ፈልግ

የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም  

የሰኔ 11/2015 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የእለቱ ምንባባት

1.       ዘጸሐት 8፡2-3.14-16

2.     መዝሙር 147

3.     1ቆሮንጦስ 10፡16-16

4.     ዩሐንስ 6፡51-58

የእለቱ  ቅዱስ ወንጌል

እርሱም ተቀብሎአቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው። ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለ ነው በምድረ በዳ ስለ ሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት። እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተው ስጧቸው” አላቸው።እነርሱም፣ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ሄደን ካልገዛን በስተቀር፣ እኛ ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ አይበልጥም” አሉት፤ አምስት ሺህ ያህል ወንዶች በዚያ ነበሩና።

ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሕዝቡን በአምሳ በአምሳ ሰው መድባችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም በታዘዙት መሠረት ሰዎቹ እንዲቀመጡ አደረጉ። እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ ባረካቸው፤ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእነርሱ የተረፈውን ቊርስራሽ እንጀራ ዐሥራ ሁለት መሶብ አነሡ። (ሉቃስ 9፡11-17)

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በጣሊያን እና በሌሎች ሀገራት የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም የሚታወስበት በዓል ተከብሮ ውሏል። በመጨረሻው እራት ወቅት የተቋቋመው፣ ቅዱስ ቁርባን የጉዞው መድረሻን ይመስላል፣ ኢየሱስ በብዙ ምልክቶች ተመስሏል፣ ከሁሉም በላይ በዛሬው የቅዳሴ ወንጌል ውስጥ የተነገረው ኢየሱስ በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ አምስት ሺህ ሰዎችን የመገበበት ሁኔታ እናያለን (ሉቃ. 9፡11-17)። ኢየሱስ ቃሉን ለመስማትና ከተለያዩ ክፉ መንፈስ ለመገላገል የተከተሉትን እጅግ ብዙ ሰዎች ይንከባከባል። አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ ባረከ፣ ቈርሶም ደቀ መዛሙርቱ በመስጠት እንዲያከፋፍሉት አደረገ፣ እናም “ሁሉም በልተው ጠገቡ” (ሉቃ. 9፡17) ይላል የዛሬ ቅዱስ ወንጌል። በቅዱስ ቁርባን ውስጥ፣ ሁሉም ሰው ይህን የጌታን አፍቃሪ እና ተጨባጭ ትኩረት ሊለማመዱ ይችላሉ። የክርስቶስን ሥጋና ደም በእምነት የሚቀበሉ መብላት ብቻ ሳይሆን ይጠግባሉ። ለመብላትና ለመርካት፡- በቅዱስ ቁርባን ሁለት አስፈላጊ ነገሮች ይጠግባሉ።

መብላት። “ሁሉም በልተዋል” ሲል ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል። በመሸ ጊዜ የደቀመዛሙርቱ ሸንጎ ኢየሱስ ሕዝቡን በማሰናበት ምግብ ፍለጋ እንዲሄዱ እንዲያደርግ ጠየቁ። ነገር ግን መምህሩ ለእነዚያም ሰዎች ምግብ ለማቅረብ ይፈልጋል - እርሱን ያዳምጡት የነበሩትንም መመገብ ይፈልጋል። የእንጀራውን እና የዓሣው ተአምር በአስደናቂ ሁኔታ ሳይሆን የተከሰተው ነገር ግን በሚስጥር ማለት ይቻላል በዚህ መልኩ ነበር የተከሰተው፣ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ እንደ ተከሰተው - እንጀራው ከእጅ ወደ እጅ ሲሸጋገር መጠኑ እየጨመረ ሄዷል። ሕዝቡም ሲበሉ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር እንደሚንከባከበው ተገነዘቡ። ይህ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ያለው ጌታ ነው። የሰማይ ዜጎች እንድንሆን ጠርቶናል፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ፣ እዚህ ምድር ላይ የምንገጥመውን ጉዞ ግምት ውስጥ ያስገባል። በመሶቤ ውስጥ ምንም እንጀራ ከሌለኝ እርሱ ራሱ ያውቃል እና ይንከባከበኛል።

አንዳንድ ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን ግልጽ ባልሆነ መንገድ ራቅ አድርገን በተመለከትን ቁጥር ምናልባትም ብሩህ እና በዕጣን የታወጀ አድርገን ቢቻ በምንመለከትበት ወቅት ከዕለት ተዕለት ሕይወት ችግሮች የራቀ የመገደብ አደጋ አለ። እንደ እውነቱ ከሆነ ከሁሉም መሠረታዊ ነገሮች ጀምሮ ጌታ ፍላጎታችንን ሁሉ ወደ ልባችን ያስገባል። ለደቀ መዛሙርቱም “የሚበሉትን ስጡአቸው” (ሉቃስ 9፡13) እንዳለው ሁሉ በቀን ሲያዳምጡት ለነበሩት ሰዎች ምሳሌ ሊሰጣቸው ይፈልጋል። የቅዱስ ቁርባንን ስግደት መመዘን የምንችለው ኢየሱስ እንደሚያደርገው ባልንጀራችንን ስንከባከብ ነው። በዙሪያችን የምግብ ረሃብ አለ ግን ደግሞ ጓደኝነት፣ የመጽናናት፣ የፍቅር እና የጥሩ ግንኙነት ረሃብ አለ፣ ትኩረትን የሚስብ ረሃብ አለ፣ እናም ቅዱስ ወንጌል ለመስበክ ረሃብ አለ። ይህንን በቅዱስ ቁርባን እንጀራ ውስጥ እናገኛለን - ለፍላጎታችን የክርስቶስ ትኩረት እና ከጎናችን ላሉትም እንዲሁ እንድናደርግ የቀረበልን ግብዣ ነው። ሌሎችን መመገብ እና መንከባከብ አለብን።

ከመብላት በተጨማሪ ግን እርካታን መርሳት አንችልም። ሕዝቡ በተትረፈረፈ ምግብ ምክንያት እንዲሁም ከኢየሱስ የተቀበለው ደስታና መገረም ረክቷል! በእርግጥ እራሳችንን መመገብ አለብን፣ ነገር ግን እርካታም ያስፈልገናል፣ ምግቡ የሚሰጠን በፍቅር መሆኑን አውቀን መቀበል አለብን። በክርስቶስ ሥጋ እና ደም ውስጥ፣ የእርሱን መገኘት፣ ህይወቱ ለእያንዳንዳችን ተሰጥቷል። ወደ ፊት እንድንሄድ የሚረዳን ብቻ ሳይሆን እራሱንም ይሰጠናል - እራሱን የጉዞ አጋራችን ያደርጋል፣ ወደ ጉዳያችን ይገባል፣ ብቻችንን ስንሆን ይጎበኘናል፣ የጋለ ስሜት ይመልሰናል። ይህ ጌታ ለህይወታችን፣ ለጨለማዎቻችን እና ለጥርጣሬዎቻችን ትርጉም ሲሰጥ ያረካናል። ትርጉሙን ያያል ይህ ደግሞ ጌታ የሚሰጠው ትርጉም ያረካናል። ይህ ሁሉም ሰው የሚፈልገውን "የበለጠ" ይሰጠናል - ማለትም የጌታ መገኘት! በእርሱ መገኘት ሙቀት ሕይወታችን ይለወጣልና። ያለ እሱ ሁሉም ነገር በእውነት ግራጫ ይሆናል። የክርስቶስን ሥጋና ደም እያከበርን፣ “ጌታ ሆይ፣ ወደፊት የምሄድበትን የዕለት እንጀራ ስጠኝ፣ ጌታ ሆይ፣ ፊትህን አጥግበኝ!” ብለን በልባችን እንጠይቀው።

ድንግል ማርያም ለኢየሱስ እንዴት እንደምንሰግድ እንድታስተምረን፣ በቅዱስ ቁርባን እንድንኖር፣ እርሱንም ለወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል ትረዳን ዘንድ አማላጅነቷን እንማጸን።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 12/2014 ዓ.ም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም የሚከበርበት አመታዊ በዓል ላይ ካደረጉት ስብከት የተወሰደ።

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

 

17 June 2023, 16:08