ፈልግ

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችንም እርሱ ነው ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችንም እርሱ ነው 

“ኢየሱስ" ሁሌም ወጣት

ኢየሱስ “በወጣቶች መኻከል ወጣት" ለወጣቶች ምሳሌ ለመሆን እና ለጌታ ለመቀደስ ሁሌ ወጣት ነው” በዚህ ምክንያት ሲኖዱ እንዲህ አለ" “ጎልማሳነት የመጀመሪያና የሚያነቃቃ የሕይወት ምዕራፍ ነው" ኢየሱስ ራሱም ያለፈበት" በዚያውም የቀደሰው ነው”

የኢየሱስ ወጣትነት

ዕድሜው ከሠላሣ ትንሽ እንደዘለለ (ሉቃ3:23) ጌታ በመስቀል ላይ “መንፈሱን አሳልፎ ሰጥቷል” (ማቴ 27: 50)ኢየሱስ ወጣት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው ሕይወቱን አሳልፎ ሲሰጥ በአሁኑ ዘመን አጠራር ወጣት" ጎልማሳ ይባላል ሕዘባዊ አገልግሎትን በመጀመሪያ የሕይወት ምዕራፍ ነው የሰጠው" በዚህም ሕይወቱን ለመጨረሻው እስኪሰጥ እንዲያንጸባርቅ “ታላቅ ብርሃን ወረደ” (ማቴ4: 16) ያ" መጨረሻ ደግሞ እንዲያው ዝም ብሎ የተከሰተ አይደለም" ይልቁንም መላ የወጣትነት ዘመኑ" በየትኛውም ወቅት ውድ የሆነ የዝግጅት ወቅት ስለነበረ ነው “በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገር የምስጢሩ ምልክት ነበር” “በእርግጥም የኢየሱስ ሙሉ ሕይወት የመዳን ምስጢር ነው”  ።

ወንጌል ስለ ኢየሱስ የሕጻንነት ወራት ብዙም የሚነግረን ነገር ባይኖርም" ስለ ወጣትነትና የጉልምስና ወራቶቹ ግን አያሌ ነገሮችን ይናገራል ማቴዎስ የጌታን የወጣትነት ግዜ በሁለት ሁኔታዎች ያነሣል: ከስደት በኋላ ከቤተሰቡ ጋር ወደ ናዝሬት የመመለሱን እና በዮርዳኖሰ ወንዝ ተጠምቆ አገልግሎት የመጀመሩን የኢየሱስ የሕጻንነት ምስል ያለን በግብጽ አገር የተሰደደበት የትንሽነቱ ወቅት ነው (ማቴ 2: 14-15)"እንደገናም ወደ ናዝሬት መመለሱን (ማቴ 2: 19-23) ኢየሱስን እንደ ወጣት ጎልማሳ የምናይበት የመጀመሪያው ምስል" ዘመዱ በሆነው በዮሐንስ መጥምቁ ለመጠመቅ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሕዝብ መኻከል እንደ ማንኛውም የሕዝቡ አባል ቆሞ ነው (ማቴ 3:13-17) ።

የጸጋ ሕይወት እንደሚያስተዋውቀን" እኛ እንደምንጠመቀው ያለ ጥምቀት ሳይሆን የኢየሱስ ጥምቀት" የሕይወቱን ተልዕኮ መፈጸም የሚጀምርበትን ቅድሚያ መሰጠት ነው ወንጌል እንደሚነግረን " በጥምቀቱ ወቅት አባቱ ተደስቶ እንዲህ አለ" “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ" በአንተ ደስ ይለኛል”(ሉቃ 3:22) ኢየሱስም ወዲያውኑ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከውሃ ውስጥ ወጣ መንፈስም እየመራው ወደ በረሃ ሄደ በዚያም ሆኖ ወጥቶ ለመስበክና ተዓምራትንም ለማድረግ" ነጻነትንና ፈውስን ለማምጣት ተዘጋጀ (ሉቃ 4:1-14) ወጣት የተባለ ሁሉ" በዚህ ምድር ለተልእኮ መጠራቱ የሚሰማው" አብ እነዚያኑ ቃላት ሲናገር ከሙሉ ልቦና እንዲሰማ ተጋብዟል"“የምወድህ ልጄ አንተ ነህ” ።

ከእነዚህ ሁለት ማስረጃዎች መኻከል ደግሞ ሌላም የምናገኘው አለ" ኢየሱስ ካደገ በኋላ ከወላጆቹ ጋር ከናዝሬት ሲመለስ" ጠፍቶ ሲፈለግ በመቅደስ የተገኘበት ወቅት (ሉቃ 2: 41 51); በዚያ ስፍራ የምናነበው"“ከዚያም ወደ ናዝሬት አብሯቸው ወረደ ይታዘዝላቸውም ነበር” (ሉቃ 2:51);ቤተሰቡን አልካደም ነበር ሉቃስ በመቀጠልም “ኢየሱስ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ” (ሉቃ 2:52)ይላል ቅዱስ ጳውሎስ ዮሐንስ 2ኛው ሲያስረዱ" “ያደገው በአካላዊ እድገት ብቻ አልነበረም በኢየሱስ ውስጥ መንፈሳዊ እድገት ነበር” ምክንያቱም" “በኢየሱስ ውስጥ

የጸጋው ሙላት ከእድሜው ጋር የተመጣጠነ ነበር; ሁልግዜም ሙላት ነበር" ነገር ግን ሙላቱ ከእድሜው መጨመር ጋር እየጨመረ የሚሄድ ነበር”። ወንጌል እንደሚነግረን ከሆነ" ኢየሱስ በወጣትነቱ ወራት የአባቱን እቅድ ለማሳካት በመዘጋጀት “እየሠለጠነ” ነበር የወጣትነቱና የጉልምስናው ወራት ለዚያ አስደናቂ ተልእኮው አደራጀው ።

በወጣትነቱና በጉልምስናው ግዜ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር የነበረው ግንኙነት የተወዳጅ ልጅ ነው ወደ አባቱ ተጠግቶ" ለጉዳዩ ግድ እያለው ነው ያደገው;“ለምን ፈለጋችሁኝ በአባቴ ቤት መገኘት እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?”(ሉቃ 2:49) እንደዚህ ሲባል ግን ኢየሱስ ራሱን ያገለለ በራሱ ጉዳይ ብቻ የተያዘ እንደነበረ ተደርጎ መታሰብ የለበትም ግንኙነቶቹ ማንኛውም ወጣት እንደሚያደርገው ከቤተሰቦቹና ከሕዝቡ ጋር በጋራ በመኖረ ነበር የአባቱን የዮሴፍን ሥራ ተምሮ የአናጢነት ሥራውን ተክቶ መሥራት ጀመረ በወንጌል ውስጥ በአንድ ስፍራ ላይ “የአናጢው ልጅ ተብሎ” (ማቴ 13 : 55) ተጠርቷል በሌላ ግዜ ደግሞ “አናጢው” (ማር 6: 3) ይህ ዝርዝር እንደሚያሳየን ከሌሎች ጋር ግንኙነት ወይም ትስስር ያለው የከተማው አንዱ ወጣት እንደነበር ነው ከሌሎች የተለየ ያልተለመደ ሰው አድርጎ የሚቆጥረው ማንም አልነበረም በዚህ ዋነኛ ምክንያት" አንድ ግዜ ኢየሱስ ሲሰብክ ይህንን ሁሉ ጥበብ ከወዴት እንዳመጣው ማወቅ ባለመቻላቸው እንዲህ ሲሉ አስተያየት ሰጡ" “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?”(ሉቃ 4:22) ።

በእርግጥ" “ኢየሱስ ከማርያምና ከዮሴፍ በጣም በቅርርብ ባያድግም ከመላው ቤተሰብ ጋር ይግባባ ነበር" ማለትም ከዘመዶቻቸውና ከጓደኞቻቸው”8 ስለዚህም የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሆኖ(ሉቃ 2: 42) " ለምን" መቼ" ከኢየሩሳሌም ጉዞ እንደተመለሰ ለማወቅ እንችላለን ምንም እንኳን አንደ ሙሉ ቀን ያላዩት ቢሆንም እንኳን" እርሱ ግን በሕዝቡ መኻከል ወዲህና ወዲያ ይል ነበር: “አብሮአቸው ያለ መስሎአቸው የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዙ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር” (ሉቃ 2:44) በእርግጥም የመሰላቸው ኢየሱስ በዚያ ከወጣቶች ጋር ተደባልቆ እየቀለደ" አየተሳሳቀ" የትልልቆቹንም ወሬ እያደመጠ ደስታቸውንና ሐዘናቸውን እየተካፈለ እንደሆነ ነበር ስብስቡን ወይም ግሩፑን ለመግለጽ ሉቃስ የተጠቀመት ግሪኩ ቃል - ሲኖዲያ- በግልጽ የሚያስረዳው ሰፋ ያለ “በማኅበራዊ ጉዞ ላይ” በዚያም ውስጥ ቅዱስ ቤተሰብ አካል የሆነበት ነበር ወላጆቹ ስላመኑት ምስጋና ይግባቸውና " ኢየሱስ በነጻነት መንቀሳቀስና ከሌሎች ጋርም መራመድን ተምሯል።

ወጣትነቱ ያስተምረናል

እነዚህ የኢየሱስ ሕይወት ሁኔታዎች" እያደጉና በሕይወታቸው ውስጥ ያለውን ተልእኮ ለማሳካት ለሚዘጋጁ ወጣቶች አረጋጋጭ ሊሆንላቸው ይችላል ይህም ከአብ ጋር በግንኙነት ማደግን" የቤተ ሰብ እና የሕዝብ አካል የመሆን ግንዛቤን" እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ለመወጣት" ምሪት ለማግኘት" በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት" ልብን መክፈትን ያካትታል ወጣቶችን ከወላጆቻቸው እና ከሰፊው ሕዝብ የሚያገልላቸው አልያም ጥቂቶች የሚመረጡበት ከሌላው የማይነካኩበት ፕሮጀክት የምንፈጥር ከሆነ" ከወጣቶች ጋር የሚሠራ ሐዋርያዊ ሥራ" ከእነዚህ ውስጥ የትኛውም ቢሆን ቸል ሊባል የሚገባ ጉዳይ አይደለም ይልቁንም" የምንፈልጋቸው ፕሮጀክቶች የሚያጠናክራቸው" ከሌሎች ጋር እንዲገናኙ አጋዥ የሚሆናቸው በተልእኮ በለጋነት እንዲሳተፉ ነው ።

ኢየሱስ የሚያስተምራችሁ ከሩቅ ወይም ካለምንም ሳይሆን ከወጣታንነታችሁ ውስጥ" ከእናንተ ጋር ወጣትነትን በመካፈል ነው በወንጌላት እንደተጠቀሰው ያለውን" ወጣቱን" ኢየሱስ ልታሰላስሉት በጣም አስፈላጊ ነው" ምክንያቱም በእውነት እርሱ ከእናንተ እንደ አንዱ ነበር" የእናንተንም ወጣት ደግ ልብ ይጋራል ይህንንም ሁኔታ በሚቀጥለው ምሳሌ እናያለን " “ኢየሱስ መጨረሻ በሌለው ሁኔታ በአባቱ ይታመናል" ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወዳጅነት ወይም ጓደኝነት ነበረው" ቀውስ በተፈጠረ ግዜ እንኳን በታማኝነቱ ቀጥሏል በጣም ለደከሙ" በተለይም ደግሞ ለድኾች" ለህሙማን" ለኀጢአተኞች እና ለተገፉ ጥልቅ የሆነ ርኅራኄ ነበረው ሃይማኖተኞችን እና በእርሱ ዘመን የነበሩ የፖሊቲካ ባለ ሥልጣናትን ያለ ምንም ፍራቻ ይጋፈጣቸው ነበር" ሰዎች አሳባችንን ሳይረዱን መቅረታቸውና የመገለል ስሜትን ያውቀው ነበር" የስቃይ ፍርሃት እንዴት እንደሚያደርግ ያውቀዋል ትኩረቱን ወደፊቱ ላይ አደረገ" በመንፈሱ ብርታት ራሱን በአባቱ እጅ ላይ አስቀመጠ በኢየሱስ ውስጥ ሁሉም ወጣት ራሱን ማየት ይችላል”።

በሌላ በኩል ደግሞ" ኢየሱስ ተነሥቷል" እኛም የዚህ አዲስ ሕይወት ተካፋዮች እንድንሆን ሊያደርገን ይፈልጋል በአረጀ ዓለም እውነተኛው ወጣትነት እርሱ ነው" ፍጥረት ሀሉ “በመቃተት” (ሮሜ 8:22) የሚጠብቀው ከብርሃኑ እንዲለብስና የእርሱንም ሕይወት እንዲኖር ነው እርሱ ከጎናችን ሆኖ" ሕይወት እውነትም እንዲኖር የተገባው እንዲሆን እየነገረን" ህልሞቻችን" ፕሮጀክቶቻችን" ታላላቅ አሳቦቻችን እውን እንዲሆኑ ከእውነተኛው ምንጭ መጠጣት እንችላለን ሁለት አጓጓጊ የሆኑ ዝርዝሮች በማርቆስ ወንጌል ውስጥ እንደሚያሳዩን ከሆነ ከክርስቶስ ጋር የተነሡ የተጠሩት ለእውነተኛ ወጣትነት እንደሆነ ነው ጌታ በስቃይ ላይ ሆኖ አንዱ ወጣት በፍርሃት ራቁቱን እንደሮጠ ይነግረናል (ማርቆስ 14: 51 - 52); ጌታን ለመከተል ብርታት አጣ በባዶው መቃብር አጠገብ ደግሞ ስለ ሌላ ወጣት እናነብባለን; “ነጭ ልብሰ የለበሰ” ጎልማሳ (ማርቆስ 14:51) ሴቶችን እንዳይፈሩ ሲነግራቸው የትንሣኤውንም ደስታ ሲያውጅላቸው(ማርቆስ 16: 6-7)።

በሌሎች ወጣቶች ጨለማ ውስጥ ከዋክብትን እንድንለኩስ ጌታ ይጠራናል ወደ እወነተኞቹ ከዋክብት እንድትመለከቱ ይጠይቃችኋል" ወደ እርሻው ለመውጣት ከዋክብትን አስቀድሞ እንደሚመለከት ገበሬ" መንገዳችንን ለመምራት የተለያዩ ምልክቶቹን እንድናይ ይፈልጋል ወደፊት ለመራመድ እንዲረዳን እግዚአብሔር ከዋክብትን ያበራልናል ክርስቶስ ራሱም የብርሃን ተስፋችን ነው በጨለማም መሪያችን" ምክንያቱም እርሱ “የሚያበራ የንጋት ኮከብ ነው”(ራዕ 22: 16)።

ምንጭ፡ “ክርስቶስ ሕያው ነው”! በሚል አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይፋ ካደረጉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 22-32 ላይ የተወሰደ።

አዘጋጅ እና አቅራቢ ባራና በርገኔ ሮም

 

08 July 2023, 11:58