ፈልግ

የባለሙያዎች ቡድን በናይሮቢ ውይይቱን ሲያክሂድ የባለሙያዎች ቡድን በናይሮቢ ውይይቱን ሲያክሂድ 

በሲኖዶሳዊነት ላይ የሚወያይ የባለሙያዎች ስብሰባ በኬንያ ተካሄደ

በአዲስ አበባ ሊደረግ የታቀደው አህጉራዊ ጉባኤ ከመካሄዱ ከአንድ ወር ተኩል አስቀድሞ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ናይሮቢ ውስጥ ግንባር ቀደም በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማትኮር ውይይት አካሂዷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከጋና መዲና አክራ እስከ ኬንያ መዲና ድረስ ሲኖዶሳዊ ሂደትን በማስመልከት ቤተ ክርስቲያን በመላው አፍሪካ ውስት በመንቀሳቀስ እንዳለች ታውቋል። ኢትዮጵያ ዋና መዲና አዲስ አበባ ከየካቲት 22 27/2015 ዓ. ም. ድረስ ሊካሄድ የታቀደውን አህጉራዊ ጉባኤ በማስመልከት ከጥር 15-17/2017 ዓ. ም. ድረስ ውይይት ተካሂዷል። በናይሮቢ የተካሄደው ስብሰባ ከመላው አህጉሪቱ የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ያካተተ መሆኑ ተመልክቷል። ሲኖዶሳዊ ሂደትን በማስመልከት በናይሮቢ የተካሄደው ሁለተኛው የባለሙያዎች ስብሰባ፣ በታህሳስ ወር 2015 ዓ. ም. ጋና ላይ ከተካሄደው እና በሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀው የአህጉራዊ መድረክ ሰነድ ለመመልክት የተሰበሰበ የአህጉራዊ መርሃ ግብር ስብሰባ እንደ ሆነን ታውቋል።

ከመጀመሪያው ስብሰባ በኋላ ሁለተኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ሲኖዶሳዊነት ረቂቅ ሰነድም የተዘጋጀ ሲሆን፣ ይህን ሰነድ የሚመለከተው የናይሮቢው ስብሰባ በአፍሪካ እና ማዳጋስካር ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚዬም ጽ/ቤት እና በአፍሪካ ሲኖዶሳዊነት ኢኒሼቲቭ ተባባሪነት መዘጋጀቱ ታውቋል።በናይሮቢ ከጥር 15-17/2017 ዓ. ም. ድረስ የተካሄደው ስብሰባው ዋና ዓላማ ረቂቁን ከየአገራቱ ቤተ ክርስቲያናት ከተሰበሰቡ አዳዲስ ግንዛቤዎች ጋር በማነጻጸር ለመገምገም እና በመጭው መጋቢት ወር ላይ በአዲስ አበባ በሚካሄደው አህጉራዊ ጉባኤ መርሃ ግብር ላይ ለመወያየት መሆኑ ታውቋል።

 

25 January 2023, 17:25