ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለ10 አዳዲስ ቅዱሳን የማዕረገ ቅድስና በሰጡበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለ10 አዳዲስ ቅዱሳን የማዕረገ ቅድስና በሰጡበት ወቅት  

የካፑችን ደናግላን ማሕበር ገዳም መስራች የሆነች ቅድስት ማሪያ ፍራንቸስካ ሩባቶ አጭር የሕይወት ታሪክ

ክፍል አንድ

ቅድስት ማረያ ፍራንቸስካ ሩባቶ ከአባትዋ  ከአቶ ቶማስ ሩባቶ እና ከእናትዋ ወ/ሮ ካቴሪና ፓቬስዮ እ.ኤ.አ የካቲት 14/1844 ዓ/ም በኢጣሊያ አገር  በካርማኞላ ከተማ ተወለደች። ሐናማሪያ በቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ቁምስና በዚያው በተወለደችበት ዕለት የምስጢረ ጥምቀትን ብርሃን በመቀበል ዳግመኛ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተወለደች። የልጅነት ስሟ ሃና ማሪያ ሩባቶ ሲሆን  ለወላጆቿ 7ኛ  ልጅ ነበረች።

ሐና ማሪያ በምስጢረ ጥምቀት  የተቀበለችውን እምነት ከቤተሰቦችዋ ካገኘችው ጥሩ ስነምግባርና አስተዳደግ ጋር መልካም የክርስትና ሕይወት እየኖረች በሁሉም ነገር የእግዚኣብሔርን ድምጽ በማዳመጥ ታከናውን ነበረች። ርህሩህ፣ ደግና ቅን ከሆነችው እናቷ፣ የቅንነትንና የአስተዋይነትን መንፈሳዊነት ተላብሳ እንዲታድግ አግዟታል። ገና ከልጅነት ዕድሜዋ ጀምሮ ሕይወቷ በመንፍሳዊነት የታነጸ፣ በደግነት የተሞላ፥ ድሆችን የሚትወድ፣ ለአቅመ-ደካሞች የተለየ ትኩረት የሚትሰጥ. . . ወዘተ እንዲሁም ከመጠን በላይ ለጋስ ስለነበረች  እናቷ ልግስናሽ ገደብ ይኑረው እያለች ትመክራት እንደነበረ፡ ሐናማሪያ ራሷ ትናገራለች።

 ሐናማሪያ የመንፈሳዊ ሕይወቷ መዓከል የሆነውን ክርስቶስን በበለጠ ለማወቅ እና ለመከተል፡ ነጻ በሆነ አእምሮና ልብ ለማገልገል፡ በድንግልና ህይወት እየኖረች ከኢየሱስ ፍቅር በቀር ሌላ ነገር በልቧ እንዳይነግስ በመንፈሳዊ ቆራጥነት ወስና ተነሳች።

ሐናማሪያ ገና በ4 ዓመት ዕድሜዋ አባቷ በ19 ዓመትዋ ደግሞ እናቷ በሞት ስትለያት የሕይወትን ውጣ ውረድ ከእያቷ ጋር ሆና በመለማመድ አደገች፡፡ በዚህ ምክንያት ከትውልድ አከባቢ ወጣ ብላ ከታላቅ እህትዋ ጋር ለመኖር ቶሪኖ ወደሚባል ከተማ ሄደች፡፡ በዚህ ከተማ አንድ የማርያም ጸሎት ቤት ጥዋት ጥዋት እየሄደች ቅዳሴ ታስቀድስ እና ትጸልይ ነበር፡፡ ገና ማህበሩን ሳትመሰርት በዶንቦስኮ የወጣቶች መዋያ ትምህርተ ክርስቶስን እያስተማረች ደግሞ ኮቶለንጎ በተባለው የሕመምተኞች ማከሚያ ጣቢያ እየሄደች በሽተኞችን ትንከባከብ ነበር።  

 የዕረፍት ጊዜዋን፣ ወደ ልዋኖ የሚባል ከተማ እየሄደች ታሳልፈው ነበር። ከእለታት፡ አንድ ቀን ጧት ወደ ቤተክርስትያን ስትሔድ በግንባታ ላይ ካለው ቤት አንድ ሰራተኛ ወድቆ ትጎድቶ ተመልክታ እየሮጠች ሄደችና፡ የመጀመርያ እርዳታ አድርጋ፡ ለማይሰራበት ቀናት ክፍያ ስጥታ ሄደች። በግንባታ ላይ የነበረው ቤት ማሪያ ኤሊቸ የተባለች የለዋኖ ከተማ ነዋሪ የሆነች ሀብታም ሴት ድሆችን የሚያገልግሉ የጥቂት ገዳማዊያን መኖሪያ እዲሆን የታሰበ ቤት ነበር። ስለሆነም የሐናማሪያ በጎ ተግባር የተመለከቱ የግንባታ ሰራተኞች ለኤሊቸ ስለሐናማሪያ በአድናቆት ስነግሯዋት “አንደዚህች ያለ ሰው ነው” እኔ የምፈልገው ማህበር ለመመስረት የሚያስፈልገኝ፡ ብላ አስቀድማ ወዳ አማከረቻቸው ወደ አባ አንጀሊኮ ሄደችና ነገረቻቸው። እርሳቸውም  ሐሳቡን ተቀብለው፡ ሐና ማሪያን ጠርተው ማህበር የመመስረት ሐሳብ ትቀበያለች ወይ? ብለው ጠየቋት። እርሷም ሃሳባቸውን ሰምታ፣ እስቲ እጸልይበታለው ብላ  በቶሪኖ ከተማ ከሚኖሩ  ከሁለቱ የነፍስ አብቶቿ  ጋር ተመካክራ፡ አንድአንድ ጥያቄዎችን ራሷን እንዲህ ስትል መጠየቅ ጀመረች።

“በኮተሊንጎ የጀመርኩን የበሽተኞች እንክብካቤ ልተው ነው ወይ? በደንቦስኮ የጀመርኩት የትምህርተ ክርስቶስ ማስተማርስ  ምን ላድርግው? ማህበሩንም የማስተዳደርበት የገቢ ምንጭስ ከየት ይመጣል? ማንስ ይረዳኛል?” . . የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ለራሷ ስታቀርብ ከቆየች በኋላ ለአባ አንጀሊኮና ለማሪያ ኤሊቸ እሺ እንግዲህ ይሁን ብላ አዎንታዊ መልስ ሰጠች። ነገር ግን ማህበሩን እየመራሁም ቢሆን ትምህርተ ክርስቶስ ማስተማርና ህሙማንን ማገልገል እቀጥላሉ ብላ መለሰችላቸው። በዚህ የሐሳብ ውጣውረዶች ሁሉ የአባ አንጅሊኮ መንፈሳዊ መሪነትና ምክር አልተለያትም ነበር።

በመሆኑም  ሐናማሪያ ከሌሎቹ 5  ወጣት ልጃገረዶች ጋር ለተወሰነ ቀናት ሱባኤ ገብተው ከጸለዩ በኋላ እ.ኤ.አ ጥር 23 1885 ዓ.ም.. ልብሰ ምንኩስና በመልበስ የሎዋኖ 3ኛ የካፑቺን ደናግል ማሕበር  መሰረተች። ከዚህ በኋላ ሐናማሪያ የሚል የቤተሰብ መጠሪያ ስም ቀርቶ፡ በምንኩስና ስም እህት ፍራንቸስካ የኢየሱስ ተብላ ተጠራች። እንደዚሁም አምስቱም ወጣት መነኮሳት የምንኩስና መጠሪያ ስም ተሰጣቸውና በክርስቶስ ፍቅር ተማርከው ተልዕኮዋቸውን ለመፈጸም በጋለ መንፈስ ተነሳስትው ህይወታቸውን በድህነት፣ በንጽህና እና በተአዝዞ ፡ለመኖር ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

 በእህትማማችነት ፍቅር፡ በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብ በመግባባት የሐዋርዊ ስራችውንና የጸሎት ሕይወት እየኖሩ፥ ልባቸውንና ቤታቸውን ለሁሉም፥ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶችና ድሆች ክፍት አድርገው ያስተናግዱ ነበር። ከዚህ የተነሳ የአከባቢ ነዋሪዎች በኑሯቸዉ ይማረኩ ነበር። በመሆኑም የእነርሱን ፈለግ የሚክተሉ ብዙ ወጣት ልጃገረዶችን የምንኩስና ሕይወት  መቀበል ጀመሩ።  ይህ ሆኖ ሳለ  የማሪያ ኤሊቸ ሐሳብና  የእህት ፍራንቸስካ ፍላጎት የማይገናኝ ሆነ። ማለትም ማሪያ ኤሊቸ የግቢው ጸጥታ እንዲጠበቅና  ለተወሰነ ሰው ብቻ አግልግሎት ለመስጠት ስትፈልግ፣ እህት ፍራንቸስካ በአንጻሩ፡ ገዳማቸው ለሁሉም ክፍት የማድረግ ፍላጎት ስለ ነበረ ሊግባቡ አልቻሉም። ስለሆነም ኤሊቸ ስጥቷቸዉ የነበረውን ቤትንና ንብረትን በሙሉ ወስዳ አስወጣቻቸው።  ይሁን እንጂ እህት ፍራንቸስካ፡ በዚህ ተስፋ ሳትቆርጥ “እግዚኣብሔር የተከለው ቤት በከንቱ አይወድቅም”፣ በማለት በእግዚኣብሔር ልግስናና ጥበቃ  ተማምና ሳለች ቀደም ሲል የምንኲስና ልብስ ያለብሷቸው የአልበጋው አቡን፣ አቡነ ፍሊጶስ አለግሮ፡ ማሕበሩን ለመቀጠል የሚያስፈልጋችውን ቤትና ቁሳቁስ በሙሉ በማመቻቸት ማሕበራዊ ሕይወቱንና አግልግሎታቸውን ኣንዲቀጥሉ አደረጓቸው።  

በዚህ ሁኔታ ማህበሩ በቁጥርም በመንፈሳዊነትም እያደገና እየጨመረ በመሄዱ በሌሎች የኢጣሊያን አውራጃዎችም ቤቶች በመክፈት የማሕበሩን መንፈስ  ማስፋፋት ጀመረች። ማሕበሩ ከተመስረተ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አባ አንጀልኮ የካፑቺን ካህን፡ ማበሩን ለማስፋፋት ባቀረቡላት ሐሳብ መሰረት እህት ፍራንቸስካ ከሶስት ወጣት እህቶች ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ላቲን አሜሪካ  ሞንተቪደዮ /ኡሩጋይ/ በመሄድ እ.አ.አ በ1892 ዓ/ም አዲስ ቤት ከፈቱ። ከተወስነ ጊዚያት በኋላ ሌሎች ስድስት እህቶች ተጨምሮላቸው ትምህርተ ክርስቶስን በማስተማር፣ የታመሙትን በመጎበኘትና በማከም፣ የተቸገሩትን በመርዳት የእግዚኣብሔርን መንግስት ማስፋፋት ቀጠሉ። በተለይም በዛ አከባቢ ትላልቅ ት/ት ቤቶችን በመክፍት ታዳጊ ሕጻናትን ስብስበው በዕውቅትና በስነምግባር አዲስ ትውልድን በማነጽ ይህን መንፈሳዊነት በእጅጉ አስፋፍተዋል። የእህት ፍራንቸስካ መንፈሳዊነት በት/ት ቤቱ ማሕበረስብ ብቻ ሳይሆን በመላው ሕብረተሰቡም ዘንድ  ሰርጾ መግባቱን ማሕበረሰቡ ስለ ፍራንቸስካ ሕይወት ከሚናገሩት መረዳት ይቻላል።                                      በዚህ መልኩ ወደ ብራዚል /በሰሜን ምስራቅ/ ወደ ሚገኝው ወደ ማራኛዎ  ከረጅም ዓመታት ጀምሮ  ይኖሩ የነበሩ የካፑቺን ወንድሞች አለቃ በኢጣሊያ አገር ለሚገኙ የማሕብር አለቃ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉላቸዉ። ምክንያቱም እነርሱ ለአከባቢው ወጣት ወንዶች የአናጺነትና የእጅ ሞያ ማሰልጠኛ ከፍተዉ ያስተምሩ ስለነበር ለሴቶችም የእጅ-ጥበብና የልብስ ቅድና ስፌት የሚያስተምሩ መነኮሳት ይፈፈለጉ ስለነበረ ነዉ። የደብዳቤዉም ይዘትም እንዲህ የሚል ነበር።

“ሶስት ለችግርና ለተጋድሎ ዝግጁ የሆኑ፣ ሙሉ ጤና ያላቸውና ከባድ ጉዞ መጋፈጥ የሚችሉ፣ በደሳሳ ጎጆ ውስጥ መኖር የማይቀፋቸው፣ ወተት፣ ቅቤና አይብ የመሳሰሉ ምግቦች የማይናፍቃቸው፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲሄዱ በደረቅ አልጋ ላይ መተኛት ቢያጋጥማቸው እንኳን የማይቆረቁራቸው እህቶች አስፈልገውን ነበር።እዚህ ቦታ ፍርሃት፣ መከራ፣ ማሀይምነት  እንድሚግጥማቸው የሚረዱ፣ አንድ ጊዜ እዚህ ቦታ ከመጡ በትዕግስትና በስነ-ልቦና ዝግጁነት እየስሩ ምንም የድካማቸው  ዋጋ ሳይጠብቁ መስራትና መሰዋዕትነትም ቢሆን እንደሚጠብቃቸዉ የሚገነዘቡ እህቶች ጥንካራ እምነት ያላቸው እህቶች አስፈልገውን ነበር” በማለት ልያጋጥማቸው የሚችሉ ሁኔታዎችን በመተንበይ ጽፈውላቸው ነበር።

 በኢጣሊያን የሚኖሩ የካፑቺን ወንድሞች አለቃ አባ በርናርዶ የተባሉ ይህንን መልእክት ባነበቡ ጊዜ፣ ከመቀራረባቸው የተነሳ እንደዚህ ያለ ሃላፊነት መወጣት የሚችሉ የካፑቺን እህቶች ብቻ ናቸው በማለት ወዲያው ለእህት ፍራንቸስካ ደብዳቤ ጻፉላቸዉ።

እናታችን ፍራንቸስካም በኡራጋይ/ ሞንተቭዲዮ ሳለች ይህንን መልዕክት ስትቀበል ልቧ በደስታ ተሞላ ምክንያቱም ለእግዚኣብሔር ያላትን ፍቅርና አግልግሎት በማራኛዎ ላሉት ማሕበረሰብ ለማዳረስ ዕድል በማግኘቴ ነው ብላ አግዚአብሔርን በማመስገን ለጉዞ መዘጋጀት ጀመረች።

በጣልያን አገር ላሉት የማሕበሩ አባላትም እንዲህ ስትል ጻፈችላቸው።

“እንግዲህ ጸሎት አድርጉ ወደ ወማራኛዎ ለምሄድ በመንፈስ የተገለጠላችሁ ካላችሁ ፍልጎታችሁን ግለጹ። እኔ የምለምናችሁ ግን ወደ እዚያ ለመሄድ የሚያስቡ እህቶች በቅዱስ ትሕትና ራሳቸዉን ያዝጋጁ።  እንዲሁም ደግሞ እውነተኛ ራስን የመካድና የመስዋዕትነት መንፈስ ይልበሱ። ወደዛ የሚትሄዱበት ምክንያት የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሳይሆን ጥሪያቸውን በቅድስና እየኖሩ የእግዚ/ርን መንግስት ለማስፋፋትና የወንድሞቻችን ነፍስ ለማዳን የሚል ግልጽ ዓላማ ይዘው መሆን አለበት”።  

ቀጥላ ደግሞ እዛ ለሚቅሩ እህቶች አንዲህ ሰትል ተማጸነቻቸው። “ወደ አዲሱ ቦታ ወደ ብራዚል (ማራኛዎ) ለመሄድ እየተዘጋጀን ነውና ወደዚህ ለሚመጡ እህቶች ከእነርሱ የሚጠበቀውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ከእግዚአብሔር ጸጋና ቡራኬ ለምኑላችው። የሚሄዱትም 6 እህቶች ሲሆኑ እነርሱም በጣም ደስትኞች ናቸው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ እኔ ራሴ እሽኛችዋለሁ” ብላ በተናገረችሁ መስረት እ.አ.አ በግንቦት 6/1899 ዓ/ም አብሯቸው ተጓዘች።         

እንደተባለውም በማራኛዎ የጠበቃቸው ቀላል ሕይወት ባይሆንም በመንፈስ ተዘጋጅተው ስለ ነበረ፥ በተለያየ ምክንያቶች ይህንን የተቀደስ አግልግሎት ከማይቀበሉ ሰዎች ጋር እየተጋፈጡ ሳሉ በ1901 ዓ/ም መጋቢት 13 ቀን በቅዳሴ ጸሎት ላይ እንዳሉ 7 ወጣት ደናግልና 2 የካፑቺን ወንድሞች እንዲሁም ደግሞ በርከት ያሉ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈው ተገደሉ። እህት ፍራንችስካ ምንም እንኳን ይህ ሁላ ሲሆን በቦታው ባትኖርም በመንፈስ የምሰዋዕትነቱ ተካፋይ ነበረች።

ሐናማሪያ በረጅም ጉዞና በተከታታይ የአየር ንብረት ሁኔታ በመቅያየሩ ምክንያት በጠና ታመመች። ከልብ ከሚታፍቅረው አምላክና ከቅዱሳን መላዕክት ጋር የሚትግናኝበት ጊዜ መቃረቡን ተግንዝባ ለሚትወዳቸው እህቶቿና የመንፈስ ልጆቿ የመጨርሻ ምክር አዘል የኑዛዜ ቃል እንዲህ ስትል ጻፍችላቸው፥

“በክርስቶስ የተወደዳችሁ ልጆቼ ይህ የምጽፍላችሁ በእግዚአብሔር መንፈስ የተገለጠልኝ አደራ ነው። እንደ አለቃም እንደ ታላቅ እህትም በድያችሁ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፣ የማሕበሩን የሕይወት መመሪያ ሕገደንብ ጠብቁ፡ እርስ በርሳችሁ በክርስቶስ ፍቅር ተዋደዱ፣ ማንኛውም ስራችሁን ስታከናውኑ፡ ስለ እግዚአብሐር ክብር ብላችሁ አከናውኑ፣ በሕይወቴ እነዚህን ወድጄ የፈጸሙኳቸው ሕጎች ስለሆኑ እናንተም ተግባራዊ አድርጓቸው፣ ማሕበራችንም በዚህ መንፍስ ይመራ። መሞቴን በተመለከተ በጥቂት ቃላቶች ብቻ የሚነገር ይሁን። እህት ፍራንቸስካ እግዚአብሄር ጠርቷት ዐረፈች፣ ስለ ነፍሷ ጸልዩ፣ ሌላ ቃላት እንዳትጨምሩ በእግዚአብሔር ስም እልምናችኋለሁ” ካላች በኋላ እ.አ.አ በነሐሴ 6/1904 ዓ/ም በኡራጋይ (ሞንትቭድዮ) ዐረፈች። ከሞትኩ በኋላ ሬሳዬም በድሆች መሃል እንዲቀበር ባለችዉ መስረት በኡሩጋይ/በሞንተቭድዎ ተቀበረች።

16 May 2022, 13:00