ፈልግ

የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች ስልጠና የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች ስልጠና 

የዓለም አቀፍ ማኅበራዊ ለውጥ ተዋናይ ስለ መሆን

በመጀመሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ቀጥሎም ጦርነት መከሰቱ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ቀውስን በማስከተል ለተጨማሪ ፈተናዎች የዳረገ ቢሆንም፣ እምነትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ድሆችን እና አቅመ ደካሞችን ከጥቃት ለመከላከል፣ ለፍጥረታት የሚደረገውን እንክብካቤ ተግባራዊ ለማድረግ ከተጀመረው ጥረት አንጻር፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስለ ሥነ-ምህዳር የተናገሩትን መሠረት በማድረግ ዘንድሮ ከሚያዝያ 12 እስከ ግንቦት 3/2014 ዓ. ም. ድረስ ለ “የውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ወደ አስከፊው ጦርነት የሚመሩ እጅግ በጣም ብዙ አሰቃቂ ነገሮች አሉ። ጦርነት ራሱ አስከፊ ገጽታ ነው። አመጽ ሞትን እና ጥፋትን ያስከትላል። የጦርነትን አስከፊነት የሰው ልጅ ጠንቅቆ ያውቀዋል። የለበሱትን ብቻ ይዘው የሚሸሹ፣ ይህን ለማድረግ እንኳን ጊዜን ያላገኙ፣ በግፍ የተገደሉ፣ አሰቃቂ የጦርነት አደጋ ለመመልከት የሚቸገሩ፣ በፍርሃት ውስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች አሉ።

በዓለማችን ከሚነሱ ግጭቶች የወረስነው ጦርነት፣ ጥሩን እና መጥፎ፣ ንጹህ እና ጥፋተኛ ሳይለይ በሁሉም ላይ ጉዳትን ያስከትላል። ጦርነት በከተማም ሆነ በገጠር እንዲሁም በጋራ መኖሪያ ምድራችን ላይ የሚያስከትለው ውድመት ከምንም ጋር ሊስተካከል አይችልም። ባሁኑ ወቅት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በመካሄድ ላይ የሚገኘው ጦርነት እውነት ሆኖ የሚያበቃ ከሆነ፣ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ታጥቀው በመነዳት በጦርነት የወደሙ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት፣ መንገዶችን ለመጠገን፣ በእሳት የወደሙ ጫካዎችን እንዲያለሙ ተጠርተዋል። ነገር ግን የልብን ቁስል ማን ሊፈውስ ይችላል? ኤሪ ዴ ሉካ የተባለ ታዋቂ ገጣሚ እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፥

ለበረዶ፣ ለእንጆሪ፣ ለዝንብም ሳይቀር ለሁሉም ዓይነት ሕይወት ዋጋን እሰጣለሁ። ለማዕድናት፣ ለከዋክብት፣ በጦርነት አደጋ ምክንያት ለተፈጠሩ ቁስሎች በሙሉ ዋጋን እሰጣቸዋለሁ። ውሃን ቆጥቦ መጠቀም፣ የተቀደደ ጫማ መጠገን፣ የዝምታ ጊዜን መምረጥ፣ ዋይታ እና ለቅሶ፣ ከመቀመጥ በፊት ፍቃድ መጠየቅ፣ የማን እንደሆነ ባላውቅም ምስጋናን ማቅረብ ጠቃሚ እና አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ።

እነዚህ እና ሌሎችም የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ ወይም ቀደም ሲል ዓለም አቀፍ ካቶሊካዊ የአየር ንብረት ለውጥ ንቅናቄ እሴቶች ናቸው። እነዚህን እሴቶች በደንብ የተገነዘበው እንቅስቃሴው፣ በየዓመቱ በባለሙያዎች እና በመምህራን አማካይነት ለ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች ዘንድሮ ከሚያዝያ 12 እስከ ግንቦት 3/2014 ዓ. ም. ድረስ ስልጠና ለመስጠት ማቀዱ ታውቋል።  

ዛሬ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ ወደ 9,000 የሚጠጋ ሲሆን፣ በ113 አገሮች በአምስቱም አህጉራት ውስጥ ሽንደሚገኝ ታውቋል። በጣሊያን ውስጥ ፕሮግራሙን የጀመረው በ2011 ዓ. ም. ሲሆን፣ በአውታረ መረብ በኩል ተገናኝተው ዕቅዱን በማስፈጸም ላይ የሚገኙ ከ2600 በላይ የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች መኖራቸው ታውቋል። በጣሊያን ውስጥ ብዙዎች ጊዜያቸውን በሙሉ ለ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ በመስጠት የሚሳተፉ እንዳሉ ታውቋል። ምዕመናን ያሉበትን አካባቢ እውነታ በመገንዘብ ከሚያቀርቧቸው አገልግሎቶች መካከል፣ ችግር ውስጥ ወድቀው የዕርዳታ እጆችን ለሚጠይቁ ድሆች እና አቅመ ደካሞች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት፣ በመንፈሳዊ ማኅበራት አማካይነት የጸሎት ሥነ-ሥርዓቶችን ማስተባበር እና ለስነ-ፍጥረት አስፈላውን እንክብካቤ ለማድረግ በተጨባጭ ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረቱ መሆናቸው ታውቋል።

የዝግጅቱ ዋና ጭብጥ

እንቅስቃሴው ዘንድሮ በባለሙያዎች እና በመምህራን በመታገዝ ለ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች የሚያቀርበው ስልጠና ጭብጥ "እስራኤል ሆይ አድምጠኝ” በሚል መሪ ቃል ላይ የተመሠረተ እና ከልብ ማድመጥን የሚያሳስብ መሆኑ ታውቋል።

ለተሻለ ዓለምን ለመገንባት ዋና ተዋናይ መሆን

"የ ‘ውዳሴ ላንተ ይሁን’ እንቅስቃሴ አስተባባሪ አባላት በዓለም ዙሪያ የሚገኘውን ካቶሊካዊ ማኅበረሰብ ለማነሳሳት እና ለመቀስቀስ የተጠሩት መሆናቸውን የገለጹት፣ በጣሊያን ውስጥ የአውሮፓ ፕሮግራሞች ተባባሪ ዳይሬክተር እና የፕሮግራሙ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሲሲሊያ ዳል ኦሊዮ፣ ሲኖዶሳዊ ሂደቱ እንቅስቃሴው ከሚያራምዳቸው እውነታዎች ጋር አብሮ የኖረ ነው” በማለት አስረድተዋል።

ዘንድሮ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ የሚሳተፉ የ “ውዳሴ ላንተ ይሁን” እንቅስቃሴ አስተባባሪዎች፣ “በሲኖዶሳዊ ጉዞ በምትመራ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኅብረት፣ ተሳትፎ እና ተልዕኮ” ቤተ ክርስቲያን የተጠራችበት የአገልግሎት ጥሪ አካል መሆኑን በመገንዘብ የብዝሃ ሕይወት ሃብት፣ ቤተክርስቲያን ከራሷ እውነታዎች በመነሳት እንክብካቤዋን መስጠት እንድትችል እንደ እርሾ የሚያግዛት መሆኑን አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መስከረም 8/2014 ዓ. ም. ለሮም ሀገረ ስብከት ምዕመናን ባቀረቡት ግብዣ፣ “በወረርሽኙ ወቅት ቤተክርስቲያን የምታቀረበው የእንክብካቤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸው፣ መላው ዓለም ተጋላጭነቱን በመግለጽ ድምጹን ከፍ ጩሄቱን በሚያሰማበት በዚህ ወቅት እንክብካቤ ሊደረግለት ያስፈልጋል ማለታቸው ይታወሳል።

28 March 2022, 16:44