ፈልግ

ማሪያ ሊያ ዜርቪኖ እና የሥራ ባልደረቦቿ ማሪያ ሊያ ዜርቪኖ እና የሥራ ባልደረቦቿ  

የማይታዩ (In-Visibles) ፡- የማይታዩ ሴቶችን እንዲታዩ ለማድረግ የሚረዱ ሴቶች

የማይታዩ ሴቶች እንዲታዩ ማድረግ የሚል ኢንቪዝብል (In-Visibles) የተሰኘ የ30 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን ሮም ውስጥ በሚገኘው የዓለም የካቶሊክ የሴቶች ድርጅቶች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚታይ ታውቋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ኤያ ሃግኖን (የአለባበስ ባለሙያ) አግነስ ሶክፖ (ሪፍሌክስሎጂስት) ቤኔዲክታ ሶክፖ (የሥ ልቦና ባለሙያ) ክርስቲን ኑሜቱ (የኬክ ባለምያ) ርብቃ አማ አግቦሊ (የኬክ ባለሙያ) ማማቱ አኩፖ ሶቶንጂ (የሺያጭ ሰራተኛ) ዶርካስ ፍሉር ክፖዶ (የሕፃናት ማሳደጊያ መስራች) ኖሊን ኢዛን አኮሲዋ (የተማሪዎች ፀጉር አስተካካይ) እና በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ሌሎች ብዙ ሴቶች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ? አዎ የመረሳት ወይም የመተው የጥቃት የብቸኝነት እና የሥራ አጥነት ስሜት ይሰማቸዋል። ይህ ግን በእነዚህ ሴቶች አልሆነም ምክንያቱምማሪያም የቤተክርስቲያ እናትየሚባሉት ገዳማዊያን አካል የሆነውየእግዚያብሄር ጥበቃ ገዳማዊያንእህቶች ማህበር እንዲውም የሌሎች ተቋሞች ገዳማዊያን ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ እነዚህ ሴቶች አሁንም ይተዋሉ ብቸኝነት ይሰማቸዋል ስራ አጥ ይሆናሉ።

ይህንን ነው In-Visibles የተባለው 30 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም የማይታዩትን እንዲታ አድርጎ ማሳየት የፈለገው።

 በሮም በሚገኘው የዓለም የካቶሊክ የሴቶች ድርጅቶች ህብረት (WUKWO) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቅዳሜ ጠዋት በሮም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ ዘጋቢ ፊልም ይታያል የዚህ ተቋም ፕሬዝዳንት ንዲሁም ለም የሴቶች ተቋም የሆነው World Womens Observatory (WWO) ዳይሬክተር የሆኑት ማሪያ ሊያ ዜርቪኖ ለቫቲካን ዜና እንደተናገሩት ኢን-ቪስብልስ ለም የሴቶች ተቋምን (WWO) ተልዕኮ የሆነውና በውቅያኖስ ውስጥ የሰመጡትን የማይታዩ ሴቶችን ማሳየትግቡ ያደረገ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስዓለም አቀፋዊ ችላ ባይነትያሉትን ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚተጋ ሲሆን ለዚህም ገዳማዊያንን ማሰማራት እንፈልጋለንብለዋል ሲስተሯ።

 

ይህ ተቋምሴቶች በአፍሪካ በፆታዊ ጥቃት ምክንያት ስለሚሰቃዩት ነገር ግንዛቤን ለማሳደግ የተሻለው መንገድ በቦታው ላይ ፊልም መስራት እንደሆነ ወስነን ነው ሥራ የጀመርነው ስትል ማሪያ ሊያ ገልጻለች። በማከልምጥበብ እራሳችንን ለሌላ እውነታ የምንከፍትበት እየሆነ ስላለው ነገር የምንገነዘብበት በስቃይ ላይ ያሉ ሴቶች ሁኔታ እና ልምድ የምንረዳበት ነገር ግን አሁን ከዛ የህይወት ውጣ ውረድ አገግመው በኢኮኖሚያዊ አቅም ራስን በራስ በማስተዳደር ቤተሰብ ለመመስረት ብሎም ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ያስቻላቸውን ሁኔታ የምናስተውልበት ቀላሉ መንገድ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው ይላሉ ሲስተሯበገዳማዊያን በማኅበረ ቅዱሳን እና በምእመናን እርዳታ ነው ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባቸዋልብለዋል።

 ወርልድ ውሜን ኦብዘርቫቶሪ የአውሮራ ቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለሆነችዋ ለሊያ ቤልትራሚ ይህን ዘጋቢ ፊልም እንድታዘጋጅ ሃላፊነት ሰጥቷታልየሥራው ዕቅድ እንደደረሰኝ ሃሳቡን ወደድኩት ምክንያቱም ይህ ከህይወት ተመኩሮዬ አንፃር ትንሹ ነገር ነውናስትል ሊያ ለቫቲካን ዜና ተናግራለች። በአፍሪካ ያሉ ሴቶች በሁሉም አካባቢዎች የተለመደ አንድ አይነት ስቃይ ስለሚደርስባቸው በቶጎ እና በጋና መካከል ያለውን አከባቢ ለፊልሙ ቀረፃ ከመረጥን በኋላ ወዲያውኑ ከሴቶች ጋር አብረን መሥራት ጀመርን ብላለች ፕሮዲውሰሯ።

 

ሊያ የፕሮቪደንስ ማህበር አባል የሆኑትን ሲስተር ኤሌኖራ አጋሳን እንደ ረዳት ዳይሬክተር መረጠች።ከገዳማዊያን ጋር የመስራትን ሃሳብ በጣም ወድጄዋለሁ በፊት ከለመድነው በተለየ አይነት የሚወደዱ እህት ናቸው ሊያ ቀጠለች ሲስተር ኤሌኖራ አንትሮፖሎጂስት መሆናቸውን እና በአሁኑ ጊዜ ለማስተርስ ዲግሪ ኢያጠኑ መሆኑን ገልጻ ከዚህ በስተጀርባ አንድ የሚያምር ታሪክ አለ የሲስተር ኤሌኖራ እናት በቶጎ የዓለም የካቶሊክ የሴቶች ድርጅቶች ህብረት አባል ናቸው ፥ስለዚህ እንደ አንድ ገዳማዊ ሲስተር ኤሌኖራ ስለዚህ ለሴቶች ጥቅም ከገዳማዊያን ጋር ስለሚሰራው የካቶሊክ ሴቶች ህብረት ግንዛቤው አላቸው ማለት ነውበማለት አብራርተዋል።

ሲስተር ኤሌኖራ ያላቸው ዕውቀት ፊልሙን በመፍጠር ረገድ አስፈላጊ ነበር ስትል ሊያ ተናግራለች። የእሳቸው ትክክለኛነት እና ቁርጠኝነት መሰረታዊ ነገር ነበር በተጨማሪም የሚነገሩትን ታሪኮች ለመምረጥ የነበራቸው ስሜትም ጥልቅ ነበር የዘጋቢው ፊልም ትኩረት ከሆኑት የሴቶች ቡድን እና ከገዳማዊያን ጋር ወዲያው ስብሰባዎችን አዘጋጁ

 

ይህ ተሞክሮ ለእኔ ቆንጆ ነበር እንደ ልምምድ ነበር እናም ይህ ዘጋቢ ፊልም ልክ እንደትንሳኤነው ማለት እችላለሁበማለት ሲስተር ኤሌኖራ ለቫቲካን ዜና ተናግሯል።  

ይህ ዘጋቢ ፊልም የአፍሪካውያን ሴቶች የተሸከሙትን ጥልቅ መከራ እና የገቡበትን ስቃይ ይተርክልናል መልሶም በተመሳሳይ ጊዜ እንደገና መወለዳቸውን እና ትንሳኤያቸውን ያሳያል በትንሳኤአቸውም ከእነዚህ ሴቶች ጎን የተቀደሱ ሴቶች ምስል ይታያል።

 “እኔ እላለሁይላሉ ሲስተር ኤሌኖራ በመቀጠል ይህ ዘጋቢ ፊልም ሁሉንም የአፍሪካ ሴቶች ስቃይ የሚያሳይ አይደለም ነገር ግን አንድ ጠብታ ብቻ ነው ይህ ፊልም እንደ ኤክስሬይ ነው ምናልባትም የአፍሪካ ሴቶች ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ያሉ ሴቶችን መከራ የሚያንፀባርቅ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ሲስተሯ በተጨማሪ እንዳብራሩት የአፍሪካ ሴቶች በውስጣቸው የሚሰቃዩበት አንዱ ገጽታ ለሌላ ሰው የመናገር ድፍረት ሲያጡ ችግሩ ምን ያህል አስከፊ እንደሆነም ያሳያልብለው አክለውበዚህ የተነሳ ሕይወት ለአብዛኛዎቹ ሴቶች እንደ መቃብር ይሆናልብለው በአጽንኦት ተናግረዋል።

 

የተባረኩ ሰዎች የሚሰጡትን እርዳታ ጊዜያዊ ፍላጎትን ሊመልስ ይችል ይሆናል ነገር ግን ሰውየውን ራሱን የቻለ የተከበረ ኑሮ እንዲያገኝ የሚያደርግ እንደሆነ እገልጻለሁ። በዚህ ምክንያት ሁሉም በጎ ፈቃድ ያለው ሰው ሴቶች እና ቤተሰቦች ራሳቸውን እንዲችሉ በመርዳት ረገድ በሚሰሩትን ገዳማዊያን የሚያግዙ ፕሮጀክቶችን እንዲደግፉ እጠይቃለሁበባለትም ጥሪያቸውን አሰምተዋል።

 ማሪያ ሊያም ለቀረጻው በቦታው ላይ ነበረች ለእኔ በግሌ በእውነት ልብ የሚነካ ተሞክሮ ነበርስትል ተናግራለች። የዓለም ሴቶች ኦብዘርቫቶሪ 30 በላይ ሃገሮች ላይ ከአፍሪካ ሴቶች የሰበሰቡትን 10,000 የሚያህሉ የዳሰሳ ጥናቶችን አንብበዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች በትንሽ ቡድን የተዋቀሩ ስብሰባዎችን ተካፍለው አድምጠዋል ያነበቡት እና የሰሙት ነገር ሁሉሥጋና ደም ለብሶ እውነት ሆነበማለት ስለ ሲስተሯ ታስታውሳለች።በእጃችን ዳሰስነው በአይናችን አየነው በልባችን ነካነው በአእምሯችን ብቻ ተረድተን አልተውነውም የነዚህን ሴቶች ድምፅ የራሳችን አድርገናልበማለትም አክላለች ሊያ።

 

በዚህም ምክንያት ነው የዓለም የሴቶች ኦብዘርቫቶሪ ኢን-ቪስብልስን ያዘጋጀው ለባልደረባችን ሒልተን ፋውንዴሽን ምስጋና ይግባውና።በአፍሪካ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ቀስ በቀስ ለማጥፋት ብሎም ዓለም አቀፍ ዘመቻ ለመክፈት በጉባኤዎች እና በሲቪል ድርጅቶች መሃል ግንኙነት መፍጠር እንፈልጋለንበማለት ሃሳባቸውን ቋጭተዋል።

12 May 2023, 15:27