ፈልግ

የሞንጎሊያ የመሬት ገጽታ የሞንጎሊያ የመሬት ገጽታ 

የር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልዩ መልእክተኛ የነበሩት ለሞንጎሊያ ልዩ ፍቅር እንዳላቸው ተናገሩ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሚመጣው መስከረም 2016 ዓ.ም. የምስራቅ እስያዋን ሀገር ሞንጎሊያን ሲጎበኙ የመጀመሪያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ይሆናሉ። ብፁዕ ካርዲናል ክሬስሴንዚዮ ሴፔ በ1994 እና 1995 ዓ.ም. የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ወደ ሞንጎሊያ የሄዱ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያጋጠሟቸውን ነገር በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ከወራት በኋላ ወደ ሞንጎሊያ ስለሚያደርጉት ሃዋሪያዊ ጉብኝትንም የራሳቸውን ምልከታ ሰጥተዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

‘ወንጌልን ለህዝቦች’ የተሰኘ ማኅበረ ቅዱሳን የቀድሞ ሊቀ መንበር የሆኑት ካርዲናል ክሬሴንዞ እንደሚያስታውሱት ፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በቅርቡ ወደ ሞንጎሊያ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1995 ዓ.ም ሊያደርጉት ያቀዱት ጉዞ አካል ነው ብለዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሞንጎሊያን ለእመቤታችን አደራ ሰጥተው እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከ70 ዓመታት የኮምኒስት ሥርዓት ዘመን በኋላ ከባዶ የታነፀችበት ሃገረ ሞንጎሊያ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ አስተዳደር መስርተው ነበር።
“ሞንጎሊያን በጣም እወዳታለሁ! ውብ ፣ ኩሩ እና ወዳጃዊ ከሆኑ ህዝቦቿ ጋርም እንዲሁ!” ብለዋል ብፁዕ ካርዲናል ክሪሴንዚዮ ሴፔ የር. ሊ. ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ልዩ መልዕክተኛ በመሆን የምስራቅ እስያ ሀገር የሆነቺውን እና በዚያ ያለችው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቀስ በቀስ በቁጥር እና በመስፋፋት ረገድ ማደግ በጀመረችባቸው ዓመታት ሞንጎሊያን ሁለት ጊዜ ሲጎበኙ ያጋጠማቸውን በማስታወስ ።

የስብከተ ወንጌል ድንበር

“ይህ የሆነው በሚሊኒየሙ መጀመሪያ ላይ ነበር” ይላሉ ካርዲናል ሴፔ ከፊደስ የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፥ በመቀጠልም “ፖላንዳዊው ር.ሊ. ጳጳሳት ሞንጎሊያ የወንጌል አገልግሎትን እውነተኛ ድንበር እንደምትወክል ጠንቅቀው ያውቁ ነበር ፥ ቦታው የመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያን ካቶሊኮችን ሲያጠምቁ እና በመንፈሳዊ እና በተጨባጭ የትምህርት እና የኑሮ መርሃ ግብሮች ድጋፍ የሚደረግባቸው የሚስዮናዊያን ጣቢያዎች እና አብያተ ክርስቲያናት የተቋቋሙበት ቦታ ነበር” ብለዋል።
እንደ አለመታደል ሆኖ ጆን ፖል ዳግማዊ የጤና ሁኔታቸው እያሽቆለቆለ በመምጣቱ በ1995 ዓ.ም. ወደ ሞንጎሊያ የታቀደውን ሃዋሪያዊ ጉዞን ማድረግ አልቻሉም። ነገር ግን ካርዲናል ሴፔን በሁለት አጋጣሚዎች ፥በ1994 እና 1995 ዓ.ም. እዚያ ከሚገኘው እና ገና እያደገ የመጣውን የካቶሊክ ማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ቅርበት ለማሳየት ብሎም በቅድስት መንበር እና በኡላንባታር መካከል የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረትን ለማመልከት ፥ በሞንጎሊያው ፕሬዝዳንት ለቤተክርስቲያን በተሰጠው መሬት ላይ በኡላንባታር የሚገኘውን የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ ካቴድራል ተሰርቶ ለመመረቅ እና የሞንጎሊያን የመጀመሪያ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ሆነው የተመረጡትን ፊሊፒናዊ ጳጳስ ዌንስላኦ ፓዲላን ለመሾም ብጹዕነታቸው ልከዋቸው ነበር።

የካህናት ፍቅር

“ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጆን ፖል ዳግማዊ ማድረግ ያልቻሉትን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እያደረጉት ነው” ብለዋል ካርዲናል ሴፔ። ብጹዕነታቸው ከነሃሴ 25 – 30 2015 ዓ.ም. ወደ ሞንጎሊያ የሚያደርጉት ሃዋሪያዊ ጉዞ ሃገሪቱን የጎበኙ በታሪክ የመጀመሪያው የሮማ ሊቃነ ጳጳስ ያደርጋቸዋል።
እዛ ላሉት ለ1,450 ጠንካራ የካቶሊክ ማህበረሰብ የካህን እንክብካቤ እና ፍቅር እንደሚያመጡ እና አብዛኛው ህዝብ የቡድሂስት ዕምነት ተከታይ ከሆነው ሀገር ጋር ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና ወሳኝ የሀይማኖቶች ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል ብለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የዱር ፈረሶች በዱር ውስጥ የሚቦርቁባት እና አብዛኛው የሞንጎሊያውያን ዘላኖች የሚኖሩባት ፣ ከበግ ፣ ፍየሎች እና ግመሎቻቸው መንጋ ጋር በመሆን ወቅቶችን በመከተል ፥ ድንኳኖቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ሁልጊዜ ይዘው የሚጓዙ ፥ ወሰን በሌለው በሳር የተሸፈነ ገላጣ ምድር ላይ ስላለው ታላቅ ውበት በማስታወስ ፥ ይህ ጉዞ ለብጹዕነታቸው አስደናቂ እንደሚሆን ካርዲናል ሴፔ ገልጸዋል ።
ብፁዕ ካርዲናል ሴፔ ያኔ ሞንጎሊያ በሄዱበት ጊዜ የወቅቱ ሐዋሪያዊ መሪ የነበሩትን ወጣቱ ብፁዕ ካርዲናል ጆርጂዮ ማሬንጎን በግል አስታውሰዋል። ካርዲናል ጆርጆ በ1998 ዓ.ም. ተልእኮአቸውን ከመጀመራቸው በፊት የሃገሬውን ቋንቋ ለመማር ብለው በአገሪቱ ውስጥ ለሶስት ዓመታት በገጠራማ ደቡባዊ ሞንጎሊያ ፥ ከጎቢ በረሃ ባሻገር ብቻቸውን እንዳልሆኑ በተረዱ እንደ እውነተኛ ክርስትያን ተደስተው የቆዩበትን አጋጣሚ ነበር ያስታወሱት።
 

24 July 2023, 15:21