ፈልግ

የጃፓን ቤተክርስቲያን "10 ቀናት ለሰላም" በሚል መሪ ቃል የሚታደርገውን ጸሎት በቅርቡ ትጀምራለች! የጃፓን ቤተክርስቲያን "10 ቀናት ለሰላም" በሚል መሪ ቃል የሚታደርገውን ጸሎት በቅርቡ ትጀምራለች! 

የጃፓን ቤተክርስቲያን "10 ቀናት ለሰላም" በሚል መሪ ቃል የሚታደርገውን ጸሎት በቅርቡ ትጀምራለች!

በጃፓን የምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን "አስር ቀናት ለሰላም" በሚል መሪ ቃል የጸሎት ስነ ስረዓት ማከናወን እንደ ምትጀምር የገለጸች ሲሆን “ሕይወትን ሁሉ መጠበቅ ሰላምን ያስገኛል” የሚል መሪ ሐሳብ ያነገበ የዐሥር ቀን ጸሎት እንደሚከናወን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ በመባል የሚታወቁ ሁለት የጅፓን ግዛቶች እና ከተሞች ላይ በተጣለው አቶሚክ ቦምብ ጥቃት ሰለባዎችን ለማስታወስ “ሕይወትን ሁሉ መጠበቅ ሰላምን ያስገኛል” በሚል መሪ ቃል ለዐስር ቀናት ያህል ለሚከናወነው የጸሎት ወቅት ለዚህ አመት የተመረጠው ጭብጥ ሐሳብ “አስር ቀናት ለሰላም” የሚል አርእስት የተሰጠው ሲሆን እ.አ.አ ከመጭው ነሐሴ 6 እስከ ነሐሴ 15/2021 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በጃፓን ቤተክርስቲያኗ የምታካሂደው የፀሎት ዝግጅት ዓመታዊ ጭብጥ ሐስብ እንደ ሚሆን ከወዲሁ ተገልጿል።

ጭብጡ የተወሰደው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞ ነው

የጃፓን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት የናጋሳኪ ጳጳስ ጆሴፍ ሚትሱኪ ይህንን የዐስር ቀን ጸሎት በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ጭብጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ ከሕዳር 23-26/2019 ዓ.ም በጃፓን አድርገውት በነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት በዚያ አሳዛኝ ሁኔታ እና እስከ አሁን ባለው የኑክሌር ጦርነት ስጋት መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ መናገራቸውን አስታውሰዋል።

በስጋት ውስጥ ላለው ዓለም ሰላም አስፈላጊ ነው

የጃፓን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት የናጋሳኪ ጳጳስ ጆሴፍ ሚትሱኪ በመልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት ዛሬም ቢሆን በትጥቅ ግጭቶች ፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ የስደተኞች ቀውስ እና በአሜሪካ እና በቻይና መካከል እየጨመረ በመጣው “አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት” በሚፈጥሩ ውጥረቶች የተነሳ እነዚህ ጉዳዮች የዓለም ሰላም እና መረጋጋት አሁንም አደጋ ላይ እንደሚጥሉ የሚያሳይ ምልክቶች እንደሆኑ አክለው ገልጸዋል። በዚህ አውድ “የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር ሀገሮች ለሚገጥሟቸው ችግሮች በውይይት ለመፍታት የሚያደርጉ ጥረቶችን እንዲቀጥሉ ማበረታታት አለብን” ብለዋል። የጃፓን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት የናጋሳኪ ጳጳስ ጆሴፍ ሚትሱኪ በበኩላቸው አክለው እንደ ገለጹት ምንም እንኳን የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን የሚከለክል ስምምነት እ.ኤ.አ. በዚህ ዓመት በጥር 22/2021 ዓ.ም በድጋሚ መፅደቁ የሚታወስ ቢሆንም እና አሁንም አስገዳጅ የሆኑ ሕጎች ቢኖሩም ቅሉ ነገር ግን ገና ብዙ አገሮች እስካሁን ድረስ ይህንን ስምምነት ላለመተግበር እየዳከሩ እንደ ሚገኙ የገለጹ ሲሆን “በአገሮች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች እና የጅምላ አጥፊ ወይም አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች መኖር ለሰላም አስጊ ናቸው” ሲሉ በመልዕክታቸው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

የጃፓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንትም አክለው እንደ ገለጹት ሌሎች እንደ ማያንማር ወይም አፍጋኒስታን ባሉ አገራት ውስጥ ለአገራቱ ሕዝቦች እና የሰው ልጆች ሁሉ አክብሮት ከመስጠት ይልቅ “ለብሔራዊ ደህንነት እና ሀብት ቅድሚያ በሚሰጡት” ጠማማ የሆነ ሐሳብ ባላቸው አለም አቀፍ አካላት በሚያደርሱት ጥቃት የተነሳ ሕዝቦች መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እና ሰላማቸው ተነፍገዋል በማለት መናገራቸው ተዘግቧል።

ዓለም የበለጠ መተባበርን ይፈልጋል

የጃፓን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት የናጋሳኪ ጳጳስ ጆሴፍ ሚትሱኪ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የሚመለክት መልእክት ያስተላልፉ ሲሆን የበለጠ በአንድነት ይህንን ወረርሽኝ ለመግታት የሚደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉም በአንድነት እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበዋል። የበለፀጉ እና ጠንካራ ሀገሮች - የጃፓን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት የናጋሳኪ ጳጳስ ጆሴፍ ሚትሱኪ አክለው እንደ ገለጹት  “እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም በአቡ ዳቢ ተፈርሞ ይፋ በሆነው ሰንድ እና ከዚያን በኋላ ደግሞ ሁላችንም ወንድማማቾች ነን በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያፋ ባደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ሁሉም ወንድማማቾች እና እህተማማቾች በመሆናችን የተነሳ የእርስ በእርስ መተማመንን ለማጎልበት ”በእኩልነት የሁሉንም ህይወት ክብር በማክበር ድሃ አገሮችን መደገፍ አለብን” የሚለው ጭብጥ ሐሳብ መደገፍ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

ሁሉም ህይወት አስፈላጊ ነው

በሕገ ቀኖና ደንብ መሰረት ቤተክርስቲያን ማንም ከየትም ይምጣ ከየት፣ ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ሕይወት ጥበቃ ከፍተኛውን ትኩረት በመስጠት “ለሰላም ግንባታ የሚደርገውን ጥረት ታበረታታለች” ያሉ ሲሆን  ምክንያቱም “ሕይወት የግለሰብ ሕይወት ብቻ ሳይሆን በሰው ግንኙነት የተፈጠረ ነው። የቀደመው ደግሞ የኋለኛውን መጠበቅ ማለት ነው፣ ሰላም በሁሉም ሕይወት መካከል ስምምነት ማምጣት ማለት ነው” በማለት መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

እ.አ.አ 1982 ዓ.ም የተቋቋመው “አስር ቀናት ለሰላም”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በጃፓን ሐዋርያዊ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት (እ.ኤ.አ. የካቲት 25 ቀን 1981 ዓ.ም) ከእዚያን በኋላ ከአንድ አመት በኋላ ማለት ነው እ.ኤ.አ. በ 1982 ዓ.ም በጃፓን ጳጳሳት ጉባኤ  “አስር ቀናት ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ተነሳሽነት ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2019 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጃፓን ባደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት “የአቶሚክ ኃይልን ለጦርነት መጠቀምና ይህንን መሣሪያ ማከማቸት ሥነ ምግባር የጎደለው ተግባር ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በጃፓን በነበራቸው የመጀመሪያው ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት  የሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ” ሥፍራን በጎበኙበት ወቅት “ይህ የሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ ስፍራ ሞትና ሕይወት ፣ ኪሳራ እና ዳግም ልደት ፣ ሥቃይና ርህራሄ የተገናኙበት ስፍራ” እንደሆነ ገልፀዋል። ለጦርነት ዓላማ አቶሚክ ኃይል መጠቀምና ማከማቸት በራሱ ሥነ-ምግባር የጎደለው ተግባር መሆኑን ከታሪክ መማር እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው ጨምረው መግለጻቸው ይታወሳል።

እ.አ.አ በነሐሴ 6/1945 ዓ.ም 8፡15 ደቂቃ ላይ በሂሮሺማ ከተማ ላይ በተጣለው የመጀመሪያው አቶሚክ ቦንብ በወቅት ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ እንድትወድም ማድርጉ የሚታወስ ሲሆን ከእዚህም ጋር በተያያዘ መልኩ በእዚህ አቶሚክ ቦንብ ምክንያት በቅጽበት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል ደግሞ የአቶሚክ ቦንቡ ባደርሰው የጨረር አደጋ ቀስ በቀስ የ 70 ሺህ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ ይታወሳል።

ከእዚህ ከተጣለው የአቶሚክ ቦንብ መሣርያ ፍንዳታ የተረፈው ብቸኛው ሕንፃ የጄንባኩ ዶም በመባል የሚታወቀው የፈረሰ ሕንጻ ሲሆን ይህ ሕንጻ በሰው ልጆች ላይ እና በአጠቃላይ በሰብዓዊነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት ያስከተለ እጅግ አስከፊ የሆነ አደጋ መሆኑን ለማስታወስ፣ ይህ ስፍራ ዛሬ በሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ ፓርክ እምብርት ላይ ቆሞ ይታያል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባልፈው አመት ኅዳር 14/2012 ዓ.ም  ይህንን የሰላም መታሰቢያ ሥፍራ መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በሂሮሽማ በሚገኘው የጄንባኩ ዶም በመባል የሚታወቀው የፈረሰ ሕንጻ ሥር ሆነው ባደረጉት ንግግር ቅዱስነታቸው እንደገለጹት ይህንን በአቶሚክ ቦንብ መሣሪያ አማካይነት የተቃጣው አደጋ በተመለከተ ሲገልጹ “በእዚህ ነጎድጓድ መብርቅ በመሰለ ከፍተኛ ጥቃት እና የእሳት ፍንዳታ፣ ብዙ ወንዶች እና ሴቶች ፣ ብዙ ህልሞች እና ተስፋዎች ጠፍተዋል፣ ጥለውት ያለፉት ጥላ እና ዝምታ ብቻ፣ በቅጽበት ሁሉም ነገር በሞት ጥላ ተውጦ ነበር” ብለዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች እና ከአደጋው የተረፉ ሰዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በዚህ አሳዛኝ ጥቃት ተጎጅ ለሆኑ ሰዎች ያላቸውን ክብር ለመግለጽ እና እነርሱ በወቅቱ የነበራቸውን ጥንካሬ ምንጭ ለመገንዘብ ወደ እዚያ እዳቀኑ ገልጸው የነበረ ሲሆን “አሁን በሕይወት ለሌሉ እና የእዚህ አደጋ ሰላብ የሆኑ ሰዎችን ጩኸት እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ማሰማታችንን እንቀጥላለን” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የእዚህ የአቶሚክ ቦንብ ጥቃት ሰለባ የነበሩ ሰዎች “ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ፣ የተለያዩ ስሞች የነበሯቸው፣ የተወሰኑት ደግሞ የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገሩ እንደ ነበረ፣ ሆኖም ሁሉም በዚህች ክፉ እጣ ፈንታ በአንድነት ገፈት ቀማሽ ሆነዋል ፣ በዚህች ሀገር ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሳይቀር እስከ መጨረሻው ድረስ ለዘለቄታዊ የሆነ ምልክት ጥሎ ያለፈ ክስተት ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

የሰላም ተጓዥ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ አክለው እንደገለጹት እርሳቸው በበኩላቸው ወደ እዚያ ስፍራ ያቀኑት  “የሰላም ተጓዥ” በመሆን “የጥላቻ እና የግጭት ሰለባዎች የሆኑትን ድሆች ጩኸት ይዘው እዚያ ስፍራ መምጣታቸውን” የተናገሩ ሲሆን  “አሁን እኛ ባለንበት ጊዜ ውስጥ እያደገ የመጣውን ውዝግብ እና ግጭት የሚሰብኩ እና ሕዝቡን የሚያስጨንቁ፣ የእዚህ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ድምፅ አልባ” የሆኑ ሰዎችን ድምጽ ለማስተጋባት ጭምር እንደ ሆነ ገልጸው “የሰውን ልጅ አብሮ የመኖር ሕልውና አደጋ የሚጥሉ ተቀባይነት የሌላቸው ኢፍትሃዊ የሆኑ ተገባሮች እና በደሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን  መንከባከብ አለመቻላችን፣ በተጠናከረ መልኩ በቀጣይነት አየተካሄዱ የሚገኙት በጦር መሣርያ የታገዙ ግጭቶች ለሰላም ዋስትና የማይሰጡ ተግባራት በመሆናቸው የተነሳ” እነዚህን እኩይ ተግባራት ለማውገዝ ጭምር ነው ወደ እዚህ ስፍራ ያቀናውት በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

የኑክሌር ጦርነት ሥነ ምግባር የጎደለው ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ንግግራቸውን በቀጠሉበት ወቅት በድጋሚ እንደተናገሩት “የአቶሚክ ኃይልን ተጠቅሞ ጦርነት ማካሄድ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ዛሬ፣ በሰው ልጆች ክብር ላይ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ የጋራ መኖርያ ቤታችን በሆነች በምድራችን ላይ የሚፈጸም በደል ነው፣ የአቶሚክ ኃይል ለጦርነት መጠቀም ሥነ ምግባር የጎደለው ተግባር እንደመሆኑ መጠን፣ የአቶሚክ የጦር መሥርያ አምርቶ ማከማቸት በራሱ ሥነ ምግባር የጎደለው ተግባር ነው” በማለት በወቅቱ የተናገሩት ቅዱስነታቸው “ስለሰላም ብቻ በማውራት ሰላምን ግን በተጨባጭ በምድር ላይ በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ለማምጣት ባለመቻላችን ምጪው ትውልድ በእኛ ላይ እንደ ሚፈርድ” ገልጸው፣ አክለውም “ሰላም በእውነት ላይ የተመሠረተ ፣ በፍትህ የተገነባ ፣ በልግስና የተሟላ እና ነጻነትን የሚያስገኝ መሆን አለበት” ብለዋል።

በእጆቻችን ላይ የሚገኙ የኒውክለር የጦር መሣሪያዎችን እናስወግድ

“ይበልጡኑ ፍትሃዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ መገንባት ከፈለግን በእጆቻችን ላይ የሚገኙትን የኒውክለር የጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ ይኖርብናል” በማለት በወቅቱ በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው  “ግጭቶችን ለመፍታት እና ለግጭቶች መፍትሄ ለመስጠት የኑውክሌር ጦርነት መሳሪያ ይህንን ስጋት ለመቀረፍ የሚያስችል  ሕጋዊ የሆነ መስመር ነው ብለን በማሰብ የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎችን ለማጋበስ በምናደርገው ሩጫ የተነሳ እንዴት ሰላምን ማረጋገጥ እንችላለን?” በማለት ቅዱስነታቸው ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወሳል።“እውነተኛ ሰላም የሚረጋገጠው የጦር መሳሪያዎችን በማስወገድ ብቻ አይደለም ፣ ምክንያቱም ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ ማለት ስላልሆነ! በአንጻሩ ሰላም ማለት ከታሪክ እንደ ተማርነው እና እንደ ተረዳነው የፍትህ፣ የልማት፣ የአንድነት፣ የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከብ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን” ማለት በመሆኑ የተነሳ ጭምር ነው ማለታቸው ይታወሳል።

28 July 2021, 15:22