ፈልግ

2021.12.15 Gruppo di cristiani che pregano insieme davanti la Bibbia

ሐሰት አትናገር

መናገር የአምላክ ትልቅ ስጦታ በመሆኑ ሰውን ከእንስሳት በላይ ያደርገዋል። እግዚብሔር ለእኛ የመናገር ችሎታ ሲሰጠን በዚህ ጥሩ መሣሪያ መልካም እንጂ ክፉ እንዳናደርግ አዝዞናል። ምላሳችንን ከክፉና ተንኰለኛ ጠመዝማዛ ንግግር እንድንገታት አስጠንቅቆናል። በአፋችን እውነት እንጂ ሐሰት እንዳንናገር አዝዞናል። በስምንተኛው ትዕዛዝ «በሐሰት አትመስክር፣ አትዋሽ´ ይለናል። በወንግገል ደግሞ ንግግራችሁ «አዎን ከሆነ አዎን ወይም አይደለም ከሆነ አይደለም ይሁን” (ማቴ. 5፣36) እያለ ይናገረናል። ስለዚህ ሐሰትንና ማታለልን ጠልተን እውነትን እንድንወድ ይመክረናል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ «ሐሰት ይቅር በነፍስ ወከፍ ሁላችን ውሸትን አንናገር፣ ከባልንጀራችን እያንዳንዱ እውነት ይናገር” (ኤፌ. 4፣25) እያለ ይህን መለኮታዋ ትዕዛዝ በድጋሚ ይነግረናል። በዚሀ አኳያ ሁላችን የአንድ አካል ክፍሎች ስለሆንን እርስ በርሳችን እውነት እንናገር´ በነፍሰ ወከፍ ከባልንጀራው እንደ ሐዋርያው ቃል እውነት ብቻ መናገር አለበት።

በመጽሐፈ ምሳሌ ከሰባቱ ነገሮች አንዱ እግዚአብሔር የሚጠላው ሐሰትን እንደሆነ እናነባለን (ምሳ. 6፣16-19)። እግዚአብሔር ራሱ ሐቅ ስለሆነ ሐሰትን ፍጹም ይጠላል። ሐሰትን ብንናገር ይፈርድብናለ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሕይወታችን ዘመን ይቀጣናል። ሐናንያ ከሚስቱ ጋር ተስማምቶ መሬቱን ሸጠ፤ ገንዘቡን እንደሚገባው በሙሉ ለቀደ መዛሙርቱና ለሐዋርያቱ በስጠት ፈንታ ከፊሉን ለራሱ አስቀረውና በቤቱ አስቀመጠው።

ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈጽ ቅድስ ገልጦለት ይህን አውቆ «ሐናንያ ሆይ! እንዴት አድርጐ ሰይጣን በልብህ ገብቶ መንፈስ ቅዱስን እንድትዋሽ አሳሳተህ; ስለምን የመሬትህን ሽያጭ ገንዘብ ከፍለህ ለራስህ አስቀረህ; እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም። መሬትህን ባትሸጥ በፊት ያንተ ነበረ፤ ከሸጥከውም በኋላ ገንዘብ በሙሉ ያንተ አልነበረምን; ታዲያ ይህን ነገር በልብህ ለምን አሰብህ; አዎ የዋሸኸው በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ በሰው ላይ አይደለም´ አለው። ሐናንያ ይህንን ከሰማ በኋላ በድንጋጤ ወደቀና ሞተ፣ ያዩት ሁሉ በጣም ፈሩ።

ከሶስት ቀን በኋላ ሚስቱ ሰጲራ በባሏ ላይ የደረሰበትን ምንም ሳታውቅ መጣች። ቅዱስ ጴጥሮስ «በዪ እስቲ ንገሪኝ መሬታችሁን የሸጣችሁት ይህን በሚያህል ገንዘብ አይደለም;´ ሲል ጠየቃት። እርሷም «አዎን ይህን በሚያህል ዋጋ ነው´ አለችው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ «የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን አንዴት ተስማማችሁ; እነሆ ባልሽን ቀብረው የሚመለሱ ሰዎች በበር ቆመዋል፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” (የሐዋ. 5፣1-11) አላት። እርሷም በድንገት በእግሩ ሥር ወደቀችና ሞተች። በቤተክርስቲያን ትልቅ ፍርሃት ሆነ፤ ሁሉም ደነገጡ።

እግዚአብሔር ሐሰትን በጣም አንደሚጠላ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በዚህ ዓለም ሳይቀር እንደሚቀጣን እያወቅን ሳንፈራ ብዙ ጊዜ እንዋሸዋለን፤ በማይረባ ምክንያት ውሸትና ሐሰት እንናገራለን። ሐሰት ከብዙ ኃጢአቶቻችን አንዱና መሣሪያችን ነው። ትንሽ ሲቸግረን እውነትን በድፍረት በናገር ፈንታ ልምድ ሆኖብን እንዳናፍር፣ ሰዎች እንዳይስቁብን ብለን ያለ አንዳች ይሉኝታ ሐሰት እንናገራለን። አንድ ጉዳይ እንዲቃናልን ውሸት መናገር የሚያስፈልግ ከሆነ ሳናወላውል እንዋሻለን። ስናወራ እንዲያምርልን ሐሰትንና ቃለ አጋኖ እንጨምርበታለን።

08 May 2023, 11:10