ፈልግ

መካከለኛው ፍልስጤማውያን ቤተልሔም መካከለኛው ፍልስጤማውያን ቤተልሔም   (ANSA)

የቅድስት ሀገር ፓትርያርክ፡ ቤተክርስቲያን በአክራሪዎች አትሸበርም ማለታቸው ተገለጸ።

በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌም የክርስቲያን ማህበረሰቦች ላይ እያነጣጠሩ ያሉ ጥቃቶች እየተበራከቱ ባሉበት ሁኔታ እና በቀጠለው የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ የላቲን ስርዓተ አምልኮ የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ቤተክርስቲያን በጥቂት ጽንፈኞች አጀንዳዋን እንዲወስኑ እንደማትፈቅድ እና ለሰላምና ለዕርቅ መሥራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

የእዚህዝ ግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በጠ/ሚ ቤንጃሚን ኔታንያሁ አወዛጋቢ የዳኝነት ማሻሻያ ዙሪያ በእስራኤል እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ፣ በእስራኤል ወታደሮች፣ በጋዛ እና በዌስት ባንክ በፍልስጤማውያን መካከል ያለው ውጥረት፣ የክርስቲያን ማህበረሰቦች በሃይማኖት አክራሪዎች ኢላማ ሆነዋል።

በናዝሬት በሚገኘው ማሮኒት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ክስተት

የመጨረሻው ክስተት የተከሰተው እ.አ.አ እሑድ መጋቢት 26 ቀን ናዝሬት ውስጥ ሲሆን አንድ ወጣት መስዋእተ ቅዳሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ማሮኒት ቤተክርስቲያን እንደገባ እና በወቅቱ መስዋዕተ ቅዳሴ ስያሳርጉ የነበሩትን ቆመስ ከቅዱስ ቁራን መጽሐፍ እንዲነበብ ጠየቀ ። አቡና ኤጀንሲ እንደዘገበው ካህኑ እምቢ ሲል ሰውዬው ጮክ ብሎ መጸለይ የጀመረ ሲሆን በተሰብሳቢዎቹ ምዕመናን ከቤተክርስቲያን እንዲወጣ እስከተደረገበት ወቅት ድረስ ጩኸቱን አላቋረጠም ነበር።

በናዝሬት ሁለት የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ኢላማ ሆነዋል

ከዚያ በፊት እ.አ.አ በመጋቢት 23 አምስት ጭንብል የለበሱ የታጠቁ ሰዎች በናዝሬት ወደሚገኝ የሳሌዢያን  እህቶች ትምህርት ቤት መነኮሳቱን 'ረመዳን ከሪም' (ረመዳን ለጋስ ይሁን) እንዲሉ በኃይል ገብተው አስገድደው ነበር። መነኮሳቱ እምቢ ብለው ሰዎቹን ከህንጻው ማስወጣት ችለዋል።

ክስተቱ የተከሰተው በናዝሬት በፍራንችስካውያን እህቶች የሚተዳደር የካቶሊክ ትምህርት ቤት በሁለት ያልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ኢላማ ከተደረገ ከሳምንት በላይ ሲሆን ይህም እንደ እድል ሆኖ ማንንም ሰው ሰለባ አላደረገም እና ከጥቂት ቀናት በኋላ ሁለት አክራሪ እስራኤላውያን በጌቴሴማኒ ቤተክርስትያን ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል በምስራቅ እየሩሳሌም አከባቢ ማለት ነው።

በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እና በቀሳውስቱ ላይ አካላዊ እና የቃል ጥቃቶች

በአብያተ ክርስቲያናት፣ በመቃብር ቦታዎች እና በክርስቲያናዊ ንብረቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ በክርስቲያን ቀሳውስት ላይ በተለይም በእስራኤል ጽንፈኛ ሰፋሪዎች ላይ ከሚደርሰው አካላዊ እና የቃላት ጥቃት በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መጥቷል፣ እናም አዲሱ የቀኝ አክራሪ ጥምረት ከተቋቋመ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በቤንጃሚን ኔታንያሁ የሚመራ መንግስት እ.አ.አ በታህሳስ 2022 ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ማለት ነው።

በክርስቲያኖች ላይ የሚቃጣው ጥቃት ኢላማዎች የካቶሊክ እና የግሪክ-ኦርቶዶክስ ሕንፃዎችን ያካትታሉ። ከአንግሊካን መካነ መቃብር ውስጥ ሁለት ሰዎች የመቃብር ድንጋይ በመጣል እና መስቀሎችን በከሰከሱበት አዲስ አመት ላይ አንዱ የቅርብ ጊዜ ክስተት ተከስቷል። በርካታ የአርመን እና የሶሪያ ቄሶች እና የሃይማኖት ተከታዮች በተደጋጋሚ ትንኮሳ እና የቃላት ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

ፒዛባላ፡ ቤተ ክርስቲያን ተጨንቃለች ግን አትፈራም።

በእነዚህ ክስተቶች ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ፣ ቤተክርስቲያኒቱ ጉዳዩ ያሳስባታል፣ ነገር ግን በአክራሪዎች አትሸበርም፣ ሁሉም ሙስሊሞች አክራሪ አይደሉም፣ አይሁዶችም አይደሉም ብሏል።

"ጥቂት የተናደዱ ወንጀለኞች አጀንዳችንን እንዲወስኑ አንፈቅድም። ከእነዚህ ሰዎች ጥላቻ የሚበልጥ ነገር አለን” ሲሉ ለሬዲዮ ማሪያ ተናግሯል። “አክራሪነት ሁሉም አንድ ነው፣ ግን አንፈራም። አጠቃላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ​​አሉታዊ እንደሆነ እና ወደ ሁከት መባባስ እየተጓዝን እንደሆነ እናውቃለን፣ ነገር ግን መፍራት የለብንም ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ፒዛባላ፣ የሃይማኖቶች ትብብር መሻትን መቀጠል እንደሚያስፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል።

"እንደ ክርስቲያን ማህበረሰብ በጥቂት ጽንፈኞች ራሳችንን ሳናሸብር የአንድነት ማህበረሰቦችን ለመገንባት መስራት እና መተባበር አለብን" ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

የእስራኤል ፓትርያርክ ብጹዕ ራፊች ናህራ ይህንን እውነታ አስተግብተው ነበር “ክርስቲያኖች በዚህች ሀገር ውስጥ፣ በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ብዙ የመሠረታዊነት እንቅስቃሴዎችን በመጋፈጥ ትንሽ ማህበረሰብ ናቸው” ሲሉ ለሬዲዮ ማሪያ ተናግሯል። "እዚህ ያለን ተልእኮ አለን፣ የኢየሱስን የማስታረቅ ወንጌል በድፍረት የመመስከር" ሲሉ ተናግሯል። "በአንድነት ለመኖር ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን" ብለዋል።

በእየሩሳሌም ውስጥ ያሉ ቅዱሳን ቦታዎችን ለተሻለ ጥበቃ እንዲደረግ አቤቱታዎችን ተቀላቅሏል።

ባለፉት ወራት በቅድስት ሀገር ያሉ የክርስቲያን መሪዎች ማህበረሰባቸው በአክራሪ የእስራኤል አክራሪ ቡድኖች ከክልሉ እየተፈናቀሉ ነው ሲሉ ደጋግመው አስጠንቅቀዋል። በቅርቡ በጌቴሴማኒ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ የኢየሩሳሌም የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኢየሩሳሌም የሚገኙ ክርስቲያኖችን እና ቅዱስ ቦታዎቻቸውን ለመጠበቅ ዓለም አቀፍ ጣልቃገብነት እንዲደረግ በመጠየቅ "በየትኛውም ቅዱስ ቦታ ላይ በሽብር ወንጀል በተሳተፉ ሁሉ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ" ጠይቀዋል።

30 March 2023, 13:53