ፈልግ

በሰሜን ኢራቅ ካራምሌሽ የሚገኘው የማር አድዳይ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ኢራቅ ካራምሌሽ የሚገኘው የማር አድዳይ ቤተ ክርስቲያን  (AFP or licensors)

ለጥንታዊቷ ምስራቃዊት ቤተክርስቲያን አዲስ ፓትርያርክ ተሾመላት

ከጥንት የክርስትና አመጣጥ ጋር የሚቆራኘው ፥ ጥንታዊቷ የምስራቅ ቤተክርስትያን ማር ጆርጅ ዮናን ሳልሳዊን ፓትርያርክ አድርጋ በመሾም እያከበረች ትገኛለች።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
ማር ጆርጅስ ሳልሳዊ ባለፈው ሰኔ 2 2015 ዓ.ም. ዕለተ አርብ በባግዳድ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት የምስራቅ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል።
የምስራቅ ጥንታዊት ቤተክርስትያን እ.አ.አ. በ1960ዎቹ ከአሦራውያን ቤተክርስቲያን ተለይታ ለብቻዋ ወጥታ ነበር። ሁለቱም ቤተክርስቲያናት የጥንት የክርስትና እምነት ተከታዮች በአንድ ወቅት በመላው እስያ ከኢራን እስከ ህንድ አልፎም እስከ ቻይና የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች የነበሯቸው እና ከጥንታዊ የምስራቅ ቤተክርስቲያን የዘር ግንዶች ጥንታዊነት ይገባኛል በሚል ይፎካከሩ እንደነበር ይታወቃል።
ዛሬ ተከታዮቻቸው በዋናነት በኢራቅ እንዲሁም በተለያዩ ሃገራት የኢራቅ ዲያስፖራ ሆነው ይገኛሉ።
ከሮማው ቤተክርስቲያን ጋር ህብረት ያላት እና የምስራቅ ቤተክርስቲያን ቅርንጫፍ የሆነቺው የከለዳውያን ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ፓትርያርክ ሉዊስ ሳኮ ፥ የፓትሪያርክ ማር ዮናንን ሹመትን ተከትሎ ጎብኝተዋቸዋል ፥ እንዲሁም ‘ፍሬያማ’ የስልጣን ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል።
በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ካሉት እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ የክርስቲያን ማህበረሰቦች አንዱ የሆኑት በኢራቅ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ፥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መድልዎ እና ሽብርተኝነትን ጨምሮ ከባድ ፈተናዎች ገጥሟቸዋል። የቤተክርስቲያኑ መሪዎች ሁኔታው ካልተስተካከለ በስተቀር ማህበረሰባቸው የመጥፋት አደጋ እንደሚደርስባቸውም አስጠንቅቀዋል።
 

14 June 2023, 15:31