ፈልግ

በጃፓን የሂሮሽማ እና ነጋሳኪ ተጥሎ የነበረው የኒውክለር ቦምብ መታሰቢያ በተዘከረበት ወቅት በጃፓን የሂሮሽማ እና ነጋሳኪ ተጥሎ የነበረው የኒውክለር ቦምብ መታሰቢያ በተዘከረበት ወቅት  

ጃፓን ኒውክለር ጥቃት ከደረሰባት ጊዜ ጀምሮ እስከ የኦሎፒክ ውድድር የማዘጋጀት ጉትት ድረስ

የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ሲጠናቀቅ አገሪቱ በዚህ ዓመት እ.አ.አ ከነሐሴ 24 እስከ መስከረም 5/2021 ዓ.ም  ድረስ የሚካሄደውን ከኦሎፒክ ውድድር ቀጥሎ የሚከናወነውን የፓራኦሎፒክ ጨዋታዎችን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ጃፓን እ.አ.አ በነሐሴ 1945 ዓ.ም በአግሪቷ ላይ የተፈጸመውን የኒውክሌር ጥቃቶችን ለማስታወስ ታቅዶ የሚከናወን ዝግጅት ነው። ከአባ አንድሪያ ሌምቦ ጋር የቫቲካን ሬዲዮ ባደረገው ቃለ ምልልስ በኦሎፒክ ውድሮች ላይ የሚበራው የእሳት ነበልባል “ያ ነበልባል የሰላም መልእክት ነው ፣ በየዓመቱ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ቃላት ያስታወሳሉ” ማለታቸውን ቃለ ምልልሱን ያከናወነው የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ እንድሪያ ዲ አንጄሊስ ገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በጃፓን ዛሬ ሰኞ እ.አ.አ ነሐሴ 9/2021 ዓ.ም በጣም ልዩ የሆነ ቀን ነው። እ.አ.አ በነሐሴ 6/1945 ዓ.ም የዛሬ 76 አመት ገደማ ማለት ነው በናጋሳኪ እና በሂሮሺማ ላይ ተቃቶ የነበረው የኒውክለር ቦንብ ፍንዳታ እየተዘከረ ይገኛል።  የትካዜ፣ የሐዘን እና የጸሎት ወቅት እንደ ሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ሲሆን ከዚህ አስከፊ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ጥቃት የተረፉ ሰዎች ድምጽ በየዓመቱ ለማዳመጥ ዕድሉን የሚከፍት ወቅት ነው። አሁንም እነዚያን ክፉ የሆኑ ቁስሎች ከትውልድ እስከ ትውልድ በልባቸው እና በአካላቸው ውስጥ የሚሸከሙትን ሰዎች ምስክርነት ለማዳመጥ እድሉን የሚከፍት ወቅት ነው። በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው አመት እ.አ.አ. በ2020 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው ይህ የመታሰቢያ ዝግጅት ለአንድ ዓመት ያህል ከተራዘመ በኋላ የቶኪዮ 2020 ዓ.ም ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ማብቃታቸውን ተከትሎ ዛሬ ማለትም እ.አ.አ. ነሐሴ 09/2021 ዓ.ም በይፋ የተጀመረ የፓራኦሎፒክ ዝግጅት ነው። በተመሳሳይ ወቅትም የረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታ በማንገብ ከዚህ በፊት በናጋሳኪ እና በሂሮሽማ ላይ ተጥሎ በነበረው የኒውክለር ቦምብ ምክንያት በደረሰው ከፍተኛ አደጋ ሐዘን የተሰማቸው ሰዎች በዚህ ለሁለት ሳምንታት ያህል በሚካሄደው የፓራኦሎፒክ ዝግጅት ላይ ሕመማቸው እና ሐዘናቸው ወደ ደስታ እና መልካም አጋጣሚ እንዲያመራ የሚያደርግ ዝግጅት እንደ ሆነም ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል።

ቶኪዮ 2020 ደስታ ከጸጸት ጋር ተደባልቋል

ቶኪዮ የኦሎፒክ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ በተመረጠችበት ጊዜ አገሪቷ በታሪክ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ያገኘቺው እድል መሆኑን ማስታወሱ ጠቃሚ ሲሆን የመጀመሪያው በቶኪዮ የተከናወነው ኦሎፒክ እ.አ.አ በ1964 ዓ.ም ላይ ነበር፣ በዚህ ኦሎፒክ ላይ ኢትዮጲያዊው ጀኛው አበበ ብቂላ ተሳትፎ ማሸነፉ ይታወሳ፣ ይህ አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በቶክዮ የተደርገው ቶኪዮ 2020 ከዚህ በፊት ከተከናወነው ኦሎፒክ ጋር ሲነፃፀር ፍጹም የተለየ ክስተት እንደ ነበረ እየተዘገበ ይገኛል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ኦሎምፒክ ውድድር ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ ከማድረጉም በላይ ስታዲየሞች ፣ የአትሌቲክስ መሮጫ መስመሮች እና የስፖርት አዳራሾች ለሕዝብ ዝግ የመሆን ምክንያት ሆኗል። ከጨዋታዎቹ ጋር የነበረው ድባብም ሆነ ሊገኝ የታሰበው ገቢ እንዲሁ ከቱሪዝም እና ከስፖንሰሮች ጋር በተገናኘ መልኩ ሊገኝ የነበረው ከፍተኛ የገንዘብ ገቢ ሳይገኝ መቀረቱ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል። ሆኖም የኦሎምፒክ መንፈስ አሸንፏል፣ ስለሆነም በእነዚህ ቀናት ውስጥ ብዙ የወዳጅነት እና ፍትሃዊ ታሪኮች ተነግረዋል ፣ በዙ መልካም የሚባሉ ስሜቶች ተንጸባርቀውበታል። ነገር ግን ዛሬ በቶኪዮ ውስጥ ያለው ድባብ ምንድነው? በጃፓን ከ 10 ዓመታት በላይ እንደ ኖሩ የተናገሩት ሚስዮናዊ አባት አባ አንድሪያ ሌምቦ ይህንን ጥያቄ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይመልሳሉ።

“ኦሎምፒክን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፉ በእርግጥ የድርጅታዊ መዋቅር ችግሮችን ብቻ ሳይሆን የሕዝቡ ጉጉት እንዲቀንስ አድርጓል፣ እናም መምጣት የነበረባቸውን ብዙ ቱሪስቶች በማስተናገድ ሊገኝ የነበረው ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ንዋይ ሳይገኝ በመቅረቱ የተነሳ ይህንን የኦሎፒክ ዝግጅት ለማዘጋጀት የወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ሳይተካ ቀርቷል። ማሕበራዊ እንቅስቃሴ እንዲገታ ያደርገ ቀዝቃዛ ስሜት የተንጸባረቀበት ኦሎፒክ ነበር። ነገር ግን ኦሎፒኩ ከተጀመረ በኋላ ፣ የአትሌቶቹ ጥረት ፣ ቁርጠኝነት ፣ መስዋዕትነት በሕዝብ መገናኛ ብዙኃን በተደርገው ስርጭት ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሮ ነበር” በማለት አባ አንድሪያ ሌምቦ ተናግረዋል።

ፓራኦሎፒክ እ.አ.አ በነሐሴ 25/2021 ዓ.ም ይጀመራል። ለዚህ ዝግጅት በአገሪቱ ውስጥ ምን ይጠበቃል? ለሚለው ጥያቄ ለአባ አንድሪያ ምላሽ የሰጡ ሲሆን እነዚህ ጨዋታዎች “በጣም የተጠበቁ ናቸው ፣ ከኦሎምፒክ የበለጠ እንኳን ሕዝቡ የሚጠብቃቸው ጨዋታዎች ናቸው ለማለት እችላለሁ” በማለት የመለሱ ሲሆን ምክንያቱ ሁለት ነው “በአንድ በኩል ቀናቶቹ በጃፓን ውስጥ ካሉ ረዥም በዓላት አንዱ ጋር ይጣጣማሉ ፣ ስለዚህ ብዙ የቴሌቪዥን ተመልካቾች ይኖራሉ። ነገር ግን ከሁሉም በላይ የጃፓን ህብረተሰብ ለአካል ጉዳተኞች ብዙ ትኩረት ይሰጣል፣ ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህ በዚህ ክስተት ጃፓን ይህንን አዎንታዊ ሐሳብ ለማስተጋባት ለአቅመ ደካሞች ፣ ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት ፣ በትውልድ ወይም በአጋጣሚ የተለየ ፣ አስቸጋሪ ሕይወት ላላቸው ፣ ነገር ግን በዚህ ሕይወት ላይ ውድድር፣ ጨዋታ ፣ ጥረት ለሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው፣ ይህ ደግሞ የእነርሱ ታላቅ ተነሳሽነት ነው ፣ እነሱ ድፍረትን እና ተስፋን ፣ በወስንነት ውስጥ ራስን የማሸነፍ ችሎታ ፣ ወደ እውነተኛ ሰብአዊነት እንደሚመራን ያምናሉ። ሁል ጊዜ ወደ ፊት መጓዝ ፣ አንድ ነጥብ ላይ መድረስ ፣ አስፈላጊ መሆኑን እጅግ በጣም ያምናሉ። ታላቅነትን በሚጠይቅ ማህበረሰብ ውስጥ ፣ በጥራት ላይ የተመሠረተ እውነታ ፣ እነዚህን የፓራኦሎፒክ አትሌቶችን ማየት ለሁሉም ትልቅ ማበረታቻ ይሆናል። በተለይ ለታዳጊዎች። ለአዲሶቹ ትውልዶች የወደፊቱን መገንባት ቀላል አይደለም ፣ ይህ ለወጣቶች ሕይወት እውነተኛ ማበረታቻ ሊሆን ይችላል” በማለት አባ አንድሪያ ሌምቦ ከልጸዋል።

ከአቶሚክ ቦምብ እስከ ኦሎምፒክ እሳት ነበልባል

ስለዚህ ጃፓን አዳዲስ ስሜቶችን ለመለማመድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች ፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ ታሪኳን በጣም የሚያሠቃየውን ገጽ ለማስታወስ ተጠርታለች - ይህም አሜሪካ በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ የጣለችው የአቶሚክ ቦምብ የናጋሳኪ ሊቀ ጳጳስ ሞንሰንጎር ጆሴፍ ሚትሱኪ እንዲሁ ለቫቲካን ሬዲዮ - ቫቲካን ኒውስ ላይ የተናገሩትን አጋጣሚ እና አባ አንድሪያ በተመሳሳይ መልኩ እንደ “ዕድለኛ እና ቆንጆ አጋጣሚ” የሆነ ነገር አድርገው ይመለከቱታል።  እንዲሁም ባለፈው ወር የጃፓን ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በአቶሚክ ቦምብ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ተከታታይ ማህበራዊ እና የጤና ቀውስ የደረሰባቸው ሰዎች ማሕበራዊ ጥቅሞች እንዲያገኙ የወሰነ ሲሆን በዚህ መሰረት በዚያ የኒውክለር ጥቃት ምክንያት ዛሬ ዕጢዎች ወይም ሌሎች በሽታዎች ያሏቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የአቶሚክ ቦምብ ሰለባ ከሆኑት በሺዎች ከሚቆጠሩ በሕይወት የተረፉት ሰዎች ጋር ይቀላቀላሉ ማለት ነው፣ ይህም ማለት የመኖሪያ ቤት የማግኘት እድል ይኖራቸዋል እንደ ማለት ነው። ጥቃቱ የዚያ አሳዛኝ ውጤት በአንድ ትውልድ ወይም በአንድ የተወሰነ ርቀት ላይ ብቻ እንደማይቆም የሚያሳይ አጋጣሚ ነው። ከዚያም አባ አንድሪያ ሌምቦ እ.አ.አ ከነሐሴ 9/2021 ዓ.ም ጀምሮ የሚከናወነው ፓራኦሎፒክ እ.አ.አ በነሐሴ 1945 ዓ.ም ከተፈጸመው የኒውክለር ቦምብ ጣቅት ጋር በማያያዝ የፓራኦሎፒክ ጨዋታዎች አስፈላጊነት ላይ ያሰምሩበታል። “በየዓመቱ አገሪቷ ሰላምን እና የጦርነትን አላስፈላጊነት ቆም ብላ ታሰላስላለች። ሁል ጊዜ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቃላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን መልእክት ይታወሳሉ። በዚህ ረገድ ቤተክርስቲያኗ ወሳኝ ሚና ትጫወታለች፣ በኒውክሌር ኃይል እና በኒውክሌር የጦር መሣሪያ ይዞታ ላይ በማሰላሰል ታላቅ አስተዋፅኦ ታደርጋለች” ማለታቸው ተገልጿል።

ከወጣቶቹ ጎን

ካለፈው ወር ጀምሮ አባ አንድሪያ ሌምቦ እ.አ.አ. በ 1930 ዎቹ ውስጥ የቶኪዮ ሀገረ ስብከት ወጣቶችን ሰብዓዊ እና ክርስቲያናዊ እድገት እንዲኖራቸው እንዲረዳቸው ፣ የመገናኛ እና የመወያያ ጊዜዎችን ለማስተዋወቅ የተቋቋመው ማዕከል አዲስ ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ማዕከሉ ሺንሴይካይካን ወይም እውነት እና ሕይወት በመባል ይታወቃል። “በዚያን ጊዜ ወጣቶች በጣም ጠንካራ በሆነ ኢምፔሪያሊዝም ሥር ፣ በሀሳብ ልዩነት ውስጥ ሁኔታ ይኖሩ ነበር። ባለፉት ዓመታት ቅዱስ ወንጌልን ማሳተዋወቅ የፈለገው ይህ ማዕከል እያደገ ይገኛል።  ኢየሱስን እና ወንጌልን ከሁሉም በላይ በሰው ጉዞ እጅግ አስገራሚ ተሞክሮዎችን ለሚኖሩ ሰዎች ለማምጣት እየጣረ የሚገኝ ማዕከል ነው። በበሽታው ወረርሽኝ ምክንያት ችግር እየጨመረ በሚሄድበት ዓለም ውስጥ ሁል ጊዜ ለችግረኞች ቅርብ ለመሆን እና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ በማሰብ ለሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ፣ ቅዱስ ወንጌል እንደ ኦክስጅን እስትንፋስ አድርጎ በመስጠት ሊያድግ የሚችል ዘር እንዲሆን ታስቦ በተለያዩ ባህሎች ፣ ቋንቋዎች ፣ ወጎች ወንድሞች መካከል የእውነተኛውን ገጠመኝ ውበት ለማንጸባረቅ የሚሰራ ማዕከል እንደ ሆነ አባ አንድሪያ ሌምቦ አክለው ገልጸዋል።

09 August 2021, 15:35