ፈልግ

እ.አ.አ. በ2022 በቱሪን ከተማ የተካሄደው የአውሮፓ ታይዜ ስብሰባ አርማ እ.አ.አ. በ2022 በቱሪን ከተማ የተካሄደው የአውሮፓ ታይዜ ስብሰባ አርማ 

ለታይዜ ማህበረሰብ ለመሪነት የተሾሙት አንግሊካኑ ወንድም

እንግሊዛዊው ተወላጅ የሆነው ወንድም ማቲዎስ በዚህ ዓመት በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ በፈረንሣይ የሚገኘውን የታይዜ ማህበረሰብ የገዳማውያን ቤተ ክርስቲያንን ቢሮ የሮማ ካቶሊክ የሆኑትን ወንድም አሎይስን በመተካት ይረከባሉ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የታይዜ ማህበረሰብ በታይዜ ፥ ሳኦኔ-ኤት-ሎየር በርገንዲ ፥ ፈረንሳይ ውስጥ ያለ ክርስቲያናዊ ወንድማማችነት ህብረት ገዳም ነው። ከዓለም ዙሪያ ወደ ሰላሳ ከሚጠጉ አገሮች የመጡ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑ ከመቶ በላይ ወንድሞችንም ያቀፈ ነው።
ወንድም አሎይስ ወደ እንግሊዝ የተመደቡ ሲሆን አንግሊካኑ ወንድም ማቴዎስ (የውልደት ስማቸው አንድሪው ቶርፕ) የታይዜ ማህበረሰብ ገዳም ቢሮውን እንዲረከቡ የበላይ መሪ ሆኖ ተሹመዋል።
በወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ፈረንሣይ ላይ የተመሠረተው ታዋቂው የታይዜ ማህበረሰብ ገዳም የለውጥ ሽግግሩ የሚከናወነው በመጪው ህዳር 23/ 2016 ዓ.ም. ነው።
የ69 ዓመቱ የጀርመን ሮማን ካቶሊክ ወንድም የሆነው አሎይስ እሳቸው ወደ ታኢዜ ማህበረሰብ ከመምጣታቸው በፊት የነበረው ታዋቂው እና መስራች የሆነው ሟቹ ወንድም ሮጀር (ሮጀር ሹትዝ) እ.አ.አ. በ2005 በአእምሮ ህመምተኛ ሴት በጩቤ ተወግተው መገደላቸው ይታወቃል።
ወንድም አሎይስ በሰጡት መግለጫ ለአሥራ ስምንት ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን “ዓለምና ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ብዙ ለውጦችን ካስተናገዱ እና ከእሳቸው በኋላ ወደ ማኅበረሰቡ የገቡት ወንድም ኃላፊነቱን የሚረከበት ጊዜ እንደደረሰ ተሰምቶኛል ብለዋል። በሹመቱም ሁኔታ ከአጋሮቻቸው ጋር ሰፊ ምክክር የተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቀጣይነት

የ58 ዓመቱ ወንድም ማቲዎስ ፥ እ.አ.አ. ህዳር 10 1986 ነው የታይዜን ማህበረሰብን የተቀላቀሉት።
ወንድም አሎይስ በሰጡት መግለጫ “አሁን የተሾሙት ወንድም የተቋሙን ቀጣይነትን እንደሚያስጠብቁ እና ማህበረሰባችን እንደ መስራቹ አስተሳሰብ ‘ትንሽ የኅብረት ምሳሌ’ እንዲሆን ለማነሳሳት ትክክለኛውን እርምጃ እንደሚወስዱ ሙሉ እምነት አለኝ” ብለዋል።

የታይዜ ማህበረሰብ

የታይዜ ማህበረሰብ በጸሎት እና በማሰላሰል ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን ጽኑ እምነት ያለው ገዳማዊ ሥርዓት ነው። በድህነት ፣ በንጽህና እና በመታዘዝ ላይ ተመስርተው ቃልኪዳን የገቡት የታይዜ ካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት መነኮሳት ለቁሳዊ እና መንፈሳዊ መጋራት ተሰጥተዋል።
ክርስቲያናዊ ህብረት፣ ጸሎት እንዲሁም ለሰላም እና ፍትህ ቁርጠኝነት
ሮጀር ሉዊስ ሹትዝ የተባለ የስዊዘርላንድ ፕሮቴስታንት መነኩሴ እ.አ.አ. በ1940 በታይዜ በርገንዲ ከተማ ማህበረሰቡን ካቋቋመ በኋላ የፈረንሳይዋ መንደር ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በዓለም ላይ ካሉት የክርስቲያን የአምልኮ ስፍራዎች አንዷ ሆናለች።
በየዓመቱ በበጋው ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ምዕመናን ከየዓለም ማእዘናት በማህበረሰቡ ጸሎት እና ጸጥታን ያማከለ የአኗኗር ዘይቤ ተደምመው ወደዚህ ሥፍራ ይጎርፋሉ ።
የቤኔዲክትን ወግ እና ባህል የሆነውን ኦራ እና ላቦራ (ፀሎት እና ስራ) በመከተል ሁሉም ጎብኚዎቹ በማህበረሰቡ ህይወት ውስጥ ሙሉ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቅባቸዋል።
ክርስቲያናዊ አኗኗር እና ህብረት የታይዜን መስህብ ቁልፍ ነገር ነው ፥ የተለያየ ባህል እና ወግ ያላቸውን ሰዎች ይስባል።
አንዳንድ ወንድሞች ለመካፈል እና ለመተሳሰብ ባላቸው ቁርጠኝነት የሚያሳይ ተጨባጭ ምልክት ሳብያ ፥ በዓለም ላይ እጅግ በተጨቆኑ እና በድሃ ህዝቦች መካከል መኖርን አስችሏቸዋል። ስለዚህም ዛሬ በአፍሪካ ፣ በእስያ፣ በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ ውስጥ እየሰሩ ይገኛሉ።

"በምድር ላይ የመተማመን ጉዞ"

እ.አ.አ. በ 1978 ማህበረሰቡም “በምድር ላይ የመተማመን ሃይማኖታዊ ጉዞ” የሚል ዓላማ ያለው ሃይማኖታዊ ጉዞን ጀመሩ። ይህ የወጣቶች አጠቃላይ ስብስብ የሆነው በሁሉም አህጉር ጉብኝት አድርጓል። እ.አ.አ. በታህሳስ ወር መጨረሻ በ1994 ከ100,000 በላይ የሚሆኑ ከመላው አውሮፓ የተውጣጡ ወጣቶች በፓሪስ ለአምስት ቀናት ለፀሎት እና ሃሳብን ለመጋራት ተገናኝተዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስብሰባዎቹ በየዓመቱ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 22 ባለው ጊዜ ትልቅ የአውሮፓ ከተማ ውስጥ ይካሄዳሉ።
ወንድም ሮጀር ከሞተ በኋላ በታተመው “ያልተጠናቀቀ ደብዳቤ” የሚል ፅሁፉ ፥ ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች “የሃይማኖት ጉዞ” እንዲስፋፋ ሐሳብ አቅርቧል። በዚህም ምክንያት በ1998 ዓ.ም. የህንድ ግዛት በሆነችው ኮልካታ ውስጥ የተጀመረው ለወጣቶች የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መካሄድ ጀምረዋል።
 

26 July 2023, 08:35