ፈልግ

2019.03.28 ቤት አልባ የሆነች ሴት 2019.03.28 ቤት አልባ የሆነች ሴት 

‘ሥነ ምግባራዊ የታሪክ አገላለጽ’፡- በችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ክብር ለመጠበቅ የሚነገርበት መንገድ

በአሜሪካ የባልቲሞር ከተማ ሲደረግ የነበረው የካቶሊክ ሚዲያ ኮንፈረንስ ሲጠናቀቅ ዶሺማ ትሴ እንዳሳሰቡት የካቶሊክ ጋዜጠኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች እና ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ታሪክ ሲዘግቡ በአክብሮት እንዲናገሩ መክረዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
የካቶሊክ ሚዲያ ባለሙያዎች ከግንቦት 29 - ሰኔ 2 2015 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ ከተማ በሆነቺው ባልቲሞር ውስጥ ዓመታዊ የካቶሊክ ሚዲያ ኮንፈረንስ አድርገዋል።
ከመላው አሜሪካ የተወጣጡት የካቶሊክ ዘጋቢዎች እና አርታኢዎች ተገናኝተው ሃሳቦችን ከመለዋወጣቸው በተጨማሪ ፕሮፌሽናል የታሪክ አወቃቀርን እና ሥነ ምግባራዊ የታሪክ አነጋገር ዘይቤን የማወቅ ዕድል በማግኘታቸው ደስተኞች ሆነዋል።
የደቡባዊ አፍሪካ የካቶሊክ የዕርዳታ አገልግሎት ክልላዊ መረጃ ኦፊሰር የሆኑት ዶሺማ ትሴ ፥ የምዕራባውያን ሚዲያዎች የቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት ጥረቶች መጨረሻ ላይ እንዴት የሰዎችን ታሪክ በተሻለ መንገድ መናገር እንደሚችሉ ግንዛቤ የሚሰጥ ኮርስ ሰጥተዋል።
የካቶሊክ የዕርዳታ አገልግሎቶች (CRS) በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የካቶሊክ ማህበረሰብ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ዕርዳታ ድርጅት ሲሆን የካሪታስ ኢንተርናሽናሊ ፌደሬሽን አባልም ጭምር ነው።
በካቶሊክ ዘገባ ውስጥ የሰውን ክብር ማክበር
ወይዘሮ ትሴ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፥ ሥነ ምግባራዊ የታሪክ አነጋገር ዘይቤ ማለት ድህነትን ወይም የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከማወደስ ይልቅ ታሪካቸውን በመናገር የሰዎችን ሰብዓዊ ክብር ማክበር ማለት ነው። “ሥነ ምግባራዊ የታሪክ አዘጋገብ ዘይቤ በተለይ ለካቶሊክ ሚዲያዎች ጠቃሚ ነው ፥ ምክንያቱም እንደ ካቶሊኮች እነዚህ የመመሪያ መርሆች ስላሉን የሰውን ክብር እናከብራለን እንዲሁም አብረናቸው የምንሠራቸውን ሰዎች እና የምናገለግላቸውን ማህበረሰቦችን እናከብራለን” ሲሉም ተናግረዋል።
ወይዘሮ ትሴ አክለውም “ሥነ ምግባራዊ የታሪክ አዘጋገብ ማለት በፍትሃዊነት ላይ አተኩሮ ስለ ሰዎቹ ችግር መናገር እንጂ የሰዎቹን ግላዊ ክብር በሚነካ መልኩ መዘገብ ማለት አይደለም” ብለዋል። የካቶሊክ ጋዜጠኞች በአጠቃላይ በባለ ታሪኩ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን በማረጋገጥ መለያየትን ወይም ኢፍትሃዊነትን እንዳያሰፍኑ መጠንቀቅ አለባቸው ብለውም አሳስበዋል።
በሁኔታዎች ሳይሆን በሰዎች ላይ አተኩር
ወይዘሮ ትሴ በኮንፈረንሱ ላይ ባቀረቡት ገለጻ የኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ ያለባቸውን ሰዎች የሚያገለግል ፕሮግራም የሚያሳይ የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ በምሳሌነት አቅርበዋል።
እርዳታውን በሚሰጡ ሰዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ ፥ ከሥነ ምግባር አኳያ የተፃፈው ዘገባ እርዳታውን የሚቀበሉትን ሰዎች እንደ ገላጭ የታሪክ ባለጉዳዮች ገልፆ ታሪካቸዉን መዘገብ አለበት።
“ሰዎችን መለያ መስጠት ወይም በሁኔታቸው ወይም አሁን ላይ በሚገኙበት ሁኔታ ልንገልጻቸው የለብንም ፥ አሁን ያሉበት የችግር ሁኔታ ምን እንደሆነ እና እንዴት ለጉዳዩ ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ 360-ዲግሪ እይታን የሚያሳዩ ታሪኮችን መዘገብ አለብን” ብለዋል።
ወ/ሮ ትሴ በመቀጠል “ይህ የታሪክ አዘጋገብ ሰዎቹ ያላቸውን ክብር እና ጽናት እንዲሁም ላሉበት ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት ያደረጉትን ጥረት ያሳያል” ብለዋል።
ክብር እና ማንነትን መጠበቅ
በማጠቃለያውም ወይዘሮ ትሴ እንደተናገሩት ፥ የካቶሊክ ሚዲያ ባለሙያዎች የሚዘግቡትን ሰዎች ክብር እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
ለምሳሌም ዘገባዎችን ስንሠራ የቃላት አጠቃቀም ላይ እንደ ‘ድሆች’ ወይም ‘የአእምሮ በሽተኞች’ ያሉ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ ፥ ሥነ ምግባራዊ ዘጋቢዎ የባለታሪኮቹን በቀላሉ የማይታዩ ስሜቶቻቸውን የሚገልጽ እና ጽናታቸውን ማሳየት የሚችል ዘገባ መስራት አለባቸው ብለዋል።
 

12 June 2023, 16:30