ፈልግ

ጥቃቱ ከደረሰ ከቀናቶች በኋላ ብዙ ሰውች ወደ ሥፍራው እየመጡ ነው ጥቃቱ ከደረሰ ከቀናቶች በኋላ ብዙ ሰውች ወደ ሥፍራው እየመጡ ነው 

በዳላስ የምትገኘው ቤተክርስቲያን በአለን ከተማ በገበያ ማዕከል ላይ በተፈፀመው ጥቃት ሰለባዎች ማዘኗን

የዳላስ ማህበረሰብ ታጣቂውን ጨምሮ 9 ሰዎች በተገደሉበት የጅምላ ግድያ ሰለባዎች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ፥ ኤጲስ ቆጶስ ኤድዋርድ ጄ በርንስ በበኩላቸው 'የአካባቢው የካቶሊክ ማህበረሰብ ለተጎጂ ቤተሰቦች ያላቸውን አጋርነት ገልጿል' ብለዋል።

ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የዳላስ ኤጲስ ቆጶስ ኤድዋርድ በርንስ ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 28 በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አለን ከተማ ውስጥ በተፈፀመው የጅምላ ጥቃት ለተገደሉት ቤተሰቦች ያላቸውን ቅርበት

 

ከጠዋቱ 330 ላይ አለን ከተማ በሚገኘው የገበያ ማዕከል በአንድ ታጣቂ በተከፈተ ተኩስ አንድ ሕፃን ጨምሮ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ደግሞ ቆስለዋል።

 

እንደ አካባቢው ባለስልጣናት ገለፃ መሰረት ተጎጂዎች 5 እስከ 61 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸውም ተብሏል።

 ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር መተባበር

ጳጳስ በርንስ ለምእመናንበተሰበረ ልብሲናገሩየካቶሊክ ማህበረሰብ በዚህ አደጋ ዘመዶቻቸውን ካጡ ቤተሰቦች ጋር በአንድነት እና በህብረት አብረው ናቸውብለዋል።

እንደ አለን ማህበረሰብ የተፈፀመው ጥቃት እና በማህበረሰባችን ውስጥ በተከሰተው ስሜት አልባ የሆነ በንጹሃን ላይ የተወሰደው እርምጃ እኔንም በጣም አስጨንቆኛልሲሉ በመግለጽ በዚህ አሳዛኝ ክስተት ላዘኑ ለአከባቢው ማህበረሰብ ለተጎጂዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ሁሉ እግዚአብሔር መጽናናቱን እና ጥንካሬውን እንዲሰጣቸውጠን እጸልያለሁብለዋል ብጹእነታቸው። በማከልም  

ለአካባቢያችን ሠላም መጸለይ አለብን እናም የክፉ መንፈስ እና የሞት ባህልን ለመቃወም ድፍረት ሊኖረን ይገባልብለዋል።

 

በአለን የተኩስ እሩምታ የተከሰተው የኤስ ሹፌር የሆነው ሰው ሆን ብሎ በቴክሳስ ድንበር ከተማ በሆነችው ብራውንስቪል ከሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ወጥተው አውቶብስ ሲጠብቁ በነበሩ የቬንዙዌላዊያን ስደተኞች ላይ መንገድ በዘጋበት ከሰዓታት በኋላ ሲሆን በድርጊቱም 8 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 10 ቆስለዋል።

 በአሜሪካ ውስጥ በተከታታይ የተካሄደው የቅርብ ጊዜ የጅምላ ጥቃት

በቅርብ ጊዜ በተከታታይ የደረሱት የጅምላ ጥቃቶች በዋናነት ያነጣጠሩት ትምህርት ቤቶችን ሱፐርማርኬቶችን የሥራ ቦታዎችን እና ሌሎች የህዝብ መሰብሰብያ ቦታዎች ላይ ሲሆን እስካሁን ምንም ውጤት ያላመጣው በጠመንጃ አጠቃቀም ማሻሻያ ላይ የሚካሄደው ብሄራዊ ክርክር ሁሌም እንደተደረገ ነው።

የአሜሪካ ጳጳሳት በተጨማሪም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስንያለ ልዩነት የጦር መሣሪያ ዝውውር 'ይበቃል' የምንልበት ጊዜ ነውበማለት ያቀረቡትን አቤቱታ በማስተጋባት ምክንያታዊ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲደረግ ደጋግመው በመጠየቅ ክርክሩን ተቀላቅለዋል።

.. ሰኔ 2022 የአሜሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ (USCCB) የአራት ኮሚቴ ሰብሳቢዎች መግለጫ አውጥተዋል። ይህም መግለጫ ሁሉም የኮንግረስ አባላት የአእምሮ ጤናን የቤተሰብን ሁኔታ የአኗኗር ዘይቤን የመዝናኛው እንዱስትሪ እና የመጫወቻ መሳሪያ ፋብሪካዎችን ተጽእኖን ስርዓት አልበኝነትን እና የመሳሪያ አምራቾችን ግምት ውስጥ ያስገባ ሁሉንም የችግሩን ገጽታዎች የሚፈታ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።

 

ከጥር 1 ጀምሮ ቢያንስ 191 የጅምላ ጥቃቶች ተደርገዋል

ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በአሜሪካ ቢያንስ 191 የጅምላ ተኩስ ተመዝግቧል (ምንም እንኳን የጅምላ ተኩስ ፍቺ አሁንም እያከራከረ ቢሆንም)

እስካሁን ድረስ እጅግ ብዙ የሰው ህይወትን የቀጠፈው ክስተት የተፈጠረው ... 2017 የላስ ቬጋስ የተኩስ እሩምታ ሲሆን 64 ዓመት ዕድሜ ያለው ታጣቂ የሙዚቃ ፌስቲቫል ለመታደም በተገኘ ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት 60 ሰዎችን የገደለበት ዘግናኝ ድርጊት ነበር።

 

በጅምላ ተኩስ ምክንያት ከመሳሪያ ጋር የተገናኙ ሞቶች በነፍስ ግድያ ራስን በማጥፋት በአከባቢ ብጥብጥ እና በአደጋ ምክንያት የሚደርሰውን ሞት ይጨምራል።

 ለአሜሪካ ህጻናት እና ታዳጊዎች ሞት ምክንያት የሆነው መሳሪያ

... 2014 ጀምሮ በአማካይ በአሜሪካ 39,000 በላይ ሰዎች በጠመንጃ ሲሞቱ በዚህ ዓመት 14,000 በላይ ሰዎች ከጠመንጃ ጋር በተያያዘ ጥቃት እንደሞቱ የመሳሪያ ሁከቶችን የሚመዘግበው ተቋም ገልጿል።

የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ጠመንጃ ለአሜሪካ ህጻናት እና ታዳጊዎች ቀዳሚ የሞት መንስኤ እንደሆነ እና 2022 በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከየትኛውም ዓመት በበለጠ ብዙ ታዳጊዎች በጥይት ተመትተዋል።

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ... 2015 የኮንግረሱ የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ጨምሮ የጠመንጃ ዝውውርን በተደጋጋሚ አውግዘዋል።በግለሰቦች እና በህብረተሰቡ ላይ ያልተነገረ ስቃይ ለማድረስ ያለሙ ገዳይ መሳሪያዎች የሚሸጡት ለምንድን ነው?” ሲሉ የአሜሪካ ህግ አውጪዎችን ጠይቀዋል።በሚያሳዝን ሁኔታ መልሱ ሁላችንም እንደምናውቀው ለገንዘብ ብቻ ነው በደም የጨቀየ ገንዘብ ብዙውን ጊዜ ደግሞ የንጹሃን ደም ነው።ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

10 May 2023, 16:08