ፈልግ

የመግባቢያ ሰነዱን በጂ.ኤስ.ኤፍ በሚደገፈው የማኅበረ ቅዱሳን ጥምረት ተወካይ በአባ ጴጥሮስ በርጋ እና እልባት ሶሉሽን ባንክ መካከል ሲፈራረሙ(አዲስ አበባ) የመግባቢያ ሰነዱን በጂ.ኤስ.ኤፍ በሚደገፈው የማኅበረ ቅዱሳን ጥምረት ተወካይ በአባ ጴጥሮስ በርጋ እና እልባት ሶሉሽን ባንክ መካከል ሲፈራረሙ(አዲስ አበባ)   (Giovanni Culmone Gsf)

የኢትዮጵያ ባንኮች የተገለሉ ዜጎችን አነስተኛ ቢዝነሶች ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

በግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ የሚደገፈው በኢትዮጵያ የሚገኙ የካቶሊክ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የግንኙነት መረብ ከሁለት ሀገር በቀል ባንኮች ጋር ለሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፣ ከስደት ተመላሾች እና ለስደተኞች አነስተኛ ብድር ለማቅረብ ስምምነት ተፈራረመ። ይህም የሶስት ዓመት ፕሮጀክት አካል ሆኖ የራሳቸውን ንግድ እንዲጀምሩ ለመርዳት የሚውል ሲሆን በኢትዮጵያ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ስፖንሰር የተደረገ ነው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በ2012 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ በአዲስ አበባ የተጀመረው የግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ የሙከራ ፕሮጀክት በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተባባሪነት ከሴቶች እና ወንድ ገዳምዊያን ማኅበራት ጋር በመተባበር በርካታ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ፣ ፍልሰተኞችን እና ከአፍሪካ ሃገራት የመጡ ስደተኞችን በማግኘት ረገድ እየተሳካለት ነው። እነዚህም ድጋፍ የሚደረግላቸው በኢትዮጵያ መዲና ውስጥ ከፕሮጀክቱ ጋር ተባብረው በሚሰሩ ኩባንያዎች ውስጥ ተቀጥረው በመሥራታቸው ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ስለጀመሩም ጭምር ነው።
የማኅበረ ቅዱሳን ኔትወርክ በቅርቡ ከሕብረት ባንክ እና እልባት ሶሉሽንስ ከተባሉት ሁለት ሃገራዊ ባንኮች ጋር የንግድ ሥራቸውን ለመጀመርና ለማሳደግ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ተፈራርሟል።

በቲላ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሳተፉት ባንኮች በመንግስት እና በማስተርካርድ ይደገፋሉ

በኢትዮጵያ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት ይህ የመግባቢያ ሰነድ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ ስደተኞች እና አቅመ ደካሞች አዲስ የፋይናንስ ማካተት ፕሮጀክት ተግባራዊ እንደሚሆን አስቀድሞ ያሳያል። ፕሮጀክቱ ተደራጅተው ለሚሠሩ የተጠቃሚዎች ቡድን የማይክሮ ብድር አገልግሎት ይሰጣል።
ሁለቱ ሃገራዊ ባንኮች በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚገኙ አቅመ ደካማ ሴቶችን ፣ ተፈናቃዮችን ፣ ስደተኞችን ፣ ቤት የሌላቸው ወጣቶችን እና አካል ጉዳተኞች እና በችግር ላይ ያሉ 42,000 ሰዎች ለመደገፍ ታስቦ በ2013 ዓ.ም. የተጀመረው እና አዳዲስ ሃሳቦች ያሉት የጥላ ፕሮጄክትን የሶስት ዓመት አካታች ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከወኑ የጥምረት አካል ናቸው።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በጋራ የሚሠራ ሲሆን ፥ በአምስት የሀገር ውስጥ የሥራ አስፈጻሚዎች የሚተገበር ነው።

አባ ጴጥሮስ ፡- ቲላ ብድር ለማግኘት ዋስትና ይሰጣል

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ማህበራዊ እና ሃዋሪያዊ ኮሚሽን ጽ/ቤት በሚገኝበት በቅዱስ ሚካኤል ቁምስና ማእከል ከእልባት ዲጂታል ባንክ ጋር የጋራ ስምምነትን የተፈራረሙት በፕሮጀክቱ የሚሳተፉ የጉባኤው ኃላፊዎች በተገኙበት የኮሚሽኑ ኃላፊ የሆኑት አባ ጴጥሮስ በርጋ እና የእልባት አስተዳደራዊ እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ዋና የኦፕሬሽን ባለሙያ ው/ሮ ሙላትዋ ተሾመ ናቸው።
ዲጂታል ባንክ በቲላ ፕሮጀክት ትግበራ ውስጥ የተካተተ ሲሆን አባ ጴጥሮስ እንዳብራሩት እንደ እልባት እና ሕብረት ባንክ ያሉ የአገር ውስጥ ባንኮች ድጋፍ ምስጋና ይግባውና ቲላ የፕሮጀክት ተጠቃሚዎችን ለምሳሌ ለንግድ ሥራቸው ብድር ለማግኘት ለባንክ ዋስትና መስጠት የማይችሉትን ፥ የባንክ ዋስትናዎችን በመስጠት ይረዳል።

የባንክ ሥራ አስኪያጅ ፡- ይህ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ይለውጣል

“እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ፥ እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ሥራ የላቸውም” ሲሉ ወ/ሮ ሙላትዋ ተሾመ ነግረውናል፣ “እንዲሁም በዚህ የመግባብያ ሰነድ የጀመርናቸው ፕሮግራሞች ቢያንስ በከፊል ይህንን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ይችላሉ። የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ይለውጣሉ” ብለዋል።
የእልባት ሥራ አስኪያጅዋ እንዳስገነዘቡት ፥ እንደ እሳቸው ባንክ ካሉ ባንኮች ከሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ፥ አቅመ ደካሞች የራሳቸውን ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ለመክፈት ከማኅበረ ቅዱሳን ልዩ ሥልጠናና የአመራር ድጋፍ ያገኛሉ።
አባ ጴጥሮስ በርጋ በበኩላቸው “ይህ የስምምነት ፊርማ እጅግ በጣም ጠቃሚ አጋጣሚ ነው ፥ ምክንያቱም ከሌሎች አካላት ጋር ያለንን ኔትወርክ እያሰፋን ነው። እናም ይህ በባንኮች እና በተጠቃሚዎች መካከል እንደ አገናኝ ሆኖ ለሚሠራው የቲላ ፕሮጀክት ምስጋና ይገባዋል” ብለዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮጀክቱን የማስፋት ዓላማ አለው

አሁንም ግንባታው ያልተጠናቀቀው አዲስ አበባ በሚገኘው የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ትልቁ ህንፃ ዉስጥ በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን (JCC) የእርዳታ እና ሽርክና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ወ/ሮ ብሩክታዊት በላይን አግኝተናል።
“የቲላ ፕሮጀክት በህብረተሰባችን ውስጥ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች የሥራ እድልን የፈጠረ በመሆኑ ማበረታታት እና ማሳደግ እንፈልጋለን” ሲሉ ነግረውናል።
“ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦቻችን ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች የሥራ እድሎችን ለመስጠት እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ልጆቻቸውን ለመደገፍ እንዲችሉ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ በገባው ቃል መሰረት እየሰራ ይገኛል ፥ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ይህ ሥራ ወሳኝ ነው ፥ እናም በግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንዲንግ እና በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው መሀል በትብብር የሚሠራው ፕሮጀክት ከእኛ ስትራቴጂ ጋር ተመሳሳይ ነው” ብለዋል።

የተገለሉትን ለማገልገል ጠቃሚ መድረክ

የጥላ ፕሮጄክት የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ባለስልጣን የሆኑት አቶ ተፈሪ ታደሰ “በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የተገለሉ ወገኖችን ለማገልገል ይህ ውጤታማ እና የተረጋገጠ መድረክ ነው ፥ በተለይም መስሪያ ቤታችን የምክር አገልግሎት እና ቀጣይነት ያለው ስልጠና በመስጠት አገልግሎቱን ለማሳደግ ቁርጠኝነቱ አለው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “ይህን ለማድረግ ብዙ እምቅ አለን ፥ ምክንያቱም በተለየ ሁኔታ የብድር አገልግሎታቸውን መስጠት የሚያስችላቸው አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት የሆኑ ብዙ አጋሮች ወደ ፕሮጀክቱ እየመጡ ነውና” በማለት ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።
 

10 July 2023, 13:07