን ድርጊት የፈጸመው ከሃገሩ ተሰዶ ወደ ስዊድን ያቀናው የኢራቅ ተወላጅ የሆነው ስደተኛው ሳልዋን ሳባህመቲ ሞሚካ በጎሳ እና በዘር ጥላቻ ተጠርጥሯል።
ተጠርጣሪው ለስዊድን የምሽት ጋዜጣ ለሆነው ‘ኤክስፕረሰን’ እንደተናገረው ‘የጥላቻ ወንጀል ወይም ሰዎችን በቁጣ ለማነሳሳት ሳይሆን ተቃውሞዬ ብጥብጥ እና ግድያን በሚቀሰቅሰው መጽሃፉ ላይ ነው’ ብሏል።

ሆን ተብሎ የሙስሊሙን እምነት መጣስ

ከክስተቱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የስዊድን የክርስቲያን ምክር ቤት (SKR) ድርጊቱን የሚያወግዝ መግለጫ በጽሁፍ አውጥቷል።
“እንደ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ማንኛውም ሰው ሀይማኖት ሳይለይ እምነቱን የመከተል መብቱን እናስከብራለን” ይላል መግለጫው። በማከልም “ቁርአንን ማቃጠል ሆን ተብሎ የሙስሊሙን እምነት እና ማንነት መጣስ ቢሆንም ፥ ይሄን ድርጊት በሁላችንም የሃይማኖት ሰዎች ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት ነው የምንመለከተው። ስለዚህም በሃገራችን ላሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች አጋርነታችንን መግለጽ እንፈልጋለን” ይላል።
የምክር ቤቱ የበላይ አመራር አባላት በስቶክሆልም ሀገረ ስብከት የካቶሊክ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንደርስ አርቦሪየስን ፣ ቄስ ማርቲን ሞዴየስ የስዊድን ሉተራን ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፣ የሉተራን እንቅስቃሴዎች መሪ ላሴ ስቬንሰን ፣ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ቤንጃሚን ዲዮስቆሮስ አታስ እና የምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን ወይዘሮ ሶፊያ ካምኔሪንን ያቀፈ ነው።

የስዊድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ አእምሮአችን መመልስ አለብን ማለታቸው

የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስተርሰን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተፈጸመውን ርኩሰት አውግዘው “ስዊድን ውስጥ ወደ አእምሮአችን መመለስ ያለብን ይመስለኛል ፥ ለራሳችን በከፍተኛ የፖለቲካ ደህንነት ስጋት ውስጥ ብንሆንም ሌሎች ሰዎችን የምናስቀይምበት ምንም ምክንያት የለም” ብለዋል።
እ.አ.አ. ከ2020 ጀምሮ በስዊድን ቁርኣንን በመቃወም ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።
በዚሁ ዓመት ጥር ወር ላይ በቱርክ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቀደሰውን የእስልምና ሃይማኖት የቁራን መጽሃፍ በመቃጠሉ ምክንያት ዓለም አቀፍ ቅሬታን አስከትሎ ነበር ፥ በተጨማሪም የኔቶ አባል እና ሲዊዲን በጦር ማኅበሩ ውስጥ ለመግባት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ድምጽ የመስጠት ሥልጣን ያላት ቱርክ ክስተቱን “አስቀያሚ ድርጊት” በማለት ተቃውማዋለች።
ለጥቃቱ ስጋት ፖሊስ ሰልፎችን መከልከል እንደማይችል የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ በቅርብ ለተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ ተሰጥቶ ነበር።
 

04 July 2023, 12:35