ፈልግ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደኅንነት ዕቅድ ስላላት ድርሻ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደኅንነት ዕቅድ ስላላት ድርሻ 

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደኅንነት ዕቅድ ስላላት ድርሻ

አሁን ያለንበት ወር የግንቦት ወር ሲሆን ይህ ወር በወር ደረጃ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የማርያም ወር እየተባለ እንደ ሚጠራ ይታወቃል። በእዚህ ምክንያት “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደኅንነት ዕቅድ ስላላት ድርሻ” በሚል አርዕስት ያዘጋጀነውን አስተንትኖ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

 የብሉይና የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደዚሁም ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የከበረ ልማድ የመድኃኔ ዓለም እናት በደኅነት ሥራ ላይ ያላትን ትልቅ ድርሻ አጉልተው ያሳያሉ ፤ እንዲመረመርም “ከፊታችን” ያቀርቡታል። የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ ወደ ዓለም ይመጣ ዘንድ ቀስ በቀስ ይዘጋጅ በነበረበት ጊዜ የደኅንነትን ታሪክ ዘርዝረው ይናገራሉ። እነዚህ ጥንታውያን መጽሐፍት በቤተ ክርስትያን በሚነበቡበት ጊዜ ፍጹምና የተሟላ ከሆነ ከብርሃን መታየት ፊት አድርገን ስንረዳቸው ቀስ በቀስ የመድኃኔ ዓለም እናት የሆነችውን የሴትን ምስል ግልጥ አድርገው ያመጡልናል።

በዚሁ ክሥተት ፊት በሚደረገው ንባብ መሠረት የቀድሞ ወላጆቻችን ወደ ኃጢአት ከወደቁ በኋላ በእባቡ ላይ ድል እንደምታገኝ አስቀድሞ በትንቢት የተነገረላት ሴት እርስዋ ናት ዘፍ 3፡15። እንዲሁም “አማኑኤል ተብሎ የሚጠራውን ልጅ የምትፀንስና የምትወልድ ድንግል” ኢሳ 7፡14 ፤ ሚል 5፡2-3 ፤ ማቴ 2፡22-23 እርሱዋ ናት። በታማኝነት እየተጠባበቁ ደህንነትን ከሚያገኙ ከጌታ ድኾችና ትሑታን መካከል ከፍ ብላና ደምቃ ስለምትታይ ማንም ለይቶ ያውቃታል።

ሰው በተስፋ ይጠብቃቸው የነበሩ ብዙ ዘመናት ከተፈጸሙ በኋላ በምስጢረ ሥጋዌ ከጽዮን ልጅ ጋር አዲስ ኪዳን ተመሠረተ። ይህ የሆነው ወልድ አምላክ ሰውን ከኃጢአት የነበሩ ብዙ ዘመናት ከተፈፀሙ በኋላ ከጽዮን ልጅ ጋር አዲስ ኪዳን ተመሠረተ። ይህ የሆነው ወልድ አምላክ ሰውን ከኃጢአት የነበሩ ብዙ ዘመናት ከተፈሙ በኃላ ከጽዮን ልጅ ጋር አዲስ ኪዳን ተመሰረተ። ይህ የሆነው ወልድ አምላክ ሰውን ከኃጢአት ነፃ ያወጣ ዘንድ በምስጢረ ሥጋዌ ከእርስዋ ሰብአዊ በአሕርይን በወሰደ ጊዜ ነው።

አዲንት ሴት የሞትን ምክንያት እንዳመጣች እንዲሁም አንዲት ሴት የሕይወትን ምክንያት ታመጣ ዘንድ የምሕረት አባት የሆነ እግዚአብሔር አብ “እናት ለመሆን ከጥንት ጊዜያት ተወስና የነበረችው ‘እሺታ’ ከምሥጢረ ሥጋዌ በፊት እንዲሆን ፈቀደ። ይህም ሁሉን የሚያድስ ሕይወትን ለዓለም ለሰጠችና እንደዚህ ላለው ከፍተኛ ሥራ ተገቢዎች በሆኑ በእግዚአብሔር ሀብት ለበለጸገች ለኢየሱስ እናት በልዩ አኳኋን የሚስማማ ነው።

ስለዚህም በቅዱሳን አበው ዘንድ ማርያምን “የአምላክ እናት ፤ ፈጽሞ ቅድስት ፤ በኃጢአት እድፍ ያልተነካች ፤ በመንፈስ ቅዱስ የተሠራች አዲስ ነገር ፤ አድስ ፍጥረት” ብሎ የመጥራት ልማድ መኖሩ የሚገርም ነገር አይደለም። ወዲያው ስትፀንስ ተወዳዳሪ በሌለው በቅድስና ውበት ያጌጠችው የናዝሬቷ ድንግል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከተላከው መልአክ “ጸጋ የመላሽ” ሉቃ 1፡28 የሚል ሰላምታን ትቀበላለች ፤ ለሰማያዊ መልእክተኛ “እነሆ የጌታ ባርያ እንደቃልህ ይሁንልኝ” ሉቃ 1፡38 በማለት መልስ ሰጠች።

በመሆኑም የአዳም ልጅ የሆነችው ማርያም ለመለኮታዊ ቃል እሺ ስላለች የኢየሱስ እናት ለመሆን በቃች። በሙሉ ፈቃድዋ አንዳች የኃጢአት እድፍ በሌለበት ሁሌታ የእግዚአብሔርን የማዳን ፈቃድ በሙሉ በመቀበልም የጌታ አገልጋይ እንደመሆንዋ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ጸጋ በእርሱ ሥር ከእርሱ ጋር በልጅዋ አካልና ለሥራው ራስዋን በሙሉ ሰጠች።

እንግዲህ ቅዱሳን አበው ማርያም በሰብአዊው የደኅንነት ሥራ ላይ ነፃ እምነትና ታዛዥነት በተሞሉበት መንፈስ ተባባሪ ሆነች። በእግዚአብሔር እጅ የምትገፋ መሣርያ አልሆነችም ማለታቸው ነው። ቅዱስ ኢረኒዩስ እንደሚለው “እርሱዋ ታዛዥ በመሆኗ ለራስዋና ለመላው የሰው ዘር የደኅንነት ምክንያት ሆነች። እንደዚሁም የጥንት አበውም ሲሰብኩ ከዚሁ ቅዱስ ጋር በመተባበር “የሔዋን የእንቢተኝነት ቋጠሮ በማርያም ተፈታ ፤ ሔዋን ባለማመንዋ ያሰረችውን ነገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማመንዋ ፈታችው።” በሁለቱም መካከል ንጽጽር በማድረግ ለማርያም “የሔዋን እናት” ብለው ይጠሩዋታል ፤ ቀጥሎም “ሞት በሔዋን መጣ” “ሕይወት ግን በማርያም መጣ” ይላሉ።

የእናትና የልጅ አንድነታዊ ትብብር የደኅንነት ሥራ ላይ የታየው ከክርስቶስ በድንግልና መፀነስ እስከሞቱ ድረስ ባለው ጊዜ ውሥጥ ነው። እነሆ የመጀመሪያውን አንድነትዋ ትብብር ስታይ ፤ ማርያም ተነሥታ በፍጥነት ወደ ኤልሳቤጥ በሄደች ጊዜ የተደረገላትን የደህንነት ተስፋ ስለአመነች “ብፀዕት” ተባለች ፤ በዚያን ጊዜም የጌታን መንገድ አቅኚ ገና “ከእናቱ ማኅፀን ሳለ በደስታ ዘለለ” ሉቃ 1፡41-45 ፤ ቀጥሎም የጌታ በልደት ጊዜ የድንግልንዋን ምላት የቀደሰች ያልቀነሰ የበኩር ልጅዋን ለእረኞች ለሰብአ ሰገል ባሳየች ጊዜ ነው።

ማርያም የድኾችን መሥዋዕት ይዛ ሕፃኑን በቤተ መቅደስ ለጌታ ባቀረበች ጊዜ ስምኦን “ሕፃኑ ፤ የብዙዎች የልብ ሐሳብ ይገለጥለት ዘንድ የተቃውሞ ምልክት ሊሆን ነው ፤ በእናቱም ልብ ውሥጥ ሰይፍ ያልፋል” ሉቃ 2፡35 ብሎ ሲናገር ሰማች። ሕፃኑ ኢየሱስ በጠፋ ጊዜ ወላጆቹ እየተጨነቁ ከፈለጉት በኋላ በአባቱ ጉዳዮች በሐሳብ ተይዞ በቤተ መቅደስ አገኙት። ልጁ የሰጣቸውን መልስ አልተረዱትም። እናቱ ግን ስለዚሁ ነገር ታስብ ነበር ሉቃ 2፡41-51።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራውን በይፋ በጀመረ ጊዜ ማርያም ታላቅ ስፍራ ይዛ ትታያለች። ይህም መታየት የጀመረው ቀደም ብሎ ነው። ማርያም በቃና ዘገሊላ ሠርግ በርኅራኄ ስለተነሣች በምልጅዋ የመሢሁ የኢየሱስ ተአምራት እንዲጀመር አደረገች ዮሐ 2፡1-11 እርስዋ የሰማችውን በታማኝነት እየጠበቀች ሉቃ 2፡19 ፤ 21 ልጅዋ በስብከቱ ከሥጋና ከደም አስተሳሰቦች በላይ በሆነ ስሜት መንግሥተ ሰማያትን የሚያሞግስ ንግግር ባደረገበት ወቅት “የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው” ማር 3፡35 ፤ ሉቃ 11፡27-28 ባለ ጊዜ ከእርሱ ምስጋናን ተቀበለች።

እንደዚህ ባለ ሁኔታ ብፅዕት ድንግል ማርያም በእምነት ጉዞ ወደፊት እየተራመደች ከልጅዋ ጋር ያላትን አንድነት እስከመስቀል ድረስ ጠበቀችው። ለመለኮታዊ እቅድ ምንም ሳትርቅ ስለ አንድ ልጅዋ ጥልቅ ሐዘን እየተሰማት በመስቀል ሥር ቆመች ዮሐ 19፡26። በዚያም እናታዊ ፍቅር በመላበት መንፈስ በመስዋዕቱ ተባበረች ፤ የወለደችው ልጅዋን እራሱን ለመስዋዕትነት ሲያቀርብ ፍቅር በመላበት ስሜት እሽታዋን ገለጸች። በመጨረሻም በመስቀል ላይ ሞቱን ይጠባበቅ የነበረው ኢይሱስ “አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ” ብሎ “ለደቀ መዛሙርቱ እንናት ትሆን ዘንድ ሰጣት” ዮሐ 19፡26-27።

እግዚአብሔር በክርስቶስ ተነግሮ የነበረውን መንፈስ እስኪልክ ድረስ የሰው ዘር የሚድንበትን ምስጢር በይፋ ማሳየት ስላልፈለገ ከበዓለ ሃምሳ በፊት ባለው ቀን “ሐዋርያት ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ሲተጉ” የሐ 1፡14 እናያቸዋለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞ የምሥራች ሲነገራት ያጠጣት የመንፈስን ስጦታ ለማግኘት በጸሎት ስትለምን እናያታለን።

በመጨረሻም “ከኃጢአት ሁሉ ነፃ የሆነችው” ንጽሕት ድንግል ምድራዊ ጉዞዋ ወደ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ በነፍስና በሥጋ ወደ ሰማያዊ ክብር ተወሰደች። “የጌታዎች ጌታ”ራእ 19፡16 የሆነው ኃጢአትና ሞትን የሚያሸንፍ ልጅዋን ትመስል ዘንድ እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ንግሥት አደረጋት።

ዋቢ መጽሐፍ

የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ የአማርኛ ትርጉም

ስለመለኮታዊ መገለጽ ምዕራፍ ፰ ከቁጥር ፳፭ - ፳፱

አቅራቢ አባ ቢኒያም ያዕቆብ 

        

04 June 2021, 11:10