ፈልግ

የሐምሌ 02/2015 ዓ.ም የ13ኛ እለተ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የሐምሌ 02/2015 ዓ.ም የ13ኛ እለተ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ  (ANSA)

የሐምሌ 02/2015 ዓ.ም የ13ኛ እለተ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የእለቱ ንባባት

1.      2 መ. ነግሥት 4፡8-11፣ 14-16

2.     መዝ. 88

3.     ሮም 6፡3-4፣8-11

4.    ማቴዎስ 10፡37-42

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። መስቀሉን ተሸክሞ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም። ሕይወቱን ሊያድን የሚፈልግ ያጠፋታል፤ ሕይወቱን ስለ እኔ አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያገኛታል።

“እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።”

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡- “ነቢይን ነቢይ ስለ ሆነ የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል” (ማቴ 10፡41) ይለናል። ስለ ነቢይ ይናገራል፥ ነገር ግን ነቢይ ማነው? ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚተነብዩ እንደ ጠንቋይ የሚገምቱ ሰዎች አሉ፥ ይህ አጉል እምነት ነው፥ እናም ክርስቲያን እንደ አስማተኛ፣ የኮከብ ቆጠራ ወይም ተመሳሳይ ነገሮች ባሉ አጉል እምነቶች አያምንም። ሌሎች ደግሞ ነብይን የሚገልጹት ከክርስቶስ ልደት በፊት ስለ ክርስቶስ መምጣት አስቀድመው ሲተነብዩ የነበሩ ሰዎች እንደሆኑ አድርገው ይቆትራሉ። ሆኖም ኢየሱስ ራሱ ዛሬ ነብያትን ስለመቀበል አስፈላጊነት ተናግሯል፡ ስለዚህ አሁንም አሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ነብያት እነማን ናቸው?

ወንድሞቼ እና እህቶቼ እያንዳንዳችን ነብይ ነን፡ በእርግጥም በጥምቀት ሁላችንም የነብይነትን ተልእኮ ተቀብለናል (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁ.1268)። ነብይ በጥምቀት አማካኝነት ሌሎች በመንፈስ ቅዱስ ተግባር የአሁኑን ጊዜ እንዲያነቡ፣ የእግዚአብሔርን እቅዶች እንዲረዱ እና ከእርሱ ጋር እንዲዛመድ የሚረዳ ነው። በሌላ አነጋገር ኢየሱስን ለሌሎች የገለጸ፣ ስለእርሱ የሚመሰክር፣ ዛሬን ለመኖር እና ነገን በእቅዱ መሰረት ለመገንባት የሚረዳ እሱ ነብይ ነው። ስለዚህ እኛ ሁላችንም ነብያት፣ የኢየሱስ ምስክሮች ነን “ስለዚህ የወንጌል ኃይል በእለት ተዕለት ማህበራዊ እና በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ እንዲበራ” (ሉመን ጀነሲውም አንቀጽ 35)። ነቢይ እግዚአብሔርን ለሌሎች የሚያመለክት ሕያው ምልክት ነው፣ ክርስቶስ በወንድሞቹ እና እህቶቹ ጎዳና ላይ ያለው ብርሃን ነጸብራቅ ነው። እናም እራሳችንን እንጠይቅ ይሆናል፡- እኔ በጥምቀት “የተመረጥኩ ነቢይ” እናገራለሁ እና ከሁሉም በላይ የኢየሱስ ምስክር ሆኜ እኖራለሁ ወይ? በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ የእሱን ብርሃን ትንሽ አመጣለሁ? በዚህ ላይ ራሴን እፈትሻለሁ? እጠይቃለሁ፡ ምስክርኔቴ፣ ትንቢቴ እንዴት ነው?

በወንጌልም ጌታ ነቢያትን እንድንቀበል ይጠይቀናል፣ ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር መልእክት ተሸካሚ፣ እያንዳንዱ እንደየ ግዛቱ ወይም እንደ ጥሪው፣ እኛም በምንኖርበት አካባቢ፣ በቤተሰብ፣ በቤተክርስቲያን፣ በሃይማኖታዊ ማኅበረሰቦች መካከል እንደ እግዚአብሔር መልእክት ተሸካሚዎች መሆናችንን መቀበል አስፈላጊ ነው። በሌሎች የቤተክርስቲያኒቷ እና የህብረተሰቡ አካባቢዎች ጭምር ማለት ነው። መንፈሱ የትንቢትን ስጦታ በቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች ላይ አሰራጭቷል፡ ስለዚህ ሁሉንም ማዳመጥ ጥሩ ነው። ለምሳሌ አንድ አስፈላጊ ውሳኔ መደረግ ሲገባው፣ በመጀመሪያ መጸለይ፣ መንፈስን መጥራት፣ ነገር ግን ማዳመጥ እና መነጋገር ጥሩ ነው፣ ሁሉም ሰው፣ ትንሹም ቢሆን፣ የሚናገረው ጠቃሚ ነገር እንዳለው በመተማመን፣ ለመካፈል ትንቢታዊ ስጦታ ያስፈልጋል። በዚህ መንገድ እውነትን በመፈለግ አምላክን እንዲሁም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የምንሰማበት ሁኔታን እናስፋፋለን፤ በዚህ ጊዜ ሰዎች የምንወደውን ነገር ሲናገሩ ብቻ ተቀባይነት አይኖራቸውም፥ ነገር ግን ለእነሱ እንደ ስጦታ ተደርጎ እንደሚቆጠር የሚሰማቸው ሰዎች አሉ።

በዚህ መንገድ ምን ያህል ግጭቶችን ማስወገድ እና መፍታት እንደሚቻል አስቡ፥ እርስ በርስ ለመረዳዳት ከልብ በመፈለግ ሌሎችን በማዳመጥ! በመጨረሻም ራሳችንን እንጠይቅ፥ ወንድሞችንና እህቶችን እንደ ትንቢታዊ ስጦታዎች እንዴት መቀበል እንዳለብኝ አውቃለሁ ወይ? እንደምፈልጋቸው አምናለሁ ወይ? ለመማር ባለው ፍላጎት፣ በአክብሮት አዳምጣቸዋለሁ ወይ? ምክንያቱም እያንዳንዳችን ከሌሎች የምንማረው ነገር አለን።

መንፈስ ቅዱስ በሌሎች ላይ የዘራውን በጎ ነገር እንድናይ እና እንድንቀበል የነቢያት ንግሥት ማርያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

 

08 July 2023, 12:12