ፈልግ

ወጣትነትና ክርስትና ወጣትነትና ክርስትና 

ወጣትነትና ክርስትና

ክርሰትና የሚለዉ ቃል ክርስቲያኖስ ከሚለዉ የግሪክ  ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው። ክርስትና ሰዎች በፍቅር እግ/ር ተስበዉ ፤ ፈጣርያቸዉን አዉቀዉ ፤ ዕረፍትን ፈልገዉ ፤ በሕጉና በትዕዛዙ ፀንተዉ ፤ ለመኖር ስሉ ከዓለም ፍቃድ ተለይተዉ የሚኖሩበት ህይወት ነዉ። ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግ/ር ፈቃድ የሚደረግ ግን ለዘለዓለም  ይኖራል 1ኛ ዮሐ 2፡16 ፡፡ በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመርያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል።

የዚህ ዝግጅት አዘጋጅ እና አቅራቢ ባራና ባርጊኔ ቫቲካን

ወጣቶች በጉርምስና ዘመናቸዉ በመጀመርያ እግ/ርን ማወቅ አለባቸዉ ፡፡ በልባቸዉ ጥሩ የተባለ የእምነት መሰረት የሆነ ምሶሶ መትከል አለባቸዉ ፡፡ መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግ/ር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል ፡፡ ይሁን እንጂ ከዕዉቀት ብዛት እግ/ርን የካዱ ( እግ/ር የለም ) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸዉ ግልጽ ነዉ፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ ዕዉቀት እንዳልሆነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል ፡፡ሰነፍ በልቡ እግ/ር የለም ይላል መዝ ዳዊ . 13፡ 1 ፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር  ማለት እንጂ እግ/ርን አለማወቅ /መካድ ማለት አይደለም ፡፡

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ቁልፍ ይጫኑ!

ክርስትና በዕድሜ ፤ በጾታ እንዲሁም በት/ት ደረጃ የሚወሰን ሳይሆን በየተኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ሆነን የምንመራበት ሕይወት ነዉ። “በጊዜዉም አለጊዜዉም ጽና” ይለናል 2ኛ ጢሞ 4፡2። በሥጋችንና በነፍሳችን ፤ በሃሳባችንና በድርጊታችን ፤ በመዉጣትና መግባታችን ፤ በኑሯችን ሁሉ እግ/ርን የሚንፈልግበትና ከእርሱም ጋር ህብረት የሚናደርግበት የተቀደሰ ህይወት ነዉ ፡፡ነገር ግን በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንማለለስ ለእያንዳንዳችን ኀብረት አለን ተብሎ እንደተጻፈ ክርስትናችን በብርሃን እየኖረንና እየተመላለስን ከአምላካችን ጋር ኀብረት የሚናደርግበትም ነዉ (1ኛ ዮሐ 1፡7) ፡፡

እግ/ርን ማወቅ ትርጉም ያለዉ ህይወት ይሰጣል ፡፡ በምድራችን ትርጉም ያለዉ ህይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት ፤ ንብረት ፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል ፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያለዉ ህይወት መኖር የሚቻለዉ  ከላይ የተጠቀሱት መሟላት ብቻ ሳይሆን በመንፈስ መርካት ነዉ ፡፡ ለዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሰሌ  ይሆናል ፡፡ ዘኪዎስ ጌታዉን ሳያዉቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበረ ፤ አምላኩን ሲያዉቅ ግን #ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታዉን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለዉ $ ሉቃ 19፡9 በማለት አድሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል።

ወጣትነት በሰዉ ልጆች አጠቃላይ ሕይወትና በክርስቲያናዊ ኑሮ ዉስጥ ትልቅ ድርሻ አለዉ  ፤ ምክንያቱም የወጣትነት ዘመን ቢሰሩ የማይደክሙበት፤ ቢሮጡ የሚቀድሙበት ፤ ስያረጁ የሚጦሩበትን ሀብት እና ንብረት የሚያፈሩበት የዕድሜ ክልል በመሆኑ ነዉ ፡፡ ስለሆነም በክርስትና ሕይወት ዉስጥ ስንኖር  ጉዟችን  ሁሉ የተሳካ ፤ በማስተዋል የሚደረግና እግ/ርንም ደስ የሚያሰኝ ሊሆን ይገባዋል፡፡  ወጣትነታችን ሥጋችንንም ሆነ ነፍሳችንን የሚቀደስበት ህይወት እንዲሆን ጥረት ማድረግ የሁላችን ድርሻ ነዉ፡፡ #ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች $፡፡ እንደተባለ ወጣትነታችን የማንሰራበት ወቅት ከመድረሱ በፍት  ያለ የሥራ ክፍለ ጊዜ ነዉ ፡፡ዮሐ 9፡4 ፡፡ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣርህን አስብ ፤ ደስ አያሰኙም የሚትላቸዉም ዓመታት ሳይደርሱ የተባልነዉም ወጣትነታችን የጉብዝናችን ወራት ስለሆነ ነፍሳችንንና ስጋችንን ሊጠቅም የሚችል በጎ ስራ እንድንሰራበት ነዉ (መክ 12 ፡ 1) ፡፡

ክርስትና ለወጣቶች ታርክን ይቀይራል ፡፡ ይህም ማለት ሰዎች እግ/ርን ስያዉቁ ዘማዊ የነበረዉ ድንግል ፤ ዘረኛና ወገንተኛ  የነበረዉ ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍታሃዊ ፤ አሳዳጅ የነበረዉ ስለ ክርስቶስ ተሳዳጅ ፤ ክፉ የነበረዉ ደግ ፤ ዘፋኝ የነበረዉ ዘማሪ ፤ ነፍስ ገዳይ የነበረዉ የሰዉን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ ለዘህም ቅዱስ ጳዉሎስ ጥሩ ምሳሌ ነዉ ፡፡

ክርስትን ለወጣቶች እንደ እግ/ር ፍቃድ እንድመላለሱ ዓይነ ልቦናቸዉን ያበራል ፡፡ እግ/ር ከእኔ ይልቅ ስለእኔ  ያስባል ብሎ ማመን ነዉ ፡፡ የእግ/ርን ፍቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል ፡፡ ዮሐ 2 ፡17 ፡፡ የጌታችን ፍቃድ ሁሉ የእግ/ር እንደሆነ  ሲያስተምር # አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ዉሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን  የአንተ እንጂ $ ሉቃ 22፡ 42 ፡፡ ምክንያቱም ሀዋርያዉ እንደተናገረ ስለ በጎ ፍቃድ መፈለግንም  ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግ/ር ነዉና ይለናል (ፊሊ 1 ፡ 13) ፡፡

ክርስትና ለወጣቶች የፍቅር ምንነትን ያስተምራል ፡፡ በክርስትና መጀመርያዉም መጨረሻዉም ፍቅር ነዉ ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር የሌለዉ እግ/ርን አያዉቅም ፡፡ እግ/ር ፍቅር ነዉና  1ኛ ዮሐ 4 ፡8 ፡፡ በመሆኑም ያለ ፍቅረ ክርስትና የለም ፡፡ ቢኖር እንኳን ቅዱስ ጳዉሎስ እንደተናገረዉ ከንቱ ነዉ ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ ይላልና (1ኛ ቆሮ 13 ፡ 1) ፡፡

ክርስትና ወጣቶችን በእምነት አንድያድጉ ያቃናል ፡፡ ብዙዎች ክርስቲያን ተብለዉ ይጠራሉ ፤ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ዉስጥ በጥበብ ይኖራሉ ፡፡ እምነት ተስፋ ስለሚናደርገዉ ነገር የሚያስረግጥ የማናየዉን ነገር የሚያስረዳ ነዉና ዕብ 11፡ 1 ፡፡ ስለዚህ ወጣት በህይወቱ ተስፋ የተሞላ ኑሮ ይኖር ዘንድ በእምነት ማደግ አለበት ፡፡ የሰዉ ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለዉም ፡፡ ያለኝ ይበቃል አይልም ፡፡ አመንዝራ ስያይ  በፍትወት ስሜት ያቃጠላል ፤ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛዉ ጠቢቡ ሰለሞን ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለዉ ፡፡

ክርስትና ወጣቶች ተስፋ እንዳይቆርጡ ያጠነክራል ፡፡ ሁሉንም ነገር ተወዉ፡፡ ህይወት እንደሆነ በጀንበር መዉጣት እና መጥለቅ እየቀጠለች ነዉ ፡፡ የአንተ ቀን ደግሞ ዛሬ ብቻ ናት ፡፡ነገ ያንተ አይደለም ነገ የእግ/ር ብቻ ናት ፡፡ ስለዚህ መመለስ በማትችለዉ ዛሬ ዉስጥ የማይጠፋዉን ኑሮ ለመኖር ተሰናዳ ፡፡ በቁጣና በምሬት ዉስጥ ሆነህ ቀንህን አትኑረዉ ፡፡ በምድር ላይ ያለህ ዕድሜ እጅግ በጣም ጥቂት ነዉ፡፡ እንኳን በምሬትና በክፋት በማሰብ ቀርቶ የጀመርከዉን መልካም ነገር እንኳን ለመጨረስ እጅግ አጭር ጊዜ ነዉ ያለህ ፡፡አንተ ምን እንዳጣህ ፣ ምን እንደጎደለህ ፣ ምን እንደምያስፈልግህ ፣ ... አምላክ እግ/ር ያዉቃልና አትጨነቅ ፣ ተስፋ አትቁረጥ ፡፡

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ “ክርስቶስ ሕያዉ ነዉ” በተሰኘዉ ሐዋርያዊ ማነቃቂያቸዉ ላይ ጌ.ኢ. ክርስቶስን እንደ ወጣት ገልጸዉታል ፡፡በመጽሐፍ ቅዱስ የጌ.ኢ .ክርስቶስን ወጣትነት በሰፊዉ ባይገለጽም በጥቅቱ ከምናገኘዉ ገለጻ በወጣትነቱ ለተልዕኮዉ በቂ ዝግጅት ያደረገና ተልዕኮዉን ገና በ33 ዓመቱ በተገቢዉ ሁኔታ መፈጸሙ ለዘመኑ ወጣቶች አርአያና አስተማር ሊሆን ይችላል ይላሉ ፡፡ ወጣቶች ጊዜ ሳያጠፉ ራሳቸዉን ለተልዕኮ እንዲያዘጋጁና እምቅ ኃይላቸዉን ለተፈጠሩበት ዓላማ እንዲያዉሉ የኢየሱስ ህይወት እንደ አንድ ወጣት ጥሩ ማነቃቂያ ነዉ ፡፡

በቤተክርስቲያናችን ታሪክ በርካታ ወጣት ቅዱሳን ይገኛሉ ፡፡ በአፍላ የወጣትነታቸዉ ዘመን የተሰጣቸዉን ተልዕኮ በባቃት በመፈጸም ፈርሃ እግ/ር ያደረበት ማህበረሰብ እንድገነባ እና የእግ/ር መንግስት እዉን እንድሆን የተጉ ናቸዉ ፡፡የሀገራችንም ታሪክ  በጥልቀት ብንመረምረዉ በርካቶች በወጣትነታቸዉ ህይወታቸዉን ለሀገር ዕድገት ፣ ክብር ፣ ነጻነት መስዋዕት ያደረጉ እና አሁን ያችንን ሀገር ያቆዩልን እናገኛለን ፡፡ስለዚህ የዘመኑ ወጣት ከአልባለ ተግባራት ወጥቶ ፍቅር ፣ሰላም ፣ፍትህ ፣አንድነት የሰፈነበት ሀገር ለመገንባት እና ፈርሃ እግ/ር የሰፈነበት ህበረተሰብ በመፍጠር የእግ/ር መንግስት እንድስፋፋና  በሀገር ግንባታ አስተዋፅኦ ማድረግ ያለበት አሁን ነዉ ፡፡ ር.ሊጳ.ፍራንቺስኮስ “ወጣቶች የእግ/ር አሁን ናቸሁ ይላል” ፡፡ ይህ አባባል ወጣቶች የዛሬ ተመላካቾች የነገ ተረካቢዎች አይደሉም፡፡ ዛሬ ነዉ ነገ የሚጀመምረዉ ማለታቸዉ ነዉ ፡፡ ወጣቶች አሁኑኑ ወደ ተግባር መግባት አለባቸዉ ፡፡ ልምድ ካላቸዉ ጋር ጎን ለጎን በመሄድ  ነገ የሚጠብቃቸዉን ሃላፍነት ተግባር ዛሬ መጀመር አለባቸዉ  ይላሉ፡፡

11 June 2021, 15:39