ፈልግ

2020.05.12 speranza, croce, mani

በኀሊናችን ተመርተን እንኑር

ኀሊናችን መልካምና ክፉን የምታስታውቀን የሕይወታችን የፀሐይ ብርሃን ናት። እርሷን ብንከተል ምን ጊዜም አንሳሳትም፣ ድቅድቅ ጨለማ አይከበንም፣ ዓይናችን አይጨፈንም፣ በጥሩ ሁኔታ እንጓዛለን። ባንከተላት ግን በጨለማ ዓይናችንን ያሳውረናል፣ የክፋትን መንገድ ተከትለን እንሄዳለን፣ ኑሮአችን ክፉና አሳዛኝ ይሆናል። እግዚአብሔር ኀሊናን የሰጠን በእርስዋ ተመርተንና ተጠብቀን በቅን መንገድ እንድንሄድ ብሎ ነው። ያለ ብርሃን ዓይንን ጨፍኖ መሄድ መጥፎ ነው ያለ ኀሊና ከተጓዝንም እንዲሁ ነው። ይህም ወደ ጥፋት የሚያደርስ ክፉና አስፈሪ ገደል ነው። እኛ ግን ብዙ ጊዜ ከሕሊናችን ውጭ እንጓዛለን፣ እንሠራለን እንዲሁም እንናገራለን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ  

ኀሊና የሌለን እንመስላለን። እርስዋ ስትናገረን እንዳናዳምጣት ጆሮአችንን እንደፍናለን፤ እየሰማን ደንቆሮዎች እንሆናለን። በዚህ ሁኔታ ያለ ኀሊና እንጓዛለን፤ እየሰማን ደንቆሮዎች እንሆናለን በዚህ ሁኔታ ያለ ኀሊና እንጓዛለን፤ ልናፍናትም እንሞክራለን። በዚህም ጊዜ ሰው እኛን «ይህ ሰው ሕሊና የለውም´ በማለት ያማናል። በተጨማሪም የኀሊናን ደወል አለመሰማት ወይም ተቃራኒ መሆን ትልቅ መንፈሳዊ ጠንቅ ያስከትላል፤ መጨረሻው ጥፋት ይሆናል። ሕይወታችን የማያስደስት እና አጉል ሆኖ የሚገኘው ኀሊናችንን ስለማንከተል ነው። በአረማመዳችን መወላወል ከአምላክ ወይም ከዓለምና ከሰይጣን ሆኖ የማይታየው መልካም ሥራ ለማድረግ የማንቆረቆርና የማናስበው ደግሞ ክፉውን ሥራ ለመተው ስለማናቅድ ነው።

ኀሊናችንን ተከትለን ካልሄድን የሕይወታችን መንገድ የሚያስፈራ ይሆናል የነፍሳችንም መዳን እጅግ አጠራጣሪና የሚያሰጋ ሆኖ ይገኛል። በመንፈሳዊ ሥራችን ሃኬትና ቸልተኝነት ይበዛል፣ የተሰጠንን ሥራ በመጥፎ ሁኔታ እንፈጽማለን፣ ተገደን እናደርገዋለን። ሌላ ሐሳብና ጥሩ የማድረግ አመለካከት የለንም። በፍጥነት ልንጨርሰው ብቻ እንፈልጋለን።

ከኀሊናችን መሪነት ስንወጣ የመንፈስ ቅንነት ይጐድለናል። በዚህም ዓይነት ከእግዚአብሔር መንገድም ውጭ እንሆናለን። የዓይኖቻችን ብርሃን ከጠፋ ምን ያህል እንጐዳለን; የሥጋዊ ኑሮአችንም ያቃወሳል። እንዲሁም ውስጣዊ ኑሮአችን የበለጠ ይጐዳል። ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሰው ሸክም እንሆናለን።

በዚህ ድንገተኛ አደጋ አንዳንጐዳ አስቀድመን ኀሊናችንን እንከተላት የውስጥ ብርሃናችንን እንመልከታት። በሥራችን፣ በሐሳባችን፣ በንግግራችን ሁሉ በኀሊናችን እንመራ የምትለንን ሰምተን በተግባር እናውል።

27 July 2023, 13:52