ፈልግ

በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ማጥፋት በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ማጥፋት  

ቤተ ክርስቲያን በሕክምና ድጋፍ ነፍስን ለማጥፋት በሚፈቅድ ሕግ ላይ ጥያቄ አቀረበች

በአውስትራሊያ የሲድኒ ከተማ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አንቶኒ ፊሸር በመዲናይቱ ከተማ ስድኒ ውስጥ በሕክምና ዕርዳታ በፈቃደኝነት የሚሞቱት ሰዎች የዕድሜ ገደብ ወደ 14 እንዲወርድ የሚለውን ሕግ በጽኑ ተችተውታል። የሲድኒ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አንቶኒ ፊሸር የአውስትራሊያ መዲና ሲድኒን የሚመለከተው አዲሱ የሕግ ማዕቀፍ ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው ሕጻናት በሕክምና ዕርዳታ በፈቃድ የሚፈጸም ግድያን እንዲቀበሉ የሚፈቅድ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ ሞትን ለሚመርጥ ለማንኛውም ሰው ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአውስትራሊያ ግዛት በሆነችው ሲድኒ ውስጥ በሕክምና ዕርዳታ በመታገዝ በፈቃድ ነፍስን ማጥፋት የተጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ጥር 31/2023 ዓ. ም. እንደ ነበር ሲታወስ ይህም ከደቡብ አውስትራሊያ፣ ከቪክቶሪያ፣ ከኩዊንስላንድ፣ ከታዝማኒያ እና በቅርቡ ሕጋዊ ከሆነበት ከኒው ሳውዝ ዌልስ ቀጥሎ እንደሆነ ታውቋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 1997 ዓ. ም. የወጣው የአውስትራሊያ፥ በሕክምና ዕርዳታ ነፍስን በፈቃድ የማጥፋት ወይም የ “ኤውታናሲያ” ሕግ ከተሻረ በኋላ በግዛቶች ዘንድ እንዲፀድቅ በአገሪቱ ፓርላማ መወሰኑ ይታወሳል። ሁሉም ግዛቶች ነፍሱን በፍላጎት ማጥፋት የመረጠ ግለሰብ ቢያንስ 18 ዓመት የሞላው እና በበሽታ ወይም በህመም የሚሰቃይ እና በራሱ ውሳኔ ለማድረግ አቅም ያለው መሆን እንዳለበት መስማማታቸው ይታወሳል።

በመዲናይቱ ስድኒ ውስጥ በሕክምና ዕርዳታ በፈቃድ የሚሞቱት ሰዎች የዕድሜ ገደብ ወደ 14 እንዲወርድ የተደረገው የሕግ ማዕቀፍ ሌሎች ግዛቶች ተግባራዊ ያደረጉትን ከ6 እስከ 12 ወራት ድረስ የሚጠበቀውን የሞት ጊዜን ውድቅ ማድረጉ ተመልክቷል። የታቀደውን የሕግ ማዕቀፍ በመምራት ላይ የሚገኙት የሲድኒ ከተማ ዙሪያ የሰብዓዊ መብት ሚኒስትር ታራ ቼይን ለአውስትራሊያ ማኅበራዊ መገናኛዎች እንደተናገሩት፥ ሕጻናትም እንደ አዋቂዎች ሕይወታቸውን በሕክምና ዕርዳታ በፈቃድ የማጥፋት ምርጫ ሊኖራቸው ይገባል ብለው፥ በተጨማሪም በማይድን በሽታ ለሚሠቃዩ የሌሎች የአውስትራሊያ ግዛቶች ሰዎች የሚሰጠውን መስፈርት በዘፈቀደ ውድቅ በማድረግ፥ ከስድስት እስከ 12 ወራት መቆየት በሚችሉ እና የአእምሮ ሕመም ላለባቸው ሰዎች ብቻ ዕድሉን ክፍት ማድረጋቸው ታውቋል።

በአውስትራሊያ የሲድኒ ከተማ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አንቶኒ ፊሸር በቀረበው ሃሳብ ላይ ጠንካራ ትችታቸውን አቅርበው፥ እውነታው በዓለም ዙሪያ የሚገኝ ማንኛውም ስልጣን ለኤውታናሲያ የሚሰጠው ፍርድ ቀስ በቀስ የሚቀር ከሆነ እንደ ሲድኒ ከተማ ክልል አስተዳደር ለሰው ልጅ ነፍስ ዝቅተኛ ግምት የሚሰጥ ከሆነ፣ ለሰው ልጅ ሕይወት ምንም ዓይነት ጥበቃ ሳይደረግለት ወደ ጉድጓድ ሊያመራ ይችላል" ብለዋል።

በአውስትራሊያ የሲድኒ ከተማ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አንቶኒ ፊሸር “የ14 ዓመት አዳጊ መኪና መንዳት እና መምረጥ የማይችል ሕጻን ተደርጎ የሚወሰድ ከሆነ የሕይወት ወይም የሞት ውሳኔን ለማድረግ ለምን አዋቂ ተደርጎ እንደተቆጠረ?” ብለዋል።

 

03 July 2023, 15:25