ፈልግ

በደቡብ ጣሊያን ካታኒያ ክፍለ ሀገር የተከበረ የማኅበራዊ መገናኛ ፌስቲቫል በደቡብ ጣሊያን ካታኒያ ክፍለ ሀገር የተከበረ የማኅበራዊ መገናኛ ፌስቲቫል 

በር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሃሳቦችን መሠረት ያደረገ የማኅበራዊ መገናኛ ፌስቲቫል ተከበረ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ ቀንን ምክንያት በማድረግ "ከልብ መናገር እና በየዋህነት ማከናወን" በማለት ያስተላለፉትን መልዕክት ዘንድሮ በደቡብ ጣሊያን ካታኒያ ክፍለ ሀገር የሚካሄደው የቅዱስ ጳውሎስ ገዳማውያን እና ገዳማውያት አሳታሚ ማኅበራት ለ18ኛ ጊዜ ላዘጋጁት ስብሰባ ዋና ርዕሥ አድርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ትክክለኛ የንግግር ባሕል፣ ቤተሰብ፣ ምሕረት፣ እውነት፣ ማኅበረሰብ፣ ለሰላም የሚሰጥ ትኩረት እና የሐሰት ዜናን መቃወም የሚሉ ሃሳቦች፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሐዋርያዊ የቤተ ክርስቲያን መሪነት ዓመታት ውስጥ ያስተላለፏቸውን አሥር ርዕሠ ጉዳዮች መሠረት ያደረጉ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግንቦት 13/2015 ዓ. ም. የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ ቀንን በማስመልከት የቅዱስ ጳውሎስ ገዳማውያን እና ገዳማውያት አሳታሚ ማኅበራት በዚህ ሳምንት በደቡብ ጣሊያን ካታኒያ ክፍለ ሀገር ለ18ኛ ጊዜ ያዘጋጁት ፌስቲቫል መሪ ቃል ሆኖ የሚያገለግል ርዕሠ እንደሆነ ታውቋል።

ማየት፣ መስማት፣ መናገር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ "ከልብ መናገር እና በየዋህነት ማከናወን" በሚል ርዕሥ ያዘጋጁት የ2023 ዓ. ም. ወይም የዘንድሮ ዓለም አቀፍ ማኅበራዊ መገናኛ ቀን መልዕክት መሪ ሃሳብ ሲሆን፣ የቅዱስ ጳውሎስ ገዳማውያን እና ገዳማውያት አሳታሚ ማኅበራትም በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ባደረጉት ስብሰባ ላይ የውይይት ርዕሥ አድርገውታል።   

በጣሊያን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የማኅበራዊ መገናኛ ቢሮ ተጠሪ የሆኑት አቶ ቪንቼንዞ ኮርራዶ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን የዘንድሮ መልዕክት ሲያብራሩ፣ ማየት፣ መስማት እና መናገር የሚሉት ቃላት በእውነት ላይ ያተኮረ የሐሳብ ልውውጥ እንዴት እንደሚረዳ ለማሳየት ቅዱስነታቸው የመረጧቸው ግሦች እንደሆኑ ተናግረዋል። ካዩ እና ካዳመጡ በኋላ ከልብ መናገር በተግባቦት ዑደት ውስጥ ዘወትር የተገናኙ ከሌሎች ጋር ለመቀራረብ ቁልፍ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በጎነት የታከለበት ግንኙነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለዓለም አቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ ቀን ባስተላለፉት መልዕክት ለቴክኒካዊ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በምንኖርበት ዘመን ያሉትን ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለማወቅ የሚያግዝ በመሆኑ "በመረጃ እና በማኅበራዊ መገናኛ ውስጥ እውነትን መፈለግ አለብን" በማለት አቶ ቪንቼንዞ ኮርራዶ በድጋሚ ተናግረው፣ ይህ ሊሆን የሚችለው በጎነት በታከለበት የመገናኛ መንገድ መሆኑን አስረድተዋል። ከልባችን ለመናገር መልዕክት ሊኖረን ይገባል ያሉት አቶ ቪንቼንዞ ኮርራዶ፤ ዓላማውም ልባችንን የእንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ አንቀሳቃሽ ሞተር እንዲሆንልን ለማድረግ ነው ብለዋል።

ደጉ ሳምራዊ መልካም ሞዴል ነው

ሮም ከተማ በሚገኝ ዘላተራን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ መገናኛ ትምህርት መምህር የሆኑት አቶ ማሲሚሊያኖ ፓዱላ፣ ደጉ ሳምራዊ ለማኅበራዊ መገናኛ መልካም ሞዴል ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ማሲሚሊያኖ በማከልም፣ "ሌላውን የሚያካትት" ከዲጂታሉ ዓለም ዕይታ በመውጣት እና የባሕላዊ ሚዲያው ዓይነተኛ ተዋረድ ሳይኖር፣ ግንኙነትን ወደ አግድም በማድረግ በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ጋር እኩል መግባባት እንዲኖር ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። ይህ ሁሉ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደተናገሩት፣ መረጃው ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደገና በመጀመር እና ከመጠን ባለፈ ፍጥነት የተነሳ ተቃርኖን ከመፍጠር መራቅ መሆኑን ሮም በሚገኝ ዘላተራን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ መገናኛ ትምህርት መምህር የሆኑት አቶ ማሲሚሊያኖ ፓዱላ አስረድተዋል። 

16 May 2023, 16:14