ፈልግ

2023.02.23 Logo: Assemblea Continentale dell'Asia_24-26 febbraio 2023

ብፁዕ ካርዲናል ፌርራኦ የሕንድ ጳጳሳት እና ካህናት 'ሲኖዶሳዊነትን’ እንዲያበረታቱ አሳሰቡ።

የሕንዱ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፊሊፕኔሪ ፌርራኦ ኤጲስ ቆጶሳት እና ካህናት ሲኖዶሳዊነትን በሁሉም የቤተ ክህነት ሕይወት ዉስጥ እንዲያስፋፉ ጥሪ አቅርበዋል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የሕንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ብፁዕ ካርዲናል ፌርራኦ ሲኖዶሳዊነት ማለት ከማስተዋል ጋር አብሮ መጓዝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው በመናገር ይህምየሲኖዳል አመራርየሚባል አዲስ የቤተ ክርስቲያን አመራር ተምሳሌትን ይጠይቃል ብለዋል።

 

በተጨማሪም የጎዋ እና የዳማን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናሉ በባንጋሎር እየተካሄደ ያለውን የህንድ ካቶሊ ጳጳሳት ብሄራዊ አውደ ጥናት ለስልታዊ ዕቅድ በባንጋሎር ከተማ ሲያስጀምሩ ነው ጥሪውን ያቀረቡት።

ይህ አመራር የቤተክርስቲያኑ አባል የሆኑ ሁሉ እንዲረዱ እንዲከበሩ እንዲመሰገኑ እና እንዲታወቁ ያላቸውን ጥልቅ ፍላጎት ለማረጋገጥ እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ሁኔታን ይፈጥራልብለዋል።

 

ብፁዕነታቸው አክለውምየምዕመናን የገዳማዊያንን እና የካህናትን ስብዕና እና ተሳትፎ የሚያጎለብት ሲኖዶሳዊ ባህል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነውበማለት ተናግረዋል።

ይህ በህንድ ማህመራዊ ጥናት ኮሌጅ ዳይሬክተር በሆኑት በአባ ጆሴፍ ዣቪየር የሚመራው ለሁለት ቀናት የሚቆየው የስልታዊት እቅድ አውደ ጥናት በሁለቱም ብሔራዊ እና ክልላዊ ደረጃዎች ሲካሄድ የነበረውን ስልታዊ ዕቅድ ሂደት ለማጠናቀቅ የሚያስችል ጥልቅ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት እንደሆነም ተብራርቷል።

09 May 2023, 12:16