ፈልግ

በፊሊፒንስ የ ‘ንፅህት ልበ ማሪያም’ ሚስዮናዊያን ማኅበር እህት በማስተማር አገልግሎት ላይ በፊሊፒንስ የ ‘ንፅህት ልበ ማሪያም’ ሚስዮናዊያን ማኅበር እህት በማስተማር አገልግሎት ላይ 

የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የሆኑ ህፃናትን እና ወጣቶችን ማስተማር እንደሚገባ ተገለጸ

የፊሊፒና ሐዋርያዊ ተልዕኮ አማካሪ የሆኑት ሲስተር አጉስቲናዳ ኦውኖ ፥ ሰዎች የካቶሊክ እምነትን እንዲቀበሉ እና ድሃ ልጆችን ፥ በተለይም ምንም ከሌላቸው ቤተሰቦች የመጡ እና በአደንዛዥ እፅ የተጠቁ ልጆችን እንዲያስተምሩ ፣ መንፈሳዊ እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና ወደ ክርስቶስ እንዲመሩ ጥሪ አድርገዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በፊሊፒንስ የ ‘ንፅህት ልበ ማርያም’ ሚስዮናዊያን (LIHM) ሐዋርያዊ አማካሪ የሆኑት ሲስተር ቴሬሳ አጉስቲናዳ ኦዋኖ ፥ ማህበረ ቅዱሳኑ በወጣቶች እና ቤተሰቦች አቅም ግንባታ ላይ እንዲሁም በትምህርት ላይ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሆነ በመግለጽ ፥ ስለ ማህበረ ቅዱሳኑ አመሰራረት ሲገልፁ “የእኛ ጉባኤ በፊሊፒንስ በግሪጎሳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1991 በይፋ የተመሰረተ ሲሆን ወጣቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመስበክ እና ለማቋቋም እንተጋለን” ሲሉም ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።

ይህ ጉባኤ ሰዎች የወንጌል አገልግሎት ማግኘት እንዳለባቸው እና ይህም አግባብነት እንዳለው እንደሚያምን ተናግረዋል። ሲስተር ኦዋኖ አክለውም “ወጣቶችን ወንጌልን በመስበክ የምናሳየው በጎ ተግባር ቀጣይነት ባለው የሃዋሪያዊ ትምህርት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፣ ወርሃዊ አደረጃጀት ፣ መዝናኛ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች በኩል ይካሄዳል” ሲሉም ገልጸዋል። ሲስተሯ የ ‘ንጽህት ልበ ማርያም’ መነኮሳት ስራዎች የሚመነጩት ካላቸው የበጎ ሥራ ጸጋዎቻቸው የተገኘ ተግባር መሆኑንም ገልፀው ነበር። “የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ በተቋሙ በወጣቶች ላይ በሚደረግ የወንጌል አገልግሎት በተለይም በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ፣ በቤተሰቦች እና አጥቢያዎች በታማኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ እና በማርያም ልብ ፍቅር በኩል እየተፈጸመ ቀጥሏል” በማለት ቀጥለውም “ለቤተክርስቲያኒቱ ፍላጎቶች ከተልዕኮቻችን ጋር በሚስማማ መልኩ ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።

“እያንዳንዳቸው የጉባኤው ደናግላን በትህትና እና በደስታ ይህንን ስጦታ ይቀበላሉ ፥ ይህም መከራዎቻችንን እና መስዋዕቶቻችንን በማቅረብ በቤተክርስቲያን ውስጥ የክርስቶስ የማዳን ስራ እርሾ እንድንሆን ነው የተጠራነው” ሲሉ ሲስተር ኦዋኖ ተናግረዋል። በመሆኑም ሁሉም መነኮሳት በልግስና እና በትህትና ልባቸውን ክፍት አርገው እንደሚሰሩ አፅንዖት ሰጥተውበታል። “የተልዕኮ ማህበሩ የሌሎችን ስቃይ ይካፈላል ፥ እነዚህን ስቃዮች ወደ ፍቅርም ይለውጣል” በማለትም አክለውበታል። የካቶሊክ እምነትን የማስፋፋት ተልእኳቸው ጠቃሚ እንደሆነም በማብራራት ፥ እግዚአብሔር እንደሚቀጥል ብቻ ሳይሆን በእኛም የጀመረውን የለውጥ ሥራ እንደሚጨርስ የገባውን ቃል በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።

ሲስተር ኦዋኖ በተጨማሪም “የዚህ ጉባኤ ገዳማዊያን የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር በመኖር እንዲሁም አርአያ በመሆን ፥ የምሥራቹን መልካም ዜና ለዓለም በማስፋፋት ረገድ እምነታቸውን በመሆን የሚያሳዩ የማህበረ ጉባኤውን ተልእኮ ሙሉ በሙሉ በመገንዘብ እንደሚኖሩም ገልፀዋል። የማህበረ ቅዱሳኑ ሐዋሪያዊ አማካሪ በተጨማሪም “ጉባኤው ሌሎች በዚህ ፈታኝ ዓለም ውስጥ የኢየሱስን ፊት እንዲመለከቱ ለማበረታታት ጥረት ያደርጋል” ብለዋል።

የካቶሊክን ትምህርት ማስተማር

ሲስተር ኦዋኖ የካቶሊክ ትምህርት ለወጣቶች አስፈላጊነት እና ያለውን ጥቅም አፅንዖት ሰጥተው ሲናገሩ ፥ “የተማሪዎችን ፣ መምህራንን ፣ የትምህርት ቤት ርእሰ መምህራንን እና የትምህርት ቤት ኃላፊዎችን ሥነ ምግባራዊ እና መንፈሳዊ ክህሎት ለማዳበር ከትምህርት ክፍል ፕሮግራም ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል። ፊሊፒናዊቷ ሲስተር ኮዋኖ ማህበራቸው “በተለይ የክርስትና እምነት ትምህርቶች በመደበኛነት በማይሰጥባቸው የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ወጣቶችን በማስተማር እና በመርዳት ላይ እንዳለ ተናግረዋል። “አብዛኞቹ ምንም ከሌላቸው ቤተሰቦች የመጡ በመሆናቸው ለወጣት ተማሪዎቻችን በሥነ ምግባራዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሁኔታ የመርዳት ኃላፊነት አለባቸው” ሲሉም ገልጸዋል።

ሲስተሯ በመቀጠልም ልጆችን በማስተማር ረገድ የጉባኤውን ሚና ሲናገሩ ፥ “በትምህርት ቤት በየቀኑ ማለት ይቻላል ከተማሪዎቹ ጋር ስለምንገናኝ እነሱን ለመርዳት የተሻለ ሁኔታ ላይ እንሆናለን ፥ እንዲሁም ብዙዎቹ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና እናታችን ድንግል ማርያምን ስለማያውቁ በአደንዛዥ ዕፅ እና በመጥፎ ጓደኞች ተጽዕኖ ውስጥ ይገባሉ ፥ በመሆኑም ከዚህ የተሻለ ነገር ፥ ከአደንዛዥ ዕፅ ማለታቸው ነው ፥ አያውቁም ምክንያቱም በዚህ ረገድ ወላጆቻቸው እንኳን ሳይቀሩ በሕይወታቸው ውስጥ የበለጠ ትርጉም ያለው እና የተሻለ ነገር እንዲያደርጉ ማንም አይነገራቸውም እንዲሁም አይመራቸውም” ብለዋል። ስለዚህ ይህን ክፍተት ለመሙላት ልጆቻቸው እንዲጸልዩ ፣ እግዚአብሔርን እንዲሰሙ እና ከጥሪውም እንዳይርቁ ለማበረታታት ወላጆችን ከቤት ወደ ቤት በመስበክ ከወላጆች ጋር እንደሚነጋገሩም ጨምረው ተናግረዋል።

ሲስተር ኦዋኖ የጉባኤው አጋዦች ለልጆቹ መገልገያዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል ምክንያቱም አብዛኞቹ ህጻናት የመጡት ከመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስለሆነ እና ድሆችም ጭምር ስለሆኑ የት/ቤት ክፍያዎቻቸውን እና ሌሎች ፍላጎቶቻቸውን መክፈል ስለማይችሉ ነው ብለዋል። በተጨማሪም አንዳንድ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሚገባ ተምረው በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ውጪ ጎበዝ ተማሪዎች እና ካቶሊኮች ለመሆን ጥረት አድርገዋል” ሲሉም ተናግረዋል።

ሲስተሯ በመቀጠል “የገዳማዊያን ማህበሩ ወጣቶችን በሃይማኖታዊ ሕይወት ውስጥ እንዲሳተፉ እና እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ ይስባል” ብለው ፥ “ወጣቶች ደፋር ፣ ጎበዝ ፣ ጽኑ እና ጥልቅ ስሜት ያላቸው ፣ ዓለምን ለመቀየር በቂ እንደመሆናቸው መጠን ፥ ሁሉንም ችሎታቸውን እና ቅንነታቸውን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲጠቀሙ በማስገደድ ኃይላቸውን ወደ በጎ እና መልካም ህይወት ለመቀየር ይጥራል” ብለዋል።

ትውልደ ፊሊፒናዊቷ ሲስተር “ይህ ጉባኤ በተማሪዎቻቸው መካከል ክርስቲያናዊ በጎነቶችን እና እሴቶችን ያስተላልፋል ፤ ሁሉንም ሰው ለመድረስ እና ለማስተማር ሁሉን አቀፍ ፣ አጠቃላይ እና አውዳዊ አቀራረቦችን ይጠቀማል” በማለት ስለ ትምህርት አሰጥጡ አብራርተዋል። አክለውም “ከወጣቶች ጋር አብረው አንዳንዴ እንደሚጓዙ እና እንደሚነጋገሩ ፥ በቆይታቸውም ጌታን እና ህዝቡን በሙሉ ልባችን ማገልገል ታላቅ ክብር እና ደስታ እንደሆነ እንደሚነግሯቸውም ጠቁመዋል። የማህበሩ ገዳማዊያን ህይወት በተለይ ወጣቶች የንጽህና እና የጥሩነት ህይወትን በመቀበል የሰውን ልጅ ህይወት እና ክብር እንዲወዱ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሃይማኖታዊ ሴቶች

ሲስተር ኦዋኖ ማህበረ ቅዱሳኑ ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደ እናታችን እንደሚገነዘበው በመግለጽ ‘በሁሉም ነገር ላይ እንደ መሪያችን እና አነሳሻችን አድርገን ነው የምናያት’ ብለዋል። አክለውም “እያንዳንዱ የማህበሩ መነኮሳት የተባረከችዋ ቅድስት ድንግል ማሪያም በሕይወቷ ውስጥ ያቀረበችውን ጸጋ ወይም አርአያነት ለማግኘት ይጥራሉ” ብለዋል። ሲስተር ኦዋኖ በ21 ዓመት አገልግሎታቸው ውስጥ ማህበረ ቅዱሳኑ ሴቶችን ቤተክርስቲያንን በማገልገል ዉስጥ አሳታፊ እንዲያደርግ ለማድረግ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ሲስተሯ ሴቶችን “ለቅድስና ህይወት እጅ እንዲሰጡ እና እግዚአብሔር ጥሪውን በእኛ ውስጥ እንደተከለ እና ህይወታችንን በሚያምር ሁኔታ እንደሚለውጠው እንዲያምኑም” ጋብዘዋል።

አክለውም ‘ገዳማዊያኑ አምላክን በማያልቀው ሁለንተናዊ ፍቅር ማገልገላቸውን እንደሚቀጥሉበት እንዲሁም በታማኝነት ህዝቡን በማገልገል እንደሚቀጥሉ ተናግረው ፥ ለእያንዳዱ ፍጡር በታማኝነት እንጸልያለን ፥ለነፍሶች ደህንነትም እንሰራለን ፥ ይህ የእኛ አንዱ አካል ሆኗል ፥ ይህ የሁሉም የገዳማዊያን የአኗኗር ዘይቤ ነው” በማለት በመጨረሻም “ሰዎች ሌሎችን እንዲያነሳሱ እና ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ የመስጠትን ሃላፊነትን እንዲወስዱ በማበረታታት ቃለ መጠይቁን ቋጭተዋል ሲስተር ቴሬሳ አጉስቲናዳ ኦዋኖ።

06 June 2023, 16:26