ፈልግ

ደስተኛ ቤተሰብ የማሕበረሰብ መሰረት ነው! ደስተኛ ቤተሰብ የማሕበረሰብ መሰረት ነው! 

የቤተሰብ ደስታ

ወደ ቤተሰብ ደስታ ዉስጥ ከመግባተ በፍት ደስታ የሚለዉ የቃሉ ትርጉም ለመናገር እወዳለሁ። ደስታ የምለዉ ቃል በግርክ ስረዉ ቃሉ “ቻራ (chara)” ሲሆን በትርጉሙ ቻረስ (charis) ከሚለው የግርክ ቃል ጋር አቻ ነዉ ፡፡ቻረስ ጸጋ ከሚለዉ ቃል ጋር ተቀራራብ ፍቺ አለው። ደስታ የሚለዉ ቃል የእግ/ር ሥጦታን እና ለዚህ ሥጦታ የምንመልሰዉን ምላሽ ጠቅልሎ ይይዛል። ደስታ ከእንግልዘኛ ቃል ሃፕ ትርጉሙም “መልካም ዕድል” ማለት ነዉ፡፡ለቡዙዎቹ ደስታ ስሜትን ሳይሆን መልካም ዕድልን ያመለክታል ፤ በራሱ ደስተኛ ማለት አስደሳች ወይም እርካታ ያለዉ ነገርን ያመለክታል፡፡ ደስተኛ ቤተሰብ ስንል በጥሩ ዕድል የተከለሉ አስደሳች ዉጤትን የተጎናጸፈ፤ ዉሰጣቸዉ በሙሉ ብርሃን እንደ ፈካ ጸገረዳ አበባ በፈገግታ የሞሉ ስኬታማ ቤተሰብ ማለት ነዉ፡፡

ይህ ዓመት የቅዱስ ቤተሰብ ዓመት ተብሎ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቺስኮስ ተሰይመዋል፡፡ቅዱስ ቤተሰብ ስንል ኢየሱስ ማርያም እና ዮሴፍ ናቸዉ ፡፡ከቤታቸዉ ደስታ ሙሉ ነበረ እነሱ ለሞላዉ ክርስቲያን ቤተሰብ ምሳሌ ናቸዉ ፡፡በቤታቸዉ ደስታ ሙሉ የሆነዉ ሁሉም የዓለም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም፤የምተዳደሩት በዮሴፍ አናጽነት ሙያ ነበረ፡፡ግን ቤተሰቡ ደስተኛ የሆነበት ምክንያት እነሱ ሙሉ በሙሉ ለእግ/ር እና በሕይወታቸዉ ለተጠሩት ጥር ታማኝ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡

ደስታ ገንዘብ የማይገዛው በድርድረ የማይገኝ øከዉስጥ እንጂ ከዉጭ የማይመጣ የዋጋ ተመን የሌለዉ ትልቅ ሀብት ቢኖር ደስታ ነዉ፡፡ደስተኛ ሆኖ መኖርን የማይመኝ የለምው ሁሉም  ሰው በየፍናው ደስታን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡ አንድ ትልቅ ዓለም አለ! ይህ ቤተሰብ የሚኖርባት ፕላነት ምድር ወይም ዩኒtርስ ነዉ ! ቀጥሎ ደግሞ አንድ ትንሽ ዓለም አለ ፤ ይህም የምንኖርበት ማህበረሰብ ነዉ። እና በዚህም  ደግሞ እንደገና አንድ ትንሹ ዓለም አለ ! ያም ዓለም ያልኩት ቤተሰብ ነዉ ! ቤተሰብ በሕይወት ሁል ጊዜ የምኖርበት ዓለም ወይም መንደር ነዉ፡፡በእሱ ደግሞ የእኔ መኖር የሚታወቀዉ ዋና ማዕበሉ በዉስጡ ደስታ ስኖር ነው። ደስተኛ ቤተሰብ ሆኖ መኖር ከምንም ሀብት በላይ ነው፤ ቤተሰብን እዉነተኛ ቤተሰብ የሚያደርገዉ ያለዉ ሀብት ብዛት ሳይሆን በዉሰጣቸዉ ያለዉ ደስታ መጠን ነው።

ደስተኛ መሆን ተጫዋች ወይም ፍልቅልቅ መሆን ብቻ እንደምያመለክት አድርገን ልናስብ አይገባም፡፡ሁነታዉን በምሳሌ ለማስረዳት “ሰካራም የሆነ ሰዉ ብዙ ስጠጣ ሳቅ ሳቅ ሊለዉ ይችላል” ስካሩ ስበርድለት ግን መሳቁን አይቀጥልም ፤ምክንያቱም በሐዘንና በችግር ከተሞላዉ ሕይወት ማምለጥ አይችልም ፤ይህ ሰዉ ለጊዜዉ ቢፈነድቅም እዉነተኛ ደስታ ነበረዉ ማለት አይቻልም። በምሳሌ መጽሐፍ ምዕርፍ 14፡13  ላይ ከዚህ በተቃራኒ ደስታ ከልብ የመነጨ ጥልቅ ስሜት ነዉ ፤ደስታ ጥሩ ነገር ከማግኘት ወይም አገኛለሁ ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስሜት ነው።

ደስታ በግድ ማንቁርቱን ይዘህ የምታመጣዉ አዉራ ዶሮ አይደለም። በግድ ደስተኛ ለመሆን ጥረት የምያደርጉ ሰዎች፤ ጥንቸል ላይ የከባድ መኪና ጡሩንባ እያንባረቁ ጥንቸሏን ከእቅፍቸዉ እንድትገባ የሚናፍቁ  ሰዎችን  ይመስላሉ። ለብዙዎቹ ደስታ የምርጫ ጉዳይ ነዉ። ደስተኛነትነ የጥረት ፍሬ ናት፤ ደስተኛ ለመሆነ የምፈልግ አካል (ሰው) ብዙ መድከም እና መስራት ያስፈልጋል። በፈተና ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ የሚፈልግ ተማር ቀን ተሌት ብዙ መጽሐፍትን ማንበብ ፤መድከም አለበት። ደራስ ኤልዛቤት ጊልበርት (eat,pray and love) ብላ፣ ጸልይ እና አፍቅር በተሰኘዉ መጽሐፍ ላይ ደስታ የጥሬት ዉጤት ነው ይላል። ትታገላለህ ! ትሟሟታህ ፤አንዴንደም ተነስተህ ፍለጋ ትወጣለህ ፤አገር፣ አህጉር ባህር ታቋርጣለህ፡፡ በረከትህን ለመቀበል ቁጭ ብለህ አይሆንም ፤ መቃረም አለብህ፤ልክ የደስታን ጅረት ስትጨብጠዉ    እንዳተለቀዉ ከባድ ጦርነት መግጠም ይኖርብሃል።

በሐሴት የተነጠፈ የዋና ዉሃ ላይ ለመንሳፈፍ የሚትችለዉን ሁሉ ማድረግ አለብህ፤ አለበለዚያ ትሰጥማለህ፡፡ክርስቲያን ቤተሰብ ደስታ ፍለጋ ብሎ መዉጣት የለባቸዉም፤ ደስታው በውስጣቸው፣ በቤታቸዉ መሆኑን መረዳት አለባቸዉ ! በቤታቸዉ የጌታችን የክርስቶስ ጸጋ እና ፍቅር ካለ ሙሉ ደስታ ይኖራል። ደስታ ፍለጋ ብሎ የወጣ ሰዉ ባዶ እጁን ይዞ ይመለሳል፣ ደስታ በፍለጋ የምገኝ ነገር አይደለም። ለደስታ ፍለጋ ብለዉ የምወጡ ሰዎች በብቸኝነት እና በጭንቀት ይሞታሉ ፤ ከሀገር ሀገር፣ ከአህጉር አህጉር ይንከራተታሉ ግን ልረኩት አይችሉም። ደስታ የግል ጥረት ነዉ የሚባለው ለዚህ ነው።

በዕድሜ እየበሰልን ስንሄድ ፉፁም ደስተኞች እንድሆን የሚያስችለን የተሟላ ሕይወት ስንኖር መሆኑን እንገነዘባለን። ይሁን እንጂ ምም እንኳን ደስታን የመፈጠርያ ተፈጥሮዋዊ እምቅ ኃይል ሁሉም ሰዉ ዉስጥ ቢኖርም ያንን ደስታ እንዴት ማግኘት እና ማቆየት እንደምንችል ለብዙዎቻችን ተሰዉሮ ሊኖር ይችላል።ባለፈዉ የደርሰባቸዉን የውድቀት ህመም ያልረሱ ሰዎች ሁሉን ነገር ስያማርሩ ይታያሉ። ይህም የባለፈዉ ቁሱሎቻችን እና ሃዘኖቻችን በመርሳት የምመጣ ዉጤት ነዉ፤ ይህ ዓይነት ድርግት ለቤተሰብ ደስታን አይሰጥም ፤ ድርግቱም በእንግልዘኛ የላይፍ እንርችሜንት ይባላል ፤ ትርጉሙም ሰዎች ለትላንት ክስተት ተጠቂ መሆን ማለት ነው። (ለምሳሌ ያህል የመጠጥ ሱስ፤ የወስብ ሱስ፤የመብላት...ወዘተ ይሆናሉ)

የክርስቲያን ሕይወት በጭራሽ በስሜቶች ላይ የተመሠረተ መሆን የለበትም ፤ግን በእምነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ስለ ዓለም ሁኔታ ሀዘን ይሰመናል ፤ነገሮቹ ስበላሹ ወይም ሳይሳኩ  ስቀሩ በጣም ያሳዝናል፡፡የሆኖ ሆኖ በተመሳሳይ ጊዜ እግ/ር በሕይወታችን ላይ እጁ እንዳለዉ እና ከምህሬቱ የተነሳ ምንም እንደማይጎለን  እምነትና መተማመን አለብን፡፡ ደስታ ብዙ ሰዎች እንደምያስቡት በዉጫዊ ሁኔታ የሚቀሰቀስና በሌሎች ሰዎች ነገሮች፣ ቦታዎች፣ ሃሳቦች፣ ክስተቶች የተመሰረተ ከሆነ በእግ/ር ላይ ልመሰረት አይችልም፡፡ምክንያቱም ክርስቲያን ደስታን ከመልካም ስሜቶች ጋር ማመሳሰል የለበትም ፡፡

ለሁሉም ነገር መጀመርያ እና መጨረሻ አለዉ። ደስታም ለዘለዓለም ደስታነቱን ይዞ እይቆይም ሃዘን ቢሆን እንደዛዉ ነዉ፡፡መከፍታችን በሁለት መንገድ ይከሰታል። ይህም ደስተኞች ስንሆን ቋም ሆኖ እንድቀጥል ያለን ፍለጎትና ህመም ስሰማን ደግሞ አሁኑኑ እንድጠፍ ያለን መሻት ነዉ ፤ ይህ አብዘኛዉ ጊዜ አይሆንም። ምክንያቱም ደስታ ማጣት የልምድን ተፈጥሮአዊ ፍሰት ካለመቀበል የሚመጣ ነዉ። ቤንጃምን ፍራንክ እንደምለዉ “ዛሬ ሀብታም ቢትሆን ነገ ድሃ ልትሆን ትችላለህ ፤ ገንዘብ ሰዉን በጭራሽ አያስደስተዉም ፤የበለጠ ባላችሁ ቁጥር የበለጠ ፍላጎት ይበዛል” ይላል።

ሕይወት ማለት አንድ ነገር ሌላ ነገር ተከትሎ የሚመጣበት የመሆኑ ግንዛቤ መለማመዱ በእጅጉ ጠቃም ነዉ። አንድ የአሁን ጊዜ ሌላ የአሁን ጊዜን ተከትሎ ይመጣል። ደስ የሚያሰኘን ነገር በሚከሰትበት ጊዜ የሚመጣዉ ደስታ ግሩም ቢሆንም ዘገይቶ ግን በሌላ ነገር ፤ በሌላ አይነት ወቅት እንደሚተካ መረዳት አለብን ፡፡ይህን ከተቀበልን ወቅቱ ስለወጥ ዉስጣዊ ሰላም ይሰማል። የሆነ ችግር ወይም የሚያስደስት ነገር በገጠመህ ጊዜም ይህም እንደምያልፍ ማወቅ አለብን።ይህም በማቴ ወንገል ምዕራፍ 6፡19-20  የነገዉ ጭንቀት ለነገዉ ይበቃል፤ ስለዝህ ለነገ በማሰብ አትጨነቁ ፤ እያንዳንዱ ቀን በቂ የሆነ የራሱ ችግር አለዉ ይላል። ይህንን ግንዛቤ በልብ ዉስጥ ማስቀመጥ በችግርም  ጊዜ ቢሆን ግሩም መንገድ እንዳለ ያመለክታል።  

ደስታ ባዙዎች ማግኘት የሚፈልጉት ትልቅ የህይወት ስኬት ነዉ ፤ ሆኖም ግን የሚፈልጉትን ያህል በሰዎች ዘንድ  ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ እየተገኘ አይደለም። ቤተሰብ ደስተኛ ስሆኑ በዉስጣቸዉ የሚሰማ እርካታ፣ፍቅርና ኩራት ከፍ ይላል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን  በየዕለቱ ስራቸዉን ለመስራት ያለዉ የሚኖረዉ ተነሳሽነት፣ በሽታ የመከላከል አቅማቸዉ። ተግባብተዉ የመስራት ችሎታቸዉ ወዘተ ይጨምራል፡፡ የአካልና የአዕምሮ ጤንነትቸዉ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ መልኩ እጹብ ድንቅ ይሆናል፡፡ይህ ሁሉ ፍሬ ከቤተሰብ ደስታ ማሳ ከመታጨዱ አንጻር ነዉ ብዙ ሰዎች በህይወታቸዉ ደስተኛ ለመሆን የማንፈነቅለዉ ድንጋይ የለም ስሉ የሚንሰማዉ። ይሁን እንጂ ደስታ ለእያንዳንዱ የራሱ የሆነ ምዛን ወይም ልከት አለዉ ፤ ይህ ስባል እኔን የምያስደስት ሌላዉን ላያስደስት ይችላል፡፡ደስታ እንደ አረዳዳችን ይለያያል ፤ በጥቅት ነገር የሚደሰት ሰዉ እንዳለ ሁሉ ዓለምን በሙሉ ብጨብጥ እንኳ የማይደሰት ሰዉ አለ፡፡ስለዚህ የደስታ እርካታን ማወቅ የሚቻለዉ ሰዉ ባለዉ መደሰት፣ መርካት እና ማመስገን ስጀምር ነዉ።

የዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ ባራና በርገኔ።

03 July 2021, 11:27