ፈልግ

ጸሎት እና የመንፈሳዊ መጽሐፍት ንባባት ጸሎት እና የመንፈሳዊ መጽሐፍት ንባባት 

በፓክስታን ውስጥ በሐሰት ክስ ለስምንት ዓመታት የታሠሩት ጥንዶች ነጻ ተለቀቁ

በፓኪስታን ላሆሬ ክፍለ ሀገር የእስልምናን እምነት ስም አሳንሳችኋል የሚል የሐሰት ክስ ለስምንት ዓመታት በእስር የቆዩት ሁለት ካቶሊካዊ ጥንዶች ነጻ መለቀቃቸው ሲነግር፣ ምዕመናኑ እ. አ. አ በ2021 ዓ. ም. ነጻ ከተለቀቁ በኋላ ታሪካቸውን በሮም ለሚገኝ አንድ የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን አብራርተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በፓክስታን ላሆሬ ክፍለ ሀገር የምትገኝ የሚያን መንደር ነዋሪ የሆኑት ሻፍጉታ እና ሻፍቃት እ. አ. አ ሐምሌ ወር 2013 ዓ. ም. የሐሰት ክስ ተመስርቶባቸው ለስምንት ዓመታት ከታሰሩ በኋላ ነጻ መለቀቃቸው ጥንዶቹ አስታውቀዋል። ከክርስቲያን ቤተሰብ መወለዷን እና ብዙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሚኖሩበት መንደር ተወልዶ ማደጓን የምትገልጽ ሻጉፍታ ወላጆቿ ጠንካራ ክርስቲያኖች መሆናቸውን አስታውቃለች።

ወላጆቼ እኔን እና ስድስት ወንድሞቼን እና እህቶቼን በእምነታችን እንድንጠነክር፣ ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁዎች እንድንሆን አስተምረውናል" የሚትለው ሻጉፍታ፣ በመንደሩ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች እንደ ብርሃነ ልደት እና ኢድ-አል ፈጥር ያሉ በዓላትን በጋራ እንዲሳተፉ የሚያስችል ባሕል ማሳደጋቸውን ገልጻለች። ጋብቻ ከፈጸሙ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ኑሮአቸውን ለማቅናት ወደ ሌላ አካባቢ መዛወራቸውን ሻፍቃት አስታውሶ፣ በሄዱበት አካባቢ ቀድሞ የለመዱት ባሕል አለማኖሩን እና አለመታደል ሆኖ በአገሪቱ በነበረው ውጊያ የመቁሰል ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ሻፍቃት ገልጿል። ከዚያን ጊዜው ወዲህ ሕይወት እየከበደ የመጣ ቢሆንም፣ በአቅራቢያው በሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ትምህርት ቤት መቀጠሯን ሻፍጉታ ገልጻለች። ትምህርት ቤት ሲዘጋ ቤተሰብን ለመደገፍ ባሏ የስልክ ጥገና ሥራ እንደጀመረ  የምትገልጸው ሻፍጉታ፣ እ. አ. አ በ2013 ዓ. ም. ውስጥ በቁጥር በርከት ያሉ ፖሊሶች ቤታቸው ገብተው እርሷ እና ባሏ፣ በስልካቸው በላኩት መልዕክታቸው የእስልምናን እምነት አዋርዳችኋል በሚል የሐሰት ክስ መታሰራቸውን ገልጻ፣ ተጻፈ የተባለው መልዕክት ምንም መናገር የማትችለው የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደነበር አስታውሳለች።         

እስር እና የሞት ፍርድ

እስር ቤት ውስጥ ግርፋት እንደደረባቸው የምትናገረው ሻጉፍታ፣ ጥፋታቸውን ካልተናዘዙ እና ካላመኑ በባሏ ፊት እንደሚደፍሯት ፖሊሶች ያስፈራሯት እንደነበር ገልጻ፣ ከጥቂት ወራት በኋላ ለሁለቱም የሞት ፍርድ መተላለፉን የገለጸችው ሽጉፍታ፣ ፍርዱ በቤተሰባቻቸው ላይ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ከመቻሉ በተጨማሪ፣ በፓኪስታን እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉትን ክርስቲያን ማኅበረሰብ በሙሉ ማስደንገጡን ገልጻለች።

እምነት ሳይጠፋ ሞትን መጠባበቅ

ሕይወቴ በጣም አስፈሪ እንደነበር የምትገልጸው ሻጉፍታ፣ በእስር ቤት ቆይታዋ ከዕለታት አንድ ቀን እርሷ እና ባሏ እንደሚሰቀሉ ታስብ እንደነበር ገልጻ፣ በእነዚያ አስፈሪ ወቅቶች ሁሉ እምነቷን እንዳላጣች እና ተስፋንም አለመቁረጧን አስረድታለች። “በየዕለቱ እጸልይ ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስን አነብ ነበር” የምትለው ሻፍጉታ፣ ይህ በጣም ያጽናናት መሆኑን ገልጻ “እኔና ባለቤቴ ንጹሐን ስለነበርን ሞትን ድል አድርጎ፣ በሶስተኛው ቀን የተነሣው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜ እኛን እንደሚያድነን፣ ከሞትም እንደሚያተርፈን እምነትና ተስፋ ነበረን” በማለት ገልጻለች። “የእስልምናን እምነት የምቀበል ከሆነ የሞት ፍርዴ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት እንደሚቀየር እና እንደምፈታ በተደጋጋሚ ተነግሮኛል” የምትለው ሻፍጉታ፣ “ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቴ እና አዳኜ ነው” በማለት አሻፈረኝ! ማለቷን ገልጻ፣ “ኃጢአተኛ ብሆንም ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለእኔ ሲል ሠውቷል” በማለት ምስክርነቷን ገልጻለች።

ነጻ መውጣት እና ስደት

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአውሮፓ ፓርላማ ላይ ኢ-ፍትሃዊነት በመቃወም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በችግር እና መከራ ውስጥ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ዕርዳታን የሚያደርግ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ጠንካራ ድምጽ ማሰማታቸው ይታወሳል። በተወሰነ ጊዜ አስያ ቢቢ የተባለች የፓኪስታን ተውላጅም እንዲሁ በሐሰት ክስ የሞት ፍርድ የተፈረደባት መሆኑን የምታስታውሰው ሻፍጉታ፣ ሲገናኙ አብረው ይጸልዩ እንደነበር፣ እርስ በርስ ይጽናኑ እንደነበር እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን  ጽኑ እምነት ያድሱ እንደነበር አስታውሳለች።

18 May 2022, 16:56