ፈልግ

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሂደትን በጥንቃቄ መሰባበር ያስፈልጋል ተባለ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሂደትን በጥንቃቄ መሰባበር ያስፈልጋል ተባለ 

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሂደትን በጥንቃቄ መሰባበር ያስፈልጋል ተባለ

“ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ፣ ማርቆስ 5፡4) በመባል የሚታወቀው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት እየጣረ የሚገኘው በካቶሊክ ቤተክርስትያን ጥላ ሥር የሚተዳደሩ መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አልቆች ሕብረት በበላይነት የሚመራው ተቋም ሕግወጥ የሰዎች ዝውውርን ዑደት ለመስበር የሚያስችል በጥንቃቄ ሊከናወን የሚገባውን ሞዴል ላይ ያተኮረ አዲስ ዘመቻ በቅርቡ እንደ ሚጀምር ይፋ አደረገ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከ 20 እስከ 40 ሚሊዮን ሰዎች ዛሬ በዘመናዊ ባርነት ቀንበር ሥር እንደ ሚገኙ የሚገመት ሲሆን “ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) የተሰኘው ሕበረት ተቋም አባላት በተደጋጋሚ እንደ ሚገልጹት ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለዝሙት አዳሪነት ፣ ለሕግወጥ የሰው አካል ክፍል ንግድ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ከገቡበት ዘመናዊ የባርነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት የሚደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸው ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እንደ መቅሰፍት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ የተነሳ በተደጋጋሚ ማውገዛቸው ይታወሳል።

ሕገ-ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ  በዓመት ከ 150 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚሆን ትርፍ እያጋበሱ እንደ ሚገኙ እና ይህንን ሂደት ለማስቆም እና ብሎም ለማጥፋት የሚደርገው ጥረት ዘርፉ ከፍተኛ የሆነ ገቢ እያስገኘ የሚገኝ አዲስ ሕግወጥ የንግድ ዘርፍ በመሆኑ የተነሳ ሂደቱን ለመግታት እጅግ በጣም ከባድ እና አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለሆነም ግንዛቤን ለማሳደግ ፣ ተጎጂዎችን ለማዳን እና በሕይወት ለተረፉ ሰዎች ፈውስ ለመስጠት የሚሠሩ ቀሳውስት እና ደናግላን የሆኑ ሰዎች በአውታረ መረብ አማካይነት ዑደቱን ለማፍረስ እያደረጉት የሚገኘው እንቅስቃሴ ተጨማሪ “ጥንቃቄ” ያስፈልጋል ማለታቸው ተገልጿል።

ጥንቃቄ ልዩነት ሊፈጥር ይችላል

ድርጅቱ አዲሱን “#ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት የሚደርገው ጥረት ጥንቃቄ ያስፈልገዋል” በሚል መሪ ቃል በቲውተር ገጽ ላይ ሐሙስ ሐምሌ 15/2013 ዓ.ም ዘመቻው ሲጀመር ድርጅቱ ዓላማውን ሲያብራራ እንደ ገለጸው ዓላማው ልዩ “ጥንቃቄ” ማድረግ ልዩነቶችን እንዴት እንደሚፈጥር ለዓለም ለማሳየት ያለመ መሆኑን ገልጿል። “በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በምደርገው ዘመቻ ላይ ለሁሉም ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ጥንቃቄ፣ ለተጎጂዎች እንክብካቤ እና በሕይወት የተረፉትን መልሶ ማቋቋም” ያስፈላጋል በማለት ገልጿል።

እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚገኙ መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አለቆች ሕብረት የተመሰረተው “ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕብረት ከ 90 በላይ በሚሆኑ አገራት ውስጥ ከ50 በላይ በሚሆን በበይነ መረብ የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች ያስተባብራል።

እ.ኤ.አ. በ 2020 ዓ.ም “ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕብረት አውታረ መረቦችን በመጠቀም በዓለም ዙሪያ ለ 17,000 ሚሆን ሰዎችን ከሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲተርፉ በማድረግ የታደጋቸው ሲሆን ደህንነታቸው የተጠበቀ የመኖሪያ ቤት ፣ የትምህርት እና የሥራ ዕድሎችን በመስጠት ፣ ፍትህ እና ካሳ የማግኘት ድጋፍ እንዲሁም የጤና እንክብካቤ እና የስነ-ልቦና ድጋፍን በመስጠት ላይ እንደ ሚገኝ ሕብረቱ ይፋ አድርጓል።  በዚሁ ጊዜ ውስጥ ወደ 170 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች “ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕብረት በተደራጁ የመከላከያና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል ሕብረቱ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የሕበረቱ የጀርባ አጥንት ሆነው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደናግላን እህቶች ልምዳቸው እንደሚያሳየው “የረጅም ጊዜ እንክብካቤን የሚሰጡ ማዕከላት እያደረጉ የሚገኘው ጥረት እና አካሄዶች በሕይወት የተረፉ ሰዎች እንደገና በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የመጠቃት አደጋን ሊቀንሱ ይችላሉ” ማለታቸው ተገልጿል። የበለጠ ውጤታማ ለመሆን “እነዚህ አቀራረቦች በተቋማት ደረጃ አጠቃላይ ድጋፍ ይፈልጋሉ” በማለት አክለው አመልክተዋል።

“ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕገወጥ የሰው ዝውውርን ለመግታት ታስቦ የተቋቋመው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚተዳደረው ዓለም አቀፍ ሕብረት ዓለም አቀፍ አስተባባሪ የሆኑት እህት ጋብሪዬላ ቦታኒ እንደ ገለጹት በዚህ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት በሚደርገው ጥረት የተሳተፉት ገዳማዊያት የሆኑ እህቶች በመንፈሳዊነታቸው እና በእምነታቸው ጥልቅ ቁርጠኝነት ያላቸው እና የተጠናከሩ መሆናቸውን ገልፀው “መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መንስኤዎች እንዲቀንሱ ከተቻለም እንዲወገዱ በሚደርገው ጥረት ተሳታፊ እንዲሆኑ  ጥሪ እናቀርባለን። በሕገወት የሰዎች ዝውውር አማካይነት የሚገኘው ኢኮኖሚ ወደ እንክብካቤ ኢኮኖሚ እንዲሸጋገር በሚደርገው ጥረት ታሳትፊ ይሆኑ ዘንድ በክብሮ እንጠይቃለን” ማለታቸው ተገልጿል።

የመንግሥታት ሚና

“ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕገወጥ የሰው ዝውውርን ለመግታት ታስቦ የተቋቋመው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚተዳደረው ዓለም አቀፍ ሕብረት ዓለም አቀፍ አስተባባሪ የሆኑት እህት ጋብሪዬላ ቦታኒ አክለው እንደ ገለጹት በተለይም “መንግስታት ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ፣ የሥራ ፈቃድ እና የሥራ ዕድሎች ተደራሽነትን ማስፋፋት፣ የፍትህ እና የካሳ ክፍያ እንዲሁም የጤና እንክብካቤ እና የስነልቦና ድጋፍን ጨምሮ በሕይወት ለተረፉ ሰዎች የረጅም ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚተዳደሩ መንፈሳዊ ማሕበራት የበላይ አለቆች ዓለም አቀፍ ሕብረት በአውታረ መረብ አማካይነት የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከዘመናዊ ባርነት እንዲያመልጡ እና የነፃነት እና የክብር ህይወትን እንደገና ለመገንባት የሚያስችል መንገድ እንዲኖራቸው ድጋፍ ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን “ጣሊታ ቁሚ!” (አንቺ ልጅ ተነሺ ማርቆስ 5፡41) በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ሕገወጥ የሰው ዝውውርን ለመግታት ታስቦ የተቋቋመው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥራ የሚተዳደረው ዓለም አቀፍ ሕብረት ዓለም አቀፍ አስተባባሪ የሆኑት እህት ጋብሪዬላ ቦታኒ ጉዳዩን በተመለከተ እንደተናገሩት ሕብረቱ “የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጠቂ የሆኑትን እና እንዲሆም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ብቻ መርዳት ሳይሆን ነገር ግን በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ተጋላጭ የሆኑና የተገለሉ ማህበረሰቦችን ለማጎልበት ፣ እንዲሁም ጭቆና እና ብዝበዛን ማስቆም የሚያስችሉ ስርዓቶችን መገንባት ላይ ተጠምዷል” ብለዋል።

23 July 2021, 14:25