ፈልግ

እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም በየመን ሰማዕት የሆኑ የፍቅር ሥራ ልጆች (የእማሆይ ትሬዛ) ማሕበር አባላት ደናግላን እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም በየመን ሰማዕት የሆኑ የፍቅር ሥራ ልጆች (የእማሆይ ትሬዛ) ማሕበር አባላት ደናግላን  

አቡነ ሂንደር የየመን ሰማዕታት እህቶች 'የኢየሱስ ፍቅር እዚህ እንዳለ' አሳይተዋል ማለታቸው ተገለጸ።

የቀድሞ የደቡቡ አረቢያ ሐዋርያዊ እንደራሴ አቡነ ፖል ሂንደር ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሰማዕትነት የተገደሉትን የፍቅር ሥራ ማሕበር (የእማሆይ ትሬዛ ማሕበር አባላት) እህቶች 'እነሆ የኢየሱስ ፍቅር' ብለው እንዳሳዩት አስታውሰው አዳዲስ ሰማዕታት ለእምነት የሰጡትን ምስክርነት ማጉላት ያለውን ጥቅም አስምረውበታል፥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የእነርሱን የሕይወት ሁኔታ የሚያጠና ኮሚሽን ማቋቋማቸውንም አክለው ገለጸዋ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"እነዚህ እህቶች 'የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እዚህ አለ' ብለው አሳዩኝ፣ እናም ሁኔታው ፈገግታ የማያስፈልገው በሚመስልበት ጊዜም እንኳ "ሁልጊዜ ፈገግ ይሉ ነበር" ብሏል።

ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በወቅቱ በአካባቢው ቤተ ክርስቲያንን የመሩት የቀድሞ የደቡብ አረቢያው ሐዋርያዊ እንደራሴ አቡነ ፖል ሂንደር እ.አ.አ በመጋቢት 2016 ዓ.ም በሰማዕትነት የተገደሉትን የፍቅር ሥራ ማሕበር አባላት ምስዮናዊያን አራቱን እህቶች አስታውሰዋል። በየመን የወደብ ከተማ በኤደን በሚገኘው በእማሆይ ቴሬዛ መነኮሳት የሚተዳደረውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአረጋዊያን ማረፊያ ቤት በታጣቂዎች ተወረረ።

አቡነ ፖል ሂንደር የእነርሱ ሰማዕትነት እስከ መጨረሻው ድረስ ለክርስቶስ እና ለሌሎች ፍቅር የመመስከር ጥልቅ ትሩፋት አስተምህሮ ትቶ አልፏል ብሏል። ሰማዕታት እህቶችን ጨምሮ ለዘመናችን ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን እንዲቋቋም መጠየቀቻው ተገልጿል። ይህም የሆነበት ምክንያት ሰማዕታት ኢየሱስን ለመመስከር በሚያደርጉት ጥረት ለሕይወታቸው ዋጋ ለመክፈል ስለማይሠስቱ ጭምር ነው ብሏል።

በዚህ ቃለ ምልልስ፣ ግዛታቸው የመንን የሚያጠቃልለው የስዊዝ ጳጳስ፣ ሐዋርያዊ እንደራሴ እና በአረብ አገር አስተዳዳሪ ሆነው ሲያገለግሉ፣ ልዩ በሆነ መንገድ አርአያነታቸውን ያስታውሳሉ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን የሚመለከት ጳጳሳዊ ተቋም መቋቋሙን የሚገልጽ ደብዳቤ ባወጡበት ዕለት ነው። እ.አ.አ የ2025 የኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ የቅዱሳን "የአዲስ ሰማዕታት ኮሚሽን - የእምነት ምስክሮች" መንስኤዎች በሚል መሪ ቃል እንደ ሚዘከር ይጠበቃል። የቡድኑ ዓላማ በክርስቶስ ላይ ያለንን ፍቅር ለመግለጽ እና ቅዱስ ወንጌልን ለመመስከር ደማቸውን ላፈሰሱ ክርስቲያኖችን ሁሉ ሰነድ ማዘጋጀት ይሆናል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በየካቲት 19/2023 የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካደረጉ በኋላ ለታዳሚዎች እንደ ተናገሩት እማሆይ አንሴልም፣ እማሆይ ማርጌሪት፣ እማሆይ ሬጂኔት እና እማሆይ ጁዲት “የዘመናችን ሰማዕታት” በማለት በአንድነት መገደላቸውን አስታውሰው ነበር። በየመን "ለብዙ ዓመታት በአስከፊ፣ በተረሳ ጦርነት የቆሰለች፣ ለብዙዎች ሞት የዳረገ እና ዛሬም ብዙ ሰዎችን በተለይም ሕፃናትን ለመከራ የሚዳርግ ምድር" በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ “አብረቅራቂ ምስክሮች እንዳሉም አስታውሰዋል። እምነት፣ እንደ የፍቅር ሥራ ማሕበር ምስዮናውያን እህቶች፣ ምንም እንኳን “በዚያ ሕይወታቸውን ቢሰጡም” “አሁንም አሉ” እና “ይቀጥላሉ” ማለታቸው ይታወሳል።

ጥያቄ፡ አቡነ ፖል ሂንደር፣ በየመን የፍቅር ሥራ ማሕበር እህቶች ሚስዮናውያን ሰማዕትነት የተሰጠው ውርስ፣ ምስክርነት ምን ነበር?

መልስ፡ የእነርሱ ምስክርነት እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝነት ምስክርነት ነው፤ በጦርነት እና በአደጋ ሁኔታ ውስጥ እንኳን አንድ ሰው በአክራሪዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ምክንያቶችም ሊገድል ይችላል። በዚህ የየመን ሁኔታ በተለይም በኤደን እ.አ.አ በ2016 እህቶች የሰጡት ምስክርነት ለኔ ሁሌም አዲስ ነገር ነበር፣ አልሸሹም ነበር። እነርሱን መንከባከብ ካለባቸው ምስኪን ሰዎች ጋር በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ቆዩ። ይህን ያደረጉት በቁርጠኝነት፣ እና በደስታ ቁርጠኝነት፣ በጣም ንጹህ ላልሆኑ እና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች ታማኝ በመሆን፣ ይህም ሁል ጊዜ ያስደነቀኝ ነበር። በየዓመቱ እህቶችንና ቤታቸውን እጎበኝ ነበር፣ እዚያም የታመሙትን፣ አረጋውያንን አግኝቼ የሚንከባከቧቸውን ሰዎች ፊት እመለከት ነበር። እህቶቹ ‘የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እዚህ አለ’ ብለው አሳዩኝ።”

በባህሪ እና በድርጊት እና በእህቶች ምስክርነት ውስጥ ስጋ ለብሶ ነበር፣ እና ይህ አስፈላጊ ይመስለኛል። በኢስላማዊው ሀገር ስለ ቅዱስ ወንጌል በግልፅ መናገር ባይችሉ እንኳን ህይወታቸው እና ባህሪያቸው፣ ተግባራቸው ከቃላት በላይ ተናግሯል። ይህ ደግሞ በየመን ውስጥ ያለውን እውነታ በመምራት ላይ በነበርኩባቸው ዓመታት ሁሉ ምልክት ሆኖኛል።

ጥያቄ፡ ስለእነዚህ ለእህቶች ልዩ ትዝታ አሎት ወይ?

ታማኝነታቸውን እና ደስታቸውን ለማየት ይህ አጋጣሚ ነበር።

“ሁኔታው ሁል ጊዜ ፈገግ የሚያስብል እንዳልሆነ ባውቅም እነዚህ እህቶች ሁል ጊዜ ፈገግ እያሉ ነው ያገኘኋቸው።

ያ ከእነርሱ ጋራ አብረው በሚሰሩ ሰራተኞችም ውስጥ ጭምር ታይቷል፣ ከተባባሪዎቹ ውስጥ በዋነኛነት ሙስሊሞች ነበሩ፣ ነገር ግን በእህቶች አውድ ውስጥ በእውነታው ውስጥ ኖረዋል፣ እና እኩል ከፍለው ህይወታቸውን ሰጡ። ከክርስቲያን እህቶች ጋር ተባብረው የሠሩት ቀላል ያልሆነ ሐቅ፣ እኔ እላለሁ፣ ‘የደም ሃይማኖትን መሠረተ እምነት’፣ እሱም ከማንኛውም ቃል የበለጠ ጠንከር ያለ ነው። በኤደንም ይሁን በሌላ ቦታ፣ ቀደም ሲል እህቶች ሊገኙባቸው በሚችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ እነሱን ስጎበኛቸው አንድ የሚያምር እውነታ አይቻለሁ።

ማንም ሰው እንደዚህ ዓይነት ህይወት ሊኖር ይችላል ብሎ በማይጠበቅበት እና እንደዚህ ዓይነት ምስክርነት ሊሰጥ በሚችል የአለም ጥግ ላይ ይህ እውነታ በማግኘታችን ኩራት ይሰማኛል።

"በጋዜጦች ወይም በሌሎች ቻናሎች አርዕስተ ዜናዎች ላይ ቦታ ላያገኝ ይችላል፣ነገር ግን የእነዚህን የፍቅር ሥራ ምሲዮናውያን ፍቅር ባጋጠማቸው እና አሁንም ባጋጠማቸው በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ የተቀረጸ ምስክርነት ነው”።

አሁን አንዳንዶች ለህይወት በህይወታቸው ከፍለዋል። ሌሎች ደግሞ በጦርነት በምትታመሰው አገር አሁን ባለው ሁኔታ የቻሉትን ያደርጋሉ።

ጥያቄ፡ እነዚህን ሰማዕታት እህቶች ጨምሮ እና በአለም ዙሪያ ህይወታቸውን ለእምነት ሲሉ ህይወታቸውን የሰጡ እና ሌሎችን ለመርዳት ቤተክርስትያን እውቅና መስጠቷ ምን ዋጋ አለው?

መልስ፡ በማስታወስ ውስጥ አጭር የመሆን አደጋ ሁል ጊዜ አለ። በተለይ በዘመናችን ብዙ አዳዲስ ነገሮች እየተከሰቱ ነው መጥፎ ነገሮች እና ጥሩ ነገሮች ዛሬ የምናውቀው ነገ የሚረሳ ነው። በቅዱሳን የቀን መቁጠሪያ ውስጥ የሚገኙትን የሩቅ ዘመናትን ብቻ ሳይሆን በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ዋልታ ጭምር ያለፉትን ምስክሮች አለመዘንጋት ጥሩ ነው።

ለዛም ነው በእየአመቱ እ.አ.አ በሰኔ 30 ቀን በሃገረ ስብከታችን  ያስተዋወቅነው የዘመናችን ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን እንዲሆንልን አሁንም ስመተ ቅድስና ወይም ስመተ ብጽዕና ላልተቀበሉ እህቶች ይሁን እንጂ ዛሬም በመካከላችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የክርስቶስ ምስክሮች እንዳሉን መዘንጋት አይኖርብንም። በእርሱ ማመን እና በህይወታቸው ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ሰዎችም ጭምር። በማስታወሻችን፣ በአጀንዳችን፣ በዘመን አቆጣጠራችን ላይ ማስቀመጥ እና አለመዘንጋት ተገቢ መሆኑን ያሳያል።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋጋ በከፈሉ ሌሎች ምስክሮች ጫንቃ ላይ መቆማችንን መዘንጋት የለብንም ስለዚህ በሁሉም አሳፋሪ ነገሮች የተቸገረን ብቻ ሳይሆን እስከ ምእመናን ድረስ የበረታን እምነት ይዘን መሄድ እንችላለን። በመጨረሻው ሰዓት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕትነትን እንኳን ለመታገሥ ዝግጁ ነበሩ።

ጥያቄ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሰማዕታት በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ በቅርቡ በጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ታዳሚዎች ላይም ተናግረው ነበር፣ ነገር ግን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ። ዛሬ ግን ይህ ኮሚሽን አዲስ ሰማዕታትን እና ለእምነት ሲሉ የሞቱትን ወይም የተገደሉትን ለማሰብ ተጨባጭ ተነሳሽነት ይፋ ሆነ። በዚህ ውስጥ ምን ዋጋ ታያለህ?

እንዳንረሳው፣ እንደምናውቀው፣ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ትውልድ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚ ምስክሮችም አሉ። ለወንጌል ምስክርነት ነፍሳቸውን ይከፍላሉ። እርግጥ ነው ሁልጊዜ ግልጽ አይደለም።

ያንን በቤተክርስቲያን የጋራ ትውስታ ውስጥ ለማስታወስ ለእያንዳንዳችን በጣም አስፈላጊ ነው፡ ምክንያቱም አለበለዚያ የምናስበው ስለ ሌሎች የወንጌል ገጽታዎች ብቻ ነው። ነገር ግን “ኢየሱስን እወድሃለሁ” ለማለት የሕይወታችንን አጠቃላይ ቁርጠኝነት ይጠይቃል። በተፈጥሮአዊ ስሜታችን የማንሄድበትን መንገድ እርሱን ወደሚመራን መከተል ማለት ነው። ያ የክርስትና ሕይወት አካል ነው።

እህቶች በተለይም በየመን ያሉ ሰማዕታት ተመሳሳይ እውነታ አስተምረውኛል። ምናልባት አንድ ቀን አንተም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ልትመራ እንደምትችል እና ጌታ ብርታቱን እንዲሰጠኝ መጠየቅ አለብኝ ወይም እንድንሸሽ ሳይሆን ብርታትን እንዲሰጠን ማሰቡ ለራሴ ፈታኝ ነበር። በታማኝነት፣ በጎልጎታ የመስቀል ግርጌ ቢሆንም፣ እህቶችም አስተምረውኛል።

06 July 2023, 12:55