ፈልግ

በናይጄሪያ ውስጥ ካቶሊካዊ ምዕመናን በጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ በናይጄሪያ ውስጥ ካቶሊካዊ ምዕመናን በጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ 

ናይጄሪያ ውስጥ በምዕመናን ላይ ለደረሰው አደጋ በቂ የብዙሃን መገናኛ ትኩረት እንዳልተሰጠው ተገለጸ

በናይጄሪያ ውስጥ ኦዎ ከተማ ካቶሊካዊ ቁምስና ውስጥ እሑድ ግንቦት 28/2014 ዓ. ም. መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች አሰቃቂ ጥቃት ማድረሳቸው ታውቋል። ዕለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉት ምዕመናን ዘንድ የጴንጠቆስጤ በዓል የተከበረበት ዕለት መሆኑ ይታወሳል። በዚያች አገር በምትገኝ ካቶሊካዊት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለደረሰው ከፍተኛ ጥቃት የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሰጡት ዝቅተኛ ሽፋን ለተጨማሪ ጥቃት የሚዳርግ እና እንደ "ሁለተኛ ደረጃ ስቃይ" በመመልከት ትኩረትን ካለመስጠት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በናይጄሪያ ውስጥ የበዓለ ሃምሳ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎታቸውን እሑድ ግንቦት 28/2014 ዓ. ም. በማቅረብ ላይ በሚገኙ ካቶሊካዊ ምዕመናን ላይ የወረደው አሰቃቂ አደጋ፣ በዋና ዋና የዜና ማሰራጫ ድረ-ገጾች ላይ ከወጡት ዜናዎች መካከል አለመታየቱ ብዙዎችን አሳዝኗል ተብሏል። “የአፍሪካ ሚዲያዎች አሳዛኝ ሁኔታዎችን ብቻ ሳይሆን በተለይም በአህጉሪቱ ውስጥ የሚታዩ ውብ እና አወንታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ለአሥርተ ዓመታት ያህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ ነበሩ” በማለት ብዙዎች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የአፍሪካ ሰብዓዊነት ለተፈጥሮ ሀብቶቿ ብቻ በርካታ ድብቅ ወይም ግልጽ ጥቅሞች ትኩረትን በመስጠት ችላ የተባለለት መሆኑ ተነግሯል።

በመስዋዕተ ቅዳሴው ጸሎት ላይ በነበሩት ምዕመናን ላይ የደረሰው አደጋን የሚያሳዩ የጅምላ ጭፍጨፋው ምስሎች አሰቃቂ እንደሆኑ ሲነገር፣ ረዳት በሌላቸው ሰዎች ላይ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መልኩ የተንሰራፋውን እና ብዙ ሕይወትን ያጠፋው አደጋ ሰለባ የሆኑትን ለመርዳት የተደረገ ዕርዳታ ዝቅተኛ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ከአደጋው ተጎጂዎች መካከል ብዙዎቹ ሕጻናት እንደነበሩ ታውቋል። ምዕመናኑ ላይ ለደረሰው ስቃይ ሙሉ በሙሉ ችላ ሲባል ማየት እና በአደጋው ለሚሰቃዩት ግዴለሽነትን ማሳየት እና ርኅራሄ ማጣትን መመልከት ብዙዎችን እንዳሳዘናቸው ታውቋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ለአፍሪካ ያላቸው ፍቅር

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መላዋ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሯትን ሐዋርያዊ ስልጣን ከተቀበሉ በኋላ ባቀረቡት የመጀመሪያ ጥሪ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክን በማስታወስ መናገራቸው ሲታወስ፣ በዚያም የምሕረት ኢዮቤልዩ ቅዱስ በርን መክፈታቸው ይታወሳል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ሰው ለድሆች፣ ከማኅበረሰቡ ለተገለሉ እና ለተረሱ ሰዎች ልባቸውን እንዲከፍት በማለት ደጋግመው ማሳሰባቸው እና በማሳሰብ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በበላይነት ለመምራት ሐዋርያዊ ስልጣናቸውን ከተቀበሉ በኋላ ከአፍሪካ አገራት የሚመመጡ በርካታ ስደተኞች በማስታወስ የጣሊያን የወደብ ከተማ ወደ ሆነች ላምፔዱሳ የመጀመሩያ ጉብኝት ማድረጋቸውም ይታወሳል።

የተዘነጉ ጦርነቶች እና የሕዝብ ስቃዮች

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በርካታ የተረሱ ጦርነቶች እና ቀውሶች በሌሎችም አካባቢዎች እንዳሉ የተገነዘቡ ሲሆን ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ሶርያ፣ የመን፣ አፍጋኒስታን፣ ምያንማር፣ ሄቲ እና ሌሎች አገራትም እንዳሉ ብዙ ጊዜ መግለጻቸው ይታወሳል። እሑድ ግንቦት 28/2014 ዓ. ም. መሣሪያ ታጣቂዎቹ በኦዎ ካቶሊካዊ ቁምስና ምዕመናን ላይ ያደረሱት ጥቃት፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ በትንቢተ ኢሳይያስ 62:1-12፣ ሰዎች በሙሉ አንድ ቀን የእግዚአብሔርን ፍትህ እንደሚያዩ፣ የተናቁት ከተሞች፣ የተረሱ እና የተገለሉ ሰዎች በሙሉ የአዳኙን የእግዚአብሔር ፍቅር በግልጽ እንደሚያዩ መገለጹ ተመልክቷል።

07 June 2022, 16:28