ፈልግ

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ለሕዝባቸው የፍትህ እና የሰላም ጥሪ አቀረቡ!

በመንግስት እና በትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መካከል በተደረገው ጦርነት ሁሉም ነገር ለጠፋባቸው ሰዎች "ፍትህ፣ ካሳ እና ይቅርታ" እንደሚያስፈልጋቸው ሊቀ ጳጳስ ዘካቶሊካዊያን፣ የኢትዮጲያ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባሄ ፕሬዝዳንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል መናገራቸው ተገለጸ። ብጹነታቸው ይህንን የተናገሩት የቫቲካን ራዲዮ ጋዜጠኛ ከሆነው አሌሳንድሮ ዲ ቡሶሎ ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ እንደ ነበረም ተገልጿል።

የእዚህ ዘጋብ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ አክለው እንደገለጹት ከሆነ በአገረ ስብከታቸው በአዲስ አበባ እና በገዳማዊያን እና ሚስዮናዊያን ማሕበራት የሚሰጡትን የተቀናጀ መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ አገልግሎት ለማዳበር የሚረዳ የግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ ፕሮጀክት እድገትን በጉጉት እየተጠባበቁ እንደ ሚገኙ አክለው ለጋዜጠኛ አሌሳንድሮ ዲ ቡሶሎ  ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ "በአየር ላይ ሰላም አለ" በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እና ወለጋ ክልሎች ከፍተኛ ጥቃትና ጉዳት ከደረሰ በኋላ አሁንም ሰላም በሚገባ ይጸና ዘንድ ጸሎት እየተደረገ ነው በማለት የተናገሩት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ለቫቲካን ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት “እውነተኛ ፍትህ እና በሕዝብ መካከል ይቅር መባባል እንዲፈጸም” እና ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃንየሱስ ሱራፌል እና የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት አባላት
ብጹዕ ካርዲናል ብርሃንየሱስ ሱራፌል እና የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት አባላት

በአፍሪካ ቀንድ በምትገኘው ታላቋ ሀገር ኢትዮጲያ ከ400,000 በላይ ሱዳናውያን ስደተኞች፣ 600,000 ሶማሊያውያን፣ ኤርትራዊያን፣ የመኖች እና ሶሪያውያን የሚገኙባት ሲሆን በቅርቡ ከ100,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ሲመለሱ ታይቷል።

እነዚህን "ተመላሽ" ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ተፈናቃዮች አምስት ሚስዮናዊያን ማሕበራት እና የመዲናዋን የአዲስ አበባ አገረ ስብከት የሚያካትት ግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ የሙከራ ፕሮጄክትን ተስፋ ያደርጋል።

በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ “ሲኖዶሳዊነት” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ አህጉራዊ ሲኖዶስ  ጉባኤን  ያዘጋጀው ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን በበላይነት የሚያስተዳድሩት የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ጋሊቀ ጳጳስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ አበይት ሃሳቦች ናቸው።

ቤተሰብን ማእከል ያደረግ የአፍሪካ አህጉራዊ ሲኖዶስ ጉባኤ

እ.አ.አ ከሐምሌ 1999 ዓ.ም ጀምሮ በእዚያን ወቅት የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት በነበሩት ካርዲናል ብርሃነየሱስ መሪነት ቤተስብ በአፍሪካ ስላለው ወሳኝ ሚና ተወያይተው ነበር።

በአዲስ አበባ አገረ ስብከት ውስጥ የሚኖሩ 12,000 ካቶሊኮዊያንን የሚመሩት ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነየሱስ  ከ200 የሚበልጡ የሲኖዶሱ ተሳታፊዎች ቤተሰብ “የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን ምስል” በማለት አጽንኦት ሰጥተው እንደ ተናገሩ ያስታውሰናል።

ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ ልጆች ያሏቸው ወጣት ብቻቸውን የሚኖሩ ሴቶች እና በአዲሲቷ አፍሪካ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለመደ የመጣው “አንድ ወላጅ ያለው ቤተሰብ” “አካታች” መሆን አለበት የሚለው ሐሳብ ነው።

ቤተ ክርስቲያን እና ትምህርት

በቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ሥራ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር “የቁምስና ተግባር ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ተግባራት ከትምህርት ቤት እስከ ማኅበራዊና ጤና ጥበቃ” ድረስ ሊሳተፉ ይገባል ሲሉ ብፁዕ ካርዲናል ሱራፊኤል ነግረውናል ሲል የቫቲካን ራዲዮ ጋዜጠኛ አሌሳንድሮ ዲ ቦሶሎ ከብጹነታቸው ጋር የነበረውን ቆይታ የገለጸ ሲሆን በአፍሪካ የተለመደ ለሆነው “ሰፊ ለሆነ ቤተሰብ” የሲኖዶሱ ጉባኤ ምስረታና ድጋፍ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀውልናል ብሏል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደሩ 430 ትምህርት ቤቶች እና በአዲስ አበባ ዳርቻ ላይ የኢትዮጵያ ጳጳሳት እያስገነቡት የሚገኘውን የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲ ጋር በመተባበር የቤተስብ አስፈላጊነት ላይ እና ሊደረግለት ስለሚገባው መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ ድጋፍ እንደ ሚሰራም ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ገልጿል።

 “ትምህርት የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ብሄሮች እና ጎሳዎች መካከል አብሮነትን ለማምጣት ወሳኝ” መሆኑን ስለምናምን በእዚህ ረገድ ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ አስረድተዋል፣  

"ከድህነት ለመውጣት" ነፃ የሰዎች እንቅስቃሴ

ካርዲናሉ በአህጉሪቱ ሲኖዶስ ጉባኤ የተገለጸው “ወጣቶቻችንን በአህጉሪቱ ውስጥ ለማቆየት፣ በአህጉሩ እንዲኖሩ በአፍሪካ ውስጥ እንደ አውሮፓ ህብረት ሁሉ ነፃ የሰዎች ዝውውር ቁልፍ እንደሚሆን እምነታቸውን” የገለጹ ሲሆን  በሜዲትራኒያን ባህር ለመሞት ወደ ሱዳን ከዚያም ወደ ሊቢያ ለመሄድ ወይም ወደ ባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ለመሰደድ "መጨረሻ ላይ እንግልት ወይም ስቃይ እንዲደርስባቸው የሚያደርጉትን ነገሮች መቅረፍ ይኖርብናል” ብሏል።  

በየካቲት ወር ደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ የኢትዮጵያ ካርዲናል በርዕሰ ሊቀ ጳጳሳቱ ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ በተገኙበት ወቅት “ብዙ ኢትዮጵያውያን፣ ኬንያውያን፣ ኤርትራዊያን፣ ኡጋንዳውያን ወጣቶች በደቡብ ሱዳን ሲሰሩ አይቻለሁ” ማለታቸው ተገልጿል።

በርካታ የአፍሪካ ድንበሮች ሰው ሰራሽ መሆናቸው በቀድሞ ቅኝ ገዢዎች የተደነገጉ መሆናቸውን ጠቁመው ድንበሮች ክፍት ከሆኑ ወጣቶች በተሻለ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ሁኔታቸውን በመቀየር "ከድህነት ወጥተው የሰውን ልጅ ክብር ማስጠበቅ ይችላሉ" ብለዋል።

የግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ የሙከራ ፕሮጀክት

ግሎባል ሶሊዳሪት ፈንድ እ.አ.አ በ2020 መገባደጃ ላይ በአዲስ አበባ ወጣት አፍሪካውያንን በማሰልጠን ላይ ያተኮረ የሙከራ ፕሮጀክት ጀምሯል ሲሉ የተናገሩት ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ይህ ሚስዮናዊ ከሆኑ ማሕበራት፣ የግል ኩባንያዎች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች “ተመላሽ” ስደተኞችን፣ የሌሎች አፍሪካ ሀገራት ስደተኞችን እና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።  

ይህንንም ያደረገው  በካቶሊክ ገድማት ሕብረት ኔትወርክ እንዲቋቋም በመደገፍ ነው፣ እሱም አሁን የሳሌዢያን ማሕበር አባቶች እና ደናግላን እህቶች (የክርስቲያኖች ረዳት የማርያም ልጆች ማሕበር)፣ የኡርሶላይን ማሕበር እህቶች፣ የእማሆይ ትሬዛ ማሕበር እህቶች እና ኢየሱሳውያን (በኢየሱሳውያን የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም) በአዲስ አበባ አገረ ስብከት የማሕበራዊ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጫ ኮሚሺን አስተባባሪነት እየተከናወነ ይገኛል ብሏል።

እያንዳንዱ ገዳም እና የሚስዮናዊያን ማሕበር ከ1,500 በላይ ተጠቃሚዎችን በሙያ ስልጠና፣ በድርጅት ውስጥ በመቀጠር ወይም ሥራ እንዲጀምሩ በማድረግ ወደ አገር ውስጥ የስራ ገበያ የመግባት ክህሎት እንዲያገኙ ያስቻለ በጎ መንገድ በመፍጠር ረገድ የራሳቸውን ሚና መጫወታቸውን ካርዲናል ገልጿል።  

ስልጠና፣ የሥራ ፈጠራ እና ለሚሰቃዩ ሰዎች እንክብካቤ ማድረግ

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል የግሎባል ሶሊዳሪት ፈንድ ፕሮጀክትን ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ አንዳንድ የሥልጠናና የሥራ ምደባ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፣ እናም ለስኬቱ በጣም አመስጋኝ እንደሆኑ እንደተሰማቸው፣ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ይህንኑ ተሞክሮ ለማጋራት ሐሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ወደ ባህረ ሰላጤው ሀገራት በቤት ሰራተኝነት የሚሰደዱ በርካታ ወጣት ሴቶችን ችግር አስታውሰዋል። ነገር ግን በቂ ዝግጅት አላደረጉም፤ ከኢትዮጵያ መንደሮች ወደ ዱባይ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች የሚደረገው ሽግግር ብዙ ጊዜ አሰቃቂ ነው ሲል ተናግሯል።

በቅርቡ ወደ 100,000 የሚጠጉ የቤት ሰራተኞች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ለመኖር የሚያስችል ገንዘብ የላቸውም፣ እነዚህ "ተመላሽ" ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ግሎባል ሶሊዳሪት ፈንድ በሚያራምደው ሕብረተሰብ አቀፍ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች ናቸው ብሏል።

ህይወትን መቀየር

ግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለተበደሉት፣ ለተጣሉ እና ተስፋ ለሌላቸው እና በጣም ለተቸገሩት ከአረብ ሀገራት ወይም ከሌላ ቦታ ለተመለሱ ሰዎች ትልቅ እገዛ እንድታደርግ እያገዘ መሆኑን የገለጹት ካርዲናል ብርሃነየሱስ የተለያዩ የክቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማት እና ሚስዮናዊ ማሕበራት እነዚህ የተቸገሩ ሰዎች በደስታ ተቀብለው ለእነዚህ ስደተኞች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንዲሁም የማኅበረሰባዊ ሥነ ልቦናዊ ድጋፍ በመስጠት ከአገር ሳይወጡ ሕይወታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ እየሰሩ እንደ ሆነ ገልጿል።

ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች ልጆቻቸውን ለእህቶች/ገዳማዊያን/ገዳማዊያት አደራ በመስጠት እና ወደ ስልተና ማዕከላት በመሄድ የተለያዩ የስራ ክህሎቶችን መማር ይችላሉ። አንዳንዶች የራሳቸውን አነስተኛ የግል ሥራ መጀመር ችለዋል። ሌሎች በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ኩባንያዎች ተቀጥረው እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ገልጿል።

ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ይህ ፕሮጀክት እንዲቀጥል እና ጥረቱን እዚህ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቦታዎች ላይ እንዲያተኩር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። በመቂ አገረ ስብከት ተመሳሳይ ጥረት አለ፣ ነገር ግን በሌሎች አገረ ስብከቶች ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

አብሮ የመሥራት ጉልህ ውጤቶች

ትብብር እና ትሥሥር መፍጠር ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ከግለሰቦች ጋር አብሮ ለመስራት መሳሪያ ሊሆን እንደሚችልም ካርዲናል ብርሃነየሱስ የጠቆሙ ሲሆን ይህ አዲስ የአገር ውስጥ ሥራ ሞዴል ምናልባት ከሀገር ለመውጣት ለሚመኙ ሌሎች ወጣቶችም ተስፋ ሊሰጥ ይችላል ብለው ስለዚህ የግሎባል ሶሊዳሪቲ ፈንድ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች እነሱም ኢትዮጵያ ውስጥ በመቆየት አዲስ ሙያ፣ ሥራ፣ መተዳደሪያ፣ የተከበረ ሕይወት እንዲኖራቸው በማሰልጠኛ ማዕከላት መማር እንደሚችሉ አስረድተዋል።

 

04 May 2023, 10:33