ፈልግ

የውርጃ ተቃውሞ እንቅስቃሴ በሰሜን አሜሪካ የውርጃ ተቃውሞ እንቅስቃሴ በሰሜን አሜሪካ 

የሰሜን አሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ውርጃን በመቃወም ድጋሚ ጥሪ አቀረቡ

የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት፣ የባይደን አስተዳደር “የተሻለ እርምጃን ይውሰዱ!” በሚል መሪ ቃሉ፣ የህዝብ ገንዘብን ለውርጃ አገልግሎቶች ማዋሉን በመቃወም ለአሜሪካ ኮንግሬስ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ከዚህ በፊት የገለጹትን አቋም በመድገም፣ ጳጉሜ 2/2013 ዓ. ም ለአሜሪካው ኮንግሬስ በላኩት መልዕክት፣ በመጪው የበጀት ዓመት የግብር ከፋዮችን የገንዘብ ድጋፍ ፅንስ በማስወረድ ተግባር እንዳያውሉት በማለት የሕግ አውጭዎችን ጠይቀዋል። የብጹዓን ጳጳሳቱ መልዕክት በውስጡ ከያዛቸው ርዕሠ ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ “ያልተወለደውን የሰው ልጅ ሕይወት ለማበላሸት መንገድ የሚከፍቱ የገንዘብ ድጋፍ ሕጎችን ማጽደቅ እንደሌለባቸው ሴናተሮችን እና የግዛት ተወካዮችን አሳስበዋል። እነዚህ ድንጋጌዎች በበጀቱ ረቂቅ ውስጥ የሚካተቱ ከሆነ ብጹዓን ጳጳሳቱ አጥብቀው የሚቃወሙት መሆኑን አስታውቀዋል።

ለውርጃ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አሁንም አሉ

ሆኖም፣ የኮንግሬሱ ኢነርጂ እና ንግድ ምክር ቤት “የተሻለ እርምጃን ይውሰዱ!” የሚለውን መሪ ቃሉን መሠረት በማድረግ፣ መስከረም 5/2014 ዓ. ም ባስተላለፈው የግብር ክፍያ መንገዶች እና የፕሬዚዳንት ባይደን መልሶ ግንባታ ሕግ በሚለው ረቂቅ ውስጥ ውርጃን ለመደገፍ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ድንጋጌዎች ሳይወገዱ ማሻሻያዎች ብቻ መደረጋቸው ታውቋል። ላለፉት 40 ዓመታት ያህል ፣ ይህ የሁለት ወገን የሕግ አውጭ ድንጋጌ፣ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ አንዳንድ ልዩነቶችን ፣ ፅንስ ለማስወረድ የሚውል የፌዴራል ገንዘብ ክፍያን አግዶ መቆየቱ ታውቋል።

አሜሪካውያን ለውርጃ እንዲከፍሉ መገደድ የለባቸውም

የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ድርጊቱን በጥብቅ በመቃወም ለኮንግሬሱ በሰጡት ምላሽ፣

“የተሻለ እርምጃን!” በሚል ሰበብ የግብር ከፋዮችን የገንዘብ ድጋፍ ፅንስን በማስወረድ ተግባር ላይ ማዋል እንደሌለባቸው አሳስበዋል። ብጹዓን ጳጳሳቱ አክለውም “የተሻለ እርምጃን ይውሰዱ!” በሚለው መመሪያ ውስጥ በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ለችግር የተጋለጡ ሰዎች የጤና እንክብካቤ ሽፋንን ለማሻሻል ለሚያልሙ ሌሎች እርምጃዎች ድጋፋቸውን በድጋሚ ገልጸው፣ ነገር ግን ፅንስን ለማስወረድ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ድንጋጌ ከደንቡ እንዲወገድ ወይም እንዲሰረዝ በማለት አጥብቀው ጠይቀዋል።

የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት   

ለሁሉም የኮንግሬሱ እና የአስተዳደሩ አባላት ባቀረቡት ጥሪ፣ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ገና ያልተወለደ የሰውን ሕይወት ሆን ብሎ ለመግደል አሜሪካዊያንን ሳያስገድዱ አስፈላጊ እና ሕይወት አድን የጤና እንክብካቤ አቅርቦቶችን ለማራመድ በቅን ልቦና መሥራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት መግለጫን በፊርቸው ያጸደቁት፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጆሴፍ ኖማን፣ የሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ እና የሕይወት እንክብካቤ ኮሚቴዎች ሊቀ-መንበር ሲሆኑ ከእርሳቸው ጋር ሆነው ፊርማቸውን ያኖሩት፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ኤስ ኮክሌይ፣ በሰሜን አሜሪካ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ውስጥ የአገር ውስጥ ፍትህ እና የሰብዓዊ ልማት ኮሚቴ ሊቀ መንበር መሆናቸው ታውቋል።         

23 September 2021, 17:17